Get Mystery Box with random crypto!

MuhammedSirage M/Nur TextPosts

የቴሌግራም ቻናል አርማ msiragetext — MuhammedSirage M/Nur TextPosts M
የቴሌግራም ቻናል አርማ msiragetext — MuhammedSirage M/Nur TextPosts
የሰርጥ አድራሻ: @msiragetext
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 984
የሰርጥ መግለጫ

ለግጥሞች እና ለፅሁፎች የተዘጋጀ ቻናል

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-03-27 13:11:11 ረመዳንን አስመልክቶ አጭር ምክር

ኢኽስላስ ፣ ነብዩን መከተል

t.me/Muhammedsirage

የድምፅ ፋይሎችን ለማግኘት
t.me/Muhammedsiragecom
781 viewsكوني زوجة صالحة تقية, 10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 18:24:44 ማረኝ ጌታዬ ሆይ !

ያምና የካቻምና ክምሩን ወንጀሌ
የዛሬን የትላንት የከፋው አመሌ
ሳስታውስ በዛብኝ በረታ ለቀልቤ
አልዘለቅ አለኝ ቆጥሬና አስቤ
የጄን ወንጀል ሳስብ ምላሴ እየመጣ
ያይኔ ሲያቃጥለኝ ደግሞ የግሬ ጣጣ
እጅግ ያስፈራኛል ህልፈቴ እንዳይመጣ
በድፍርስ ተግባሬ በጨቀየ ስራ
ቀብሬን ብጎበኘው ደርሶ የኔ ተራ
ምን ይሆን እጣዬ
የቀብሩ ድርሻዬ
ብዬ ሳሰላስል እጅጉን ጨነቀኝ
ክምሩ ወንጀሌ አሳሞ አማቀቀኝ
አዛኙ ጌታዬ በዝነትህ ጠብቀኝ
አምናለሁ ጌታዬ ባርያህ ነኝ ርካሹ
ስራው ያላማረ ደም ስጋው ብልሹ
…… ባመጽ የቆሸሹ!!
ባበዛሁት ወንጀል ቀልቤ የቆሸሸ
አልጸዳም እያለኝ እየጠቀረሸ
ነኝና ጌታዬ ………
በሰፊው እዝነትህ አውጣኝ ከወንጀሌ
ቀብሩን ሳልገናኝ ሳይነዳኝ አጀሌ
አንተንም ስገናኝ ማረኝ የኔ ጌታ
ተስፋ አይቆረጥም በራሕማን ችሮታ
አቋድሰኝ በዝነትህ ከጀነት ገበታ

በሙሓመድሲራጅ አቡ ዒምራን

https://t.me/Muhammedsirage
1.5K viewsMuhammedSirage MuhammedNoor, 15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 18:12:08 የኔዋ መኪና !!!

መዝነቡን ጀመረ ደርሶ ማካፋቱ
ይከባብድ ይዟል ወጥቶ መግባቱ
እንግዲህ ከገባ የዝናብ ወራቱ
ደሞ እነደ ካቻምና እንዳምና ትናንቱ
ዣንጥላየን ልግዛ የኔዋን መኪና
እሷኑ ላሽከርክር በሰፊው ጎዳና!!


https://t.me/Muhammedsirage
543 viewsMuhammedSirage MuhammedNoor, 15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-24 20:25:35 የሁለቱ ዓሊሞች ንግግር በኢኽዋን አንጃ ላይ
~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~
ለኢኽዋን መንገድና ስልት የሚሟገቱ ግለሰቦች የዚህን አንጃ ክፋትና መጤነት የሚገልፁ የዑለሞችን ትችቶች በምንጠቅስ ግዜ የተለያዩ መከላከያዎችን ያቀርባሉ። አንዳንዶች በኢኽዋን ላይ የሚሰጡ ትችቶችን ከሃይማኖታዊ ይዞታ አውጥተው ፖለቲካዊ ቅርፅን ማልበስ ይሻሉ ። ለዚህም ነው "በኢኽዋኖች ላይ የተከፈተው ዘመቻ የተጠነሰሰው በባህረ ሰላጤው ጦርነት ማግስት ነው" ብለው አንዳንዶች የሚቀጥፉት።
የባህረ ሰላጤው ጦርነት የተከሰተው ከ20 አመታት በፊት ነው። ነገር ግን ዑለሞች ከተጠቀሰው ጦርነት በፊት የአንጃውን ጥመት ሲያጋልጡ ኖረዋል!!

ታላቁ ግብፃዊ የሐዲስ ሊቅ አሕመድ ሻኪር ኢኽዋኖችን በተመለከተ ከ60 አመታት በፊት እንዲህ ይላሉ ። ልብ ይበሉ ከ60 አመታት በፊት ነው!!! ልብ ይበሉ! በርካታ ዑለሞች በመልካም የመሰከሩለት ታላቅ ዓሊም የሰጠው ምስክርነት ነው! !! የታማኝ ንግግር ነው

"حركة الشيخ حسن البنا وإخوانه المسلمين الذين قلبوا الدعوة الإسلامية إلى دعوة إجرامية هدامة، ينفق عليها الشيوعيون واليهود كما نعلم ذلك علم اليقين "ا

"ኢስላማዊ ጥሪን /ዳዕዋን/ ወደ እኩይ እና አጥፊ ሰበካ የቀየረው የሸይኽ ሐሰን አልበና እና የሙስሊም ወንድሞቹ እንቅስቃሴ ሶሻሊስቶችና አይሁዶች በገንዘብ ይደግፉታል— ይህንን በእርግጠኝነት እንደምናውቀው!!"

የመዲናው ታላቅ ሸይኽ ሱለይማን አርሩሓይሊ የተጠቀሰውን የሸይኽ አህመድ ሻኪርን ንግግር ከጠቀሱ በኋላ እንዲህ ይላሉ:–

وإلى اليوم ينفق عليهم لأن هذه الجماعات تحقق أهداف أعداء الدين في الأمة

"ዛሬም ድረስ በነሱ ላይ ወጪ ይድደረጋል (በገንዘብ ይረዷቸዋል)። እንዚህ አንጃዎች የዚህ ሃይማኖት /የኢስላም/ ጠላቶችን አላማ በህዝቡ ላይ የሚያረጋግጡ /የሚያስፈፅሙ/ ናቸውና!!"
t.me/Muhammedsirage
571 viewsMuhammedSirage MuhammedNoor, 17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 21:44:56
አሕባሾች እና መሰሎቻቸው አላህ ከዐርሽ በላይ ነው የሚለው እምነት በኢብኑ ተይሚያ ዳብሮ በሙሀመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ የተሰራጨ የ ወሃቢያ እምነት አድርገው እንደሚያስቡት ህፃን አዋቂው ዘንድ ይታወቃል።በዚህ ስራዬ ውስጥ ለነዚህ ሀሰተኞች ስበብ ላለመስጠት የሙሀመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብን ቀርቶ የኢብኑ ተይሚያ እና የተማሪዎቻቸውን ንግግሮችም አላካተትኩም ።
ከቁርኣን እና ከሐዲስ ባለፈ ቀዳሚ ትኩረቴ ያደረኩት የአሽዐሪያ አንጃ ከመፈጠሩ በፊት ባለፊት እስከ 300 ሂ . ድረስ በነበሩ ዑለማዎች ላይ ነው ።
ከዚህ ዘመን በኋላ በመጡ ስመ ገናና ዑለማዎች ሊሞግቱን ለሚሹ ማርከሻ ይሆን ዘንድ ያክል ብቻ ከ300 ሂ . ጀምሬ እስከ 7ኛው ክ/ዘመን 2ኛ አጋማሽ ድረስ ከለፉ ዑለማዎች እያለፍኩ አጣቅሻለሁ።

"ከዐርሹ በላይ" ከሚለው መፅሀፍ መግቢያ የተወሰደ
https://t.me/fejir_tube

t.me/Menhaj_Salafiya
370 viewsكوني زوجة صالحة تقية, 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ