Get Mystery Box with random crypto!

Mushitaq tube ሙሽታቅ ቲዩብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ mushitaq_tube — Mushitaq tube ሙሽታቅ ቲዩብ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mushitaq_tube — Mushitaq tube ሙሽታቅ ቲዩብ
የሰርጥ አድራሻ: @mushitaq_tube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 290
የሰርጥ መግለጫ

#هدفنا الأكبرهو الاتباع الحق / ونشر الخير@
እውነታን መከትል እና# /ኸይርን ማስፋፋት
Chanalun
https://t.me/ oenAgZ8QStdlZDk0
☟︎︎︎ወደ #YouTube ቻናላችን☟︎︎︎
https://youtube.com/channel/UCU9vnAaFwHNYCN0WQE_2ZJA

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-11-27 21:28:28 من_ديوان_الرجال_የወንዶች_መዝገብ

ሙሀመድ ኢብኑ ዋሲእ ወደ ቁተይባህ ቤት ገብተው ሲያዩዋቸው የሱፍ (ከበግ ፀጉር የተሰራ) ልብስ ለብሰዋል

ለምን እንዲህ አረግክ አሏቸው ዝም ..... አሉ
አሁንም "እያናገርኩህ አትመልስም??? " አሉ
ከዛም ሙሀመድ "የዝህድና ነው እንዳልልህ ራሴን ከፍ ያረግኩ ይመስለኛል
የድህነት ነው እንዳልልህ ጌታየን ያማረርኩ ይመስለኛል" አሉ

አመስግን ዝም ብለህ ሪዝቅ በምን በኩል እንደሚመጣ አታውቅም

https://t.me/mushitaq_tube
74 views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-26 21:17:46 #አሰላሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱህ#

#ታታር_ከየእጁጅና_መእጁጅ_በፊት_የመጡ_የእጁጅና_መእጁጆች
   እውነተኛ ትክክለኛ ታሪክ ነው
ክፍል 1
መጀመሪያ ለምን በየእጁጅና መእጁጅ ለምን ገለፅኳቸው??
ከነብዩሏህ ኑህ በሁዋላ የመጣው የሰው ዘር ባጠቃላይ የልጃቸው የሶስቱ ልጆች ዘር ነው
1 ሀም ኢብኑ ኑህ
2 ሳም ኢብኑ ኑህ
3 ያፊስ ኢብኑ ኑህ
የእጁጅ እና መእጁጅ የሚባሉት የያፊስ ዝርያ ናቸው
ታታሮች ከዚሁ ያፊስ ኢብኑ ኑህ ዘር ነበሩ

" የታታሮች መነሻ "
የታታሮችን አነሳስ ከማየታችን በፊት በጊዜው የነበሩትን ልዕለ ሀያላን አካላቶችን እንመልከት።
1/ ሙስሊሙ ኡማ :- ምንም እንኳ የሙስሊሙ ዓለም ግዛት እጅግ ሀያልና የዓለምን ግማሽ አካል ቢያስተዳድርም የተቦጫጨቀና በትንንሽ ግዛቶች የተከፋፋለ ነበር። የዓባሲያው ኺላፋ እንደ በላይ አካል የተሾመውም ለስም ብቻ እንጅ ምንም አይነት ስልጣን አልነበረውም።

ኸሊፋዎቹም ቢሆኑ የሙስሊሙን ኡማ ችግር ከመቅረፍ ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም በማሳደድ የተጠመዱ ነበሩ።
ልክ እንደ አሁኑይቱ የሳውዲ ግዛት ለስልጣን እንጅ የእምነትን ጉዳይ ጀርባቸው ጥለውት ነበር

ህንድ፣ ኸዋርዚም ፣ሒጃዝ ፣የመን ፣ሻም ፣ግብፅ ፣ሰሜን አፍሪካ፣ አንደሉስ፣ ቱርክ እንዲሁም ፊሊስጢን ሁሉም የየራሳቸው ሙስሊም አስተዳዳሪ የነበራቸው ሲሆን አስተዳዳሪዎቹም እርስ በርስ የሚናቆሩና ለፀብ የሚፈላለጉ ነበሩ።

እነዚህ ሁሉ ተዳምረው የሙስሊሙን ኡማ ሀይልና ክብር አዳክመውታል።

2/ መስቀላውያን:- በጊዜው ከነበሩት ኃያላን የሚመደቡ ቢሆንም በሰላሁዲን አል አዩቢ ባደረሰባቸው ተከታታይ ሽንፈቶች ተዳክመው ነበር።
ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ሙስሊሙን ለመዝመትና የተወሰደባቸውን መሬት(ቁድስን ሶላሁዲን አልአዩቢይ በገራሚ ታሪክ መቀማቱን ታሪክ አይረሳውም) ለመንጠቅ ምኞታቸው እንዳለ ነበር።

በዚህ መሐል  ታታር የተባለ ሀይል መነሻውን ሞንጎሊያ አድርጎ አለምን በወረራ አጥለቀለቀው። በሒጅራ በሰባተኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ (603 አመተሂጅራ)ታዋቂው የታታሮች መሪ ጂንኪዝ ኻን(ቺንግስ ካን) ግዛቱን ለማስፋት እንቅስቃሴውን ጀመረ።
ደም የሚወድና ርህራሄ የማያውቅ ሰው ነው
በሚደንቅ ሁኔታ የዛሬወቹን ቻይና፣ ኮሪያ፣ ቬትናም፣ ሳይቤሪያ፣ ሞንጎሊያ፣ ታይላንድ፣ ኔፓልና ማይናማርን ከግዛቱ ጨመረ።

ታታሮች ሀይማኖታቸው ቺንግስ ኻን ባዘጋጀላቸው "ያሰክ" በተባለ መፅሐፍ የሚመራ ነው።
አንዳንዶችም
እምነት እንደሌላቸው ጋብቻ የማያውቁ ሀላልና ሀራም የሌለው ኑሮ የሚኖሩ እነደሆኑ ይገልፃሉ" አህመድ ዘይኒ ዳህላን 

የታታሮች ጦርነት ብዙ ልዩ ባህሪያቶች አሉት።ከነርሱ መካከል

የተዋጣና የተስተካከ አደረጃጀት
እጅግ ግዙፍ የሰው ሀይል
የተካኑ የጦር መሪዎች
ርህራሄ አለማወቅ
አስቸጋሪ ሁኔታዎችን የመጋፈጥ ችሎታ
የሌሎችን ሀሳብ አለመቀበል
ቃል ኪዳን አለመጠበቅ

እነዚህ ባህሪያት በሀይማኖት ለማይመራና ፈጣሪን ለማይፈራ አካል ሲሟሉ ምን አይነት ጭካኔና ግፍ እንደሚያደርስ መገመት አይከብድም።
የጥሜት ሀይሎች ምንም ያህል ቢለያዩም ሀቅን ለመደርመስ የሚተባበሩ መሆናቸው አይሰወርብንም።
መስቀላውያን ለታታሮች ቀኝ እጅ መሆናቸው የሚጠበቅ ነው። እነርሱም ያደረጉት ይህን ነበር። በተደጋጋሚ ወደ ታታሮች የተለያዩ መልዕክተኞችን በመላክ ( ለመሄድ ብቻ ከ12 ሺህ ኪ.ሜ አቋርጠው )

የአባሳውያን ኺላፋ የድክመት ማማ ላይ እንደሆነና ሙስሊሙ አለምም ፍፁም ሊቋቋማቸው እንደማይችል፣ አባሲያዎች ያላቸውን ሊቆጠር የሚያታክት ሀብት እየጠቀሱ በማጎምጀት እነርሱም እንደሚያግዟቸው በመግለፅ ሙስሊሙን ዓለም እንዲወሩ በመገፋፋት የበኩላቸውን ሚና ተጫወቱ።...
እንዴት ወረሩ????
https://t.me/mushitaq_tube

ክፍል 2......ይቀጥላል……
78 views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 22:04:27 ታታር ከየእጁጅና መእጁጅ በፊት የመጡ የእጁጅና መእጁጆች

የሙስሊሞች እስካሁን ድረስ ያልገጠማቸው ሊገጥማቸውም የማይችል ታሪክ

ገና ሊደርስ ሲል.....

መዲና  በመብረቅ ጩኸት ሁለት ቀን አሳለፈች  በመጨረሻም የመሬት መንቀጥቀጥ ገጠማት
የነብያችን መስጅድ በከፊሉ ተቃጠለ የቀብራቸውን አካባቢ ሳይነካ
ተራራው እንደ እሳት ፈሰሰ ይህ እሳት ከወር በላይ ቆየ
ምን አይነት ፈተና ቢሆን ነው????

ከመካ መዲና አልፎ ባግዳድም.... ታሪኩን ልንጀምረው ነው በደንብ ገባ ገባ በሉ share share join
https://t.me/mushitaq_tube
81 views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 23:08:19 ታታር ከየእጁጅ እና መእጁጅ በፊት የመጡ የእጁጅና መእጁጆች

እነማን ናቸው???

እስካሁን ድረስ የታሪክ ዘጋቢዎች የእስልምና ኡመት ከዚህ ፈተና የበለጠ ተፈትና አታውቅም አሉ


ምን አይነት ፈተና ነው አሁን ካለንበት አጣብቂኝ የከፋ???

ይህ ፈተና ሊከሰት ገና ትንሽየ አመታት ሲቀረው ለዚህ ፈተና ምልክት 
የካእባ ጨርቅ በንፋስ ተገንጥሎ ለ21 ቀን ካእባ ራቁቱን አሳልፎ ነበር

በጥቁር ደመናም ተሸፍኖ ነበር
ምን ይሄ ብቻ
መዲናም ..............

በቅርቡ ሙሸረታቅ ቲዩብ ጋር ይጠብቁን እስከዛ share

ነገ ጀምሮ https://t.me/mushitaq_tube https://t.me/mushitaq_tube
82 views20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 17:17:26 የሞንጎሊያ(እምነት የሌላቸው) ህዝብ 40 ሺሁ እንዴት ሰለመ???

የክርስቲያን ህዝቦች ሞንጎሊያን ለማስለም ብዙ ይጥሩ ነበር ጋብቻም ይፈፅሙ ነበር
ሆላኮ ሚስቱ ክርስቲያን ስለሆነች ለክርስቲያኖች ዳእዋ ፈቅዶ ነበር

አንድ ቀን የሞንጎሊያ(ተታር) መሪ ክርስቲያን ጋር ተጋብቶ ዝግጅት ሲደረግ
አንዱ ክርስቲያን ተነስቶ ነብዩን ሶለሏሁአለይሂወሰለም መሳደብ ጀመረ

ያኔ ታስሮ የነበረው ውሻ ዘሎ ወጣበት
ከዛ በግድ ገልግለው አስጣሉት እንዲህም አሉት
"ነብዩን በመሳደብህ እኮ ነው የነከሰህ"
እሱም አይደለም ተቆጥቸ ስላየሁት ነው አለ  ዉሻው ምንም አላለውም

ትንሽ ቆይቶ ነብያችንን መሳደብ ሲጀምር ዘሎ አንገቱን ቦጭቆ ገደለው
ይህን ክስተት ያዩ 40 ሺህ ካፊሮች እስልምናን ተቀበሉ
ኢብኑ ሀጀር  "ዱረሩል ካሚና" ኪታብ ዘገቡት https://t.me/mushitaq_tube
83 views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 08:06:47 ድብቁ የሙስሊሞች የመጀመሪያ ንጉስ?

የሚገርመው ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም መካ/መዲና እያስተማሩ 1 ሰው ያላያቸው  በሩቅ የተቀመጠ ሰው ሲሰልም

ያያቸው ያወቃቸው ያገራቸው ሰው ደግሞ ከፍሮ ሳያያቸው የሰለመውን ሙስሊም ሊዘይር መጣ
የመጣበትም ጉዳይ ይህንን ታማኝ ነበይ ሊዋጋ ነበር
ነገር ግን ነብያችንን ሳያይ በሰለመው ሰው እጅ ሰልሞ እስልምናው አምሮ "ኢስከንድርያ" የተባለችን ከተማ ተዋግቶ የሙስሊሞች ያደረገ ጀግና ሆነ

ያ ነብይ ያልነውማ ነብያችን ሙሀመድነበሩ

ሳያያቸው የሰለመው አስሀመቱ ኢብኑ አብጀር አልነጃሺ

አይቷቸው ሳይሰልም በነጃሺ የሰለመው ደግሞ
  አምር ኢብኑል አስ https://t.me/mushitaq_tube
35 views05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 10:54:50
ሞሶሎኒ ኡመር አልሙክታርን ገደላቸው ረሂመሁሏህ ለሊቪያ ለእስልምና የለፉ ታላቅ ሰው በክብር ነበር ሞታቸው
አሏህ ሞሶሎኒን ዘቅዝቆ ገደለው
በሰው ክፋት ስትመኝ ባንተ የማይመጣ አይምሰልህ
80 views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 20:58:56
ይህ ውሀ ምን ይመስልሀል
ማኡ ዘምዘም ነው ከነብዩሏህ ኢብራሂም ዘመን አንስቶ እስካሁን ያልተቋረጠ ባለ በረካ ውሀ
አሏህ ይወፍቀን
ሀዲስ "ዘምዘም ውሀ ለጠጡለት ሀጃ አውጭ ነው"
https://t.me/mushitaq_tube
81 views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 20:07:14 ነብያችን  ﷺ በቤታቸው እሳት ሳይነድ (ምግብ ሳይበስል) ቀናት
ያልፍ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜያት እንደተራቡ ወደ መኝታቸው ተጉዘዋል ፡፡ አንድ ቀን
ኡመር  ወደ ረሱል ( ﷺ ) ቤት መጡ፡፡ ወደ ውስጥ ሲገቡም ነብዩ
ከቴምር ቅጠል ከተሰራ ፍራሽ ላይ ተኝተው ነበር፡፡ ደረቆቹ የቅጠል ጠርዞች በውድ የነብያችን ﷺ ሰውነት ላይ ሰንበሮችን አውጥተዋል ፡፡ በቤት ውስጥ ፈፅሞ አንድም ነገር የለም፡፡ በዚህ ወቅት ታድያ መላው አረቢያ በነብያችን ( ﷺ ) አስተዳደር ስር ነበረች፡፡ ኡመር እጅግ
ደነገጡ፡፡ እምባቸውንም ማቆም አልቻሉም፡፡ ነብያችን ( ﷺ ) "ኡመር ሆይ! ለምን ታለቅሳለህ?” ሲለ ጠየቁት፡፡ ኡመርም  እንዲህ ሲሉ መለሡ፡- "
እንዴት አላለቅስ የአላህ መልዕክተኛ! የሩምና የፉርሺያ ንጉሶች በምቾት ሲንደላቀቁ የአላህ መልዕክተኛ ከቴምር ዛፍ ቅጠል የተሰራ ደረቅ ፍራሽ ላይ ይተኛል !” ነብያችን ﷺ እንዲህ
አሉት ፡- "ኡምር ሆይ! ቄሳርና የፋርስ ንጉስ በዚህች አለም ይደሰቱ፤ ለኛ ግን የቀጣዩ አለም ደስታ በቂያችን ነው፡፡!" ቀጥለውም፡- "ይህ አለም ለኔ ከቶ ምን
ያደርግለኛል ! የኔና የዚህች አለም ግንኙነት እንደ መንገደኛ ነው፡፡ ከዛፍ
ጥላ ስር አረፍ ብሎ ሲነጋ መልሶ እንደሚጓዘው፡፡" ሰለላሁ አለይሂ ወሰልም ﷺ ﷺ
Joinnnnn
https://t.me/join https://t.me/Mushitaq_Tube
83 views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 21:09:18 ፈገግታ ሱና ነው እንዳነበብኩት ከልቤ ነው የሳኩት

ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም ጨዋታ ላይ የማይጎረብጡ ምቹ ሰው ናቸው!


አንድ እለት ከሰሃባዎቻቸው ጋር ተቀምጠው ተምር እየበሉ ጨዋታ ይዘዋል…… ከፊታቸው የተቀመጠ አንድ ሰሃባ ሊቀልዳቸው ፈልጎ ተምሩን ይበላና የተምሩን ፍሬ እሳቸው በልተው ካስቀመጡት የተምር ፍሬ ጋር ሳያዩት ያስቀምጠዋል… አሁንም ይበላና ፍሬውን ከሳቸው ፊት ይጨምረዋል
መጨረሻ ላይ "ያ ሩሱለላህ፣ ዛሬ ያለ ወትሮዎ ብዙ ተመገቡኮ" አላቸው……

እሳቸውም ዝቅ ብለው ከፊታቸው ያሉትን የተምር ፍሬ ሲመለከቱት በዛባቸው(ተከምሯል) ……

ሰውየው ወደተቀመጠበት ቦታ ሲመለከቱ ምንም የተምር ፍሬ የለም… ሁሉም ያለው ከሳቸው ፊት ነው……

ረሱልም ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም ነገሩ ፈገግ አሰኛቸውና እንዲህ አሉት…

«የኔ ይህን ሁሉ ተምር መብላት ብቻ ሳይሆን ያንተ ከነ ፍሬው መዋጥህም ይገርማል» :-)
      
          መልካም ቀን

                 صل الله عليه وسلم
               (ﷺ) (ﷺ) (ﷺ)

     ሼር ሼር ሼር

ተጨማሪ ኢስላማዊ እውቀቶችን ለማግኘት join ያድርጉ
https://t.me/Mushitaq_Tube
81 views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ