Get Mystery Box with random crypto!

የሁለቱ ዓሊሞች ንግግር በኢኽዋን አንጃ ላይ ~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•° | MuhammedSirage M/Nur TextPosts

የሁለቱ ዓሊሞች ንግግር በኢኽዋን አንጃ ላይ
~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~
ለኢኽዋን መንገድና ስልት የሚሟገቱ ግለሰቦች የዚህን አንጃ ክፋትና መጤነት የሚገልፁ የዑለሞችን ትችቶች በምንጠቅስ ግዜ የተለያዩ መከላከያዎችን ያቀርባሉ። አንዳንዶች በኢኽዋን ላይ የሚሰጡ ትችቶችን ከሃይማኖታዊ ይዞታ አውጥተው ፖለቲካዊ ቅርፅን ማልበስ ይሻሉ ። ለዚህም ነው "በኢኽዋኖች ላይ የተከፈተው ዘመቻ የተጠነሰሰው በባህረ ሰላጤው ጦርነት ማግስት ነው" ብለው አንዳንዶች የሚቀጥፉት።
የባህረ ሰላጤው ጦርነት የተከሰተው ከ20 አመታት በፊት ነው። ነገር ግን ዑለሞች ከተጠቀሰው ጦርነት በፊት የአንጃውን ጥመት ሲያጋልጡ ኖረዋል!!

ታላቁ ግብፃዊ የሐዲስ ሊቅ አሕመድ ሻኪር ኢኽዋኖችን በተመለከተ ከ60 አመታት በፊት እንዲህ ይላሉ ። ልብ ይበሉ ከ60 አመታት በፊት ነው!!! ልብ ይበሉ! በርካታ ዑለሞች በመልካም የመሰከሩለት ታላቅ ዓሊም የሰጠው ምስክርነት ነው! !! የታማኝ ንግግር ነው

"حركة الشيخ حسن البنا وإخوانه المسلمين الذين قلبوا الدعوة الإسلامية إلى دعوة إجرامية هدامة، ينفق عليها الشيوعيون واليهود كما نعلم ذلك علم اليقين "ا

"ኢስላማዊ ጥሪን /ዳዕዋን/ ወደ እኩይ እና አጥፊ ሰበካ የቀየረው የሸይኽ ሐሰን አልበና እና የሙስሊም ወንድሞቹ እንቅስቃሴ ሶሻሊስቶችና አይሁዶች በገንዘብ ይደግፉታል— ይህንን በእርግጠኝነት እንደምናውቀው!!"

የመዲናው ታላቅ ሸይኽ ሱለይማን አርሩሓይሊ የተጠቀሰውን የሸይኽ አህመድ ሻኪርን ንግግር ከጠቀሱ በኋላ እንዲህ ይላሉ:–

وإلى اليوم ينفق عليهم لأن هذه الجماعات تحقق أهداف أعداء الدين في الأمة

"ዛሬም ድረስ በነሱ ላይ ወጪ ይድደረጋል (በገንዘብ ይረዷቸዋል)። እንዚህ አንጃዎች የዚህ ሃይማኖት /የኢስላም/ ጠላቶችን አላማ በህዝቡ ላይ የሚያረጋግጡ /የሚያስፈፅሙ/ ናቸውና!!"
t.me/Muhammedsirage