Get Mystery Box with random crypto!

#ታታር_ከየእጁጅና_መእጁጅ_በፊት_የመጡ_የእጁጅና_መእጁጆች                 ክፍል 5 ታታ | Mushitaq tube ሙሽታቅ ቲዩብ

#ታታር_ከየእጁጅና_መእጁጅ_በፊት_የመጡ_የእጁጅና_መእጁጆች
                ክፍል 5
ታታሮች መረውን ካወደሙ በኋላ ወደ ነይሳቡር አመሩ።
       *ነይሳቡር*
በከተማው ውስጥ በቂ የጦር ሀይል ቢኖርም የመረው አስደንጋጭ ዜና ልባቸውን በፍርሃት ስለሞላው ለታታር እጅ ሰጡ። የቺንግስ ካን ልጅ የከተማዋን ነዋሪዎች በሙሉ ወደ በረሃ ወጥተው ጭንቅላታቸው እንዲበጠስ አዘዘ። ሴቶችን ማረከ። ከተማዋን ለአስራ አምስት ቀናት ለገንዘብ ፍለጋ ሲሉ ቆዩባት። በዚህ መልኩ ነይሳቡርን በቀላሉ ቅሪት አድርገው ለቀቋት።

           *በሀራት*
ተረኛዋ የኹራሳን ከተማ ናት።  ሰሜን ምእራብ አፍጋኒስታን የምትገኝ ከተማ ስትሆን በጣም ሰፊና ብርቱ ከተማ ብትሆንም የመረውና የነይሳቡር እጣ ፋንታ እልቀረላትም። ወንዶቿ ተገደሉ፤ ሴቶቿ ተማረኩ።
*"መሊክ ኻን"* የተባለው ንጉሷ ግን ከተወሰኑ ወታደሮች ጋር ወደ *ገዝና* ከተማ ሸሽቶ ማምለጥ ቻለ። ኹራሳንና በሀራት አከተሙ።

ቀጣይ እቅዳቸው የኸዋርዚም ዋና ከተማን(ኸዋሪዝም ትባላለች) delete ማድረግ ነው። በጀይሁን ወንዝ ፊት ለፊት ነች። ባላት ትልቅ ወሳኝነት ቺንግስ ካን ብዙውንና ታላቁን ሰራዊት ነበር የላከው። ይህ ሰራዊት ኸዋርዚምን ለ5_ ወር ከቦ ቢቆይም መክፈት ስላልቻለ በተጨማሪ ሀይል ጥቃታቸውን አጠናክረው ምሽጉን ደርመሰው መግባት ቻሉ። አስፈሪ ፍልሚያ ተካሄደ። በመጨረሻም ድል ለታታሮች አመዘነ። ሙስሊሞች እየሸሹ በየጉድጓዱ መደበቅ ጀመሩ።

ታታሮች መቆጣጠር ሲሳናቸው  እጅግ ዘግናኝ እርምጃ ወሰዱ።

ይኸውም የጀይሁንን ወንዝ ግድብ በማፈረስ ከተማዋን በጎርፍ አጥለቀለቋት።ቤቶች ተደረመሱ። ከኸዋርዚም ሰዎች አንድም አልተረፈም። ከሰይፍ የዳነ ሁሉ በጎርፉ አለቀ። ኸዋርዚም ከከተማነት ወደ ባህርነት በአንድ ፀሀይ ተሸጋገረች። ከዚያ በፊት ከተማዋን የሚያውቃት አሁን የት አካባቢ እንደነበረች ማወቅ አይችልም። ያሳዝናል ኸዋርዚም ስላችሁ ያሁን ሰዎች አታውቋት ይሆናል ምክንያቱም ከካርታ ላይ ሰረዟታ!!።
             *ገዝና*
ታታሮች ቀጣይ እርምጃቸው የኸዋርዚምን ደቡባዊ ግዛት መዝመት ነው። ደቡብ ኸዋርዚም የሙሐመድ ኢብኑ ኸዋርዚም ሻህ ልጅ ጀላሉዲን ነው የሚያስተዳድረው። ጀላሉዲን የታታሮች ሙሉ ዜና ደርሶታል። የኹራሳንና የኸዋርዚም መውደቅ የአባቱ ሞት ደርሶታል። ቀሪው እሱ መሆኑ ኃላፊነቱን አክብዶበታል። ቢሆንም ግን ሰራዊት እያሰባሰበ ነው። የጀላሉዲን መናገሻ ከተማው ገዝና የምትባል ከተማ ናት (ከካቡል እቅራቢያ በተራሮች የተከበበች አፍጋኒስታናዊ ከተማ ነች)።

ጀላሉዲን ትልቅ ሰራዊት ማዘጋጀት ቻለ። በቅርቡ የሸሸው የሀራቱ አሚር *መሊክ ኻን* ከቀሪው ሰራዊቱ ጋር በመሆን ከጀላሉዲን ጎን ታታርን ለመፋለም ተዘጋጅቷል። ከቱርክ ሙስሊም መሪዎች አንዱ የሆነው *ሰይፈዲን በغግራቅ* ሰላሳ ሺህ ወታደር አስከትሎ ጀላሉዲንን ተቀላቀለ።

ሰይፈዲን ጀግና፣ በሳልና ብልህ መሪ ነው። ወታደሮቹም እንዲሁ። ጀላሉዲን ሰራዊቱን አስከትሎ ከገዝና ከተማ ወጣ ብሎ በለቅ የተባለ በተራራ የታጠረ ቦታ ላይ ሰፍሮ ታታርን መጠበቅ ጀመረ። ታታሮች ደረሱ። ፍልሚያው ተጀመረ፤ ሙስሊሞች ተሟሙተው ተጋደሉ። ከኸዋሪዝም ያላቸው ቀሪ ሀገር ይሄ ነው።

የጀላሉዲን አመራርና የሰይፈዲን በግራቅ ወታደሮች ጀግንነት የሙስሊሞችን መንፈስ አደሰ። ፍልሚያው 3 ቀን ዘለቀ። ታታሮችን ውሀ በላቸው። የአሏህ እርዳታ መጣ። *ሙስሊሞች ድል አደረጉ* ። ታታሮች እግሬ አውጪኝ ብለው ወደ ቺንግስ ካን ፈረጠጡ። አላሁ አክበር! አሏሁ አክበር! አሏሁ አክበር!!!

  ሽሽት የማያውቁት ታታሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ተሸነፉ። አዎ! ሙስሊሞች በአንድነት ሲፋለሙ የአላህ እገዛም ተጨመረ።
ጀላሉዲን ቺንግስ ካንን ለዳግም ፍልሚያ ጋበዘው። ቺንግስ ካን በፍርሀት በጣም ግዙፍ ሰራዊት በልጁ አሚርነት ላከ። ከመጀመሪያው የከበደ ፍልሚያ  ተካሄደ። ሱብሀነሏህ አሁንም ድሉ የሙስሊሞች ሆነ።


  ከ10,000+ በላይ ሙስሊም ምርኮኞችን ከታታሮች ነፃ አወጡ። በጣም ብዙ ገንዘብ ማረኩ። ይህን ታላቅ ድል አጣጥመው ሳይጨርሱ ትልቅ አደጋ አንዣበበ።
ምንድን ነው???
ክፍል
ይቀጥላል.....