Get Mystery Box with random crypto!

ማረኝ ጌታዬ ሆይ ! ያምና የካቻምና ክምሩን ወንጀሌ የዛሬን የትላንት የከፋው አመሌ ሳስታውስ በዛ | MuhammedSirage M/Nur TextPosts

ማረኝ ጌታዬ ሆይ !

ያምና የካቻምና ክምሩን ወንጀሌ
የዛሬን የትላንት የከፋው አመሌ
ሳስታውስ በዛብኝ በረታ ለቀልቤ
አልዘለቅ አለኝ ቆጥሬና አስቤ
የጄን ወንጀል ሳስብ ምላሴ እየመጣ
ያይኔ ሲያቃጥለኝ ደግሞ የግሬ ጣጣ
እጅግ ያስፈራኛል ህልፈቴ እንዳይመጣ
በድፍርስ ተግባሬ በጨቀየ ስራ
ቀብሬን ብጎበኘው ደርሶ የኔ ተራ
ምን ይሆን እጣዬ
የቀብሩ ድርሻዬ
ብዬ ሳሰላስል እጅጉን ጨነቀኝ
ክምሩ ወንጀሌ አሳሞ አማቀቀኝ
አዛኙ ጌታዬ በዝነትህ ጠብቀኝ
አምናለሁ ጌታዬ ባርያህ ነኝ ርካሹ
ስራው ያላማረ ደም ስጋው ብልሹ
…… ባመጽ የቆሸሹ!!
ባበዛሁት ወንጀል ቀልቤ የቆሸሸ
አልጸዳም እያለኝ እየጠቀረሸ
ነኝና ጌታዬ ………
በሰፊው እዝነትህ አውጣኝ ከወንጀሌ
ቀብሩን ሳልገናኝ ሳይነዳኝ አጀሌ
አንተንም ስገናኝ ማረኝ የኔ ጌታ
ተስፋ አይቆረጥም በራሕማን ችሮታ
አቋድሰኝ በዝነትህ ከጀነት ገበታ

በሙሓመድሲራጅ አቡ ዒምራን

https://t.me/Muhammedsirage