Get Mystery Box with random crypto!

www.metshafkdus@gmail.com📚

የቴሌግራም ቻናል አርማ metshafkdus — www.metshafkdus@gmail.com📚 W
የቴሌግራም ቻናል አርማ metshafkdus — www.metshafkdus@gmail.com📚
የሰርጥ አድራሻ: @metshafkdus
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 228
የሰርጥ መግለጫ

“የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።”ኢያሱ 1፥8
ይህ ቻናል ሰዎችን ሁሉ የያህዌህን ቅዱስ ቃሉን ወይም መጽሐፍ ቅዱስን ጊዜ ሰጥተው እንድያነቡና ትኩረት እንዲሰጡት የዓለምን ፈተና መሸነፋቸው የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል እንዲታጠቁ የሚያሳስብ ቻናል ነው @Metshafkdus

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-02-19 20:11:00 ከምንጩ እንቅዳ!
=======================
~ <<ነገርን ከሥሩ ውኃን ከጥሩ>> እንደሚባለው የእግዚአብሔር ቃል ከመግቢያ እስከ ማጠቃለያ፣ ከአርእስት እስከ ኅዳግ ሲነበብ አሳቡ ይገኛል፣ ሲተረጐም ምሥጢሩ ይበራል፣ ሲብራራ ስፋቱ ይለካል፣ ሲተነተን ተመሥጦው ከፍ ይላል፡፡

~ የእግዚአብሔር ቃል፡-
-> የሚነበብ
-> የሚጠና
-> የሚተነተንና
-> ከሕይወት ጋር የሚዛመድ መስተዋት ነው፡፡

~ የእግዚአብሔር ቃል ዕለታዊ ዜና አይደለም፣ ዜና ከዕለቱ ሲያልፍ በማግሥቱ የወሬ ቋንጣ ይሆናል፡፡

~ የእግዚአብሔር ቃል ግን በዘመናት አዲስ፣ ሕይወትን የሚሰጥ መንፈሳዊ እንጀራ ነው፡፡

~ የእግዚአብሔር ቃል ማስታወቂያ አይደለም፤ ማስታወቂያ በቅጽበተ ዓይን ዓይተነው እናልፈዋለን፡፡ ከማስታወቂዎቹ የማይመለከተን ይበዛል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ግን በአድራሻችን የተላከ መልእክታችን ነው፡፡

~ ስለዚህ ሁላችንን ይመለከተናል፡፡ አንድን ፅሁፍ አንብበን ምን ለማለት እንደ አልገባ ቢለን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ፅሁፉን ከፃፈው የበለጠ የሚተነትንልን ማንም የለም፡፡

~ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቃል ከባለቤቱ ከመንፈስ ቅዱስ መረዳት ከምንጩ እንደ መቅዳት ነው፡፡ ስለዚህ ቃሉን ለመረዳት ጸሎትና ጽሞና ያስፈልጋል፡፡ ያልደፈረሰውን፣ ያልተበከለውን የሕይወት ውኃ ከምንጩ ከመንፈስ ቅዱስ፣ ከምንጩ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንድንረዳ በጸሎትና በተዘጋጀ ልቡና መቅረብ ያስፈልገናል፡፡

-->> ልብ አድርጉ፡- እግዚአብሔር ቃሉን የሰጠው ለሊቃውንት ሳይሆን ለልጆቹ ነው፡፡ ስለዚህ ቃሉ እኔን አይገባኝም ማለት የለብንም፡፡ ካልደፈረሰው፣ ካልተበረዘው ተቀድቶ ከማያልቀው ህያው ከሆነው ምንጭ ከመንፈስ ቅዱስ፣ መፅሐፍ ቅዱስ እንቅዳ።ብሩክ ሁኑልኝ!

< ክብር እስከ ሞት ድረስ ለወደደን::
261 viewsNathan ሰው ብቻ እንደተፈጠረው አይደለም, edited  17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-04 10:35:57 የመቅረዜ ብርሃን
የመቅረዜ ብርሃን የሕይወቴ
ጸዳልህ ፈሶልኝ በርቷል ፊቴ
ኢየሱስ ትከሻህ ተሸከመኝ
እኖራለሁ መዳፍህ እያከመኝ

በፍቅር የሾህ አክሊል የደፋኸው
በጅራፍ መቀነት የታጠከው
ደምህ ተፈተለ ልታለብሰኝ
ከባርነቴ ቤት ልትመልሰኝ
ስምህን ጽፈሃል በግንባሬ
በደምህ ተተክሎ ጸንቷል ቅጥሬ
የነፍሴ ዋስትና ነፃነቴ
አንተ ነህ ክርስቶስ ሽልማቴ

ከፍ አድርገው ሰቅለውህ በተራራ
ወጣሁ ከሸለቆ በአንተ ስራ
እምነቴ ድፍረት አለኝ ጽኑ ተስፉ
በማዕበል በወጀብ የማይገፉ
አጥብቄ ልያዝህ ምሶሶዬ
ተደግፈህ አልፋል ያ ልቅሶዬ
በአንዱ በአንተ ወድቋል እልፍ ሃዘኔ
ለዚህ ነው በስምህ መታመኔ

የልቤ ሰማዩ አይጨልምም
የነፍሴ ጀንበሯ ጠልቃ አትቀርም
አብርተህልኛል ውብ ኮከቤ
ዘመርኩኝ በብርሃን ተከብቤ
አዲስ ዘመን መጣ አዲስ ዓመት
የተወደደችው የአንተ ስዓት
የመዳኔን ወንጌል ሰብከህኛል
የማርያም ልጅ ከሞት ዋጅተህኛል

በብላቴናነት የጀመርኩት
ረጅም ጉዞዬን በአንተ ጣልኩት
ይሰማኛል ራሴን ስትዳስሰኝ
ፀጋህን ደራርበህ ስታለብሰኝ
ላግንህ ላክብርህ በዘመኔ
መብራቴን ሞልተሃል ዜማ ቅኔ
ሳትንቅ ከሰጠኸኝ ዕድል ፈንታ
ልስበክህ በእንባዬ የኔ ጌታ
├───────────
│ለእርሱ ክብርና ኃይል
│እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤
│አሜን።
│ ❏ 1ኛ ጴጥ 5፥11
├───────────
├⊙ዘማሪት ዕንቁስላሴ ጎሳ
├───────────
├@Metshafkd
217 viewsNathan ሰው ብቻ እንደተፈጠረው አይደለም, 07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-24 21:30:02 አገንሃለሁ ዘመኔን ሁሉ
ንገስ እላለሁ ዘመኔን ሙሉ
ሰው ሆነህልኝ ሰው አርገኸኛል
ወዳጄ ፍቅርህ መች ይረሳኛል

አስታዋሽ የለኝ ካላንተ ጌታ
ነፍሱን ሰውቶ ነፍሴን የፈታ
ንጹህ ደምህ ነው መማጸኛዬ
በድል ያሮጠኝ ሸክሜን ጥዬ

ከሰማያትም ሰማያት በላይ
እነጠቃለሁ ክብርህን እንዳይ
በነበልባሉ ታጥሯል ድንበርህ
አይደፈርም ጌታዬ ቅጥርህ

ዜማ ዜማ ነው የልቤ ቃሉ
ሳሸበሽብ ነው የክንዴ ድሉ
ደብሩ አይመቸኝ ካልዘመርኩልህ
አይነጋም መሽቶ ክበር ሳልልህ

ለተግዳሮቴ ቅኔን ባነሳ
ያንን የአርቡን ፍቅር ባወሳ
ያጉረመርማል ዘንዶው በከንቱ
ሕይወት ላይዘራ ታውጇል ሞቱ
├───────────
│እንዲህ በሕይወቴ ዘመን
│አመሰግንሃለሁ፥ በአንተም
│ስም እጆቼን አነሣለሁ።
│ ❏ መዝ 63፥4
├───────────
├⊙ዘማሪት ቃልኪዳን መኮንን
───────────
191 viewsNathan ሰው ብቻ እንደተፈጠረው አይደለም, 18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-22 21:09:58 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

#እውነተኛ_እምነት

«የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው» (1ኛጢሞ.1።5)።

በእምነታችን ወይም በጸሎታችን ህጻን ልንሆን አይገባንም፣ ነገር ግን እኛ መሆን የሚያስፈልገን እንደ ልጆች መሆን ያስፈልገናል። ጌታ ከእርሱ ጋር ያለን ግንኙነት ውስብስብ እንዲሆን አይፈልግም። እርሱ እውነተኛ ልባችንን ይመረምራል፣ ምክንያቱም እርሱ የልብ አምላክ ነውና። እርሱ በስሜት የሆነ ጸሎት ሳይሆን በእምነት የሆነውን ጸሎት ከእኛ ይፈልጋል። ነገር ግን መንሳዊ ኃይል በማይታየው መንፈሳዊ ዓለም ላይ ተጸዕኖ ያደርጋልና። እግዚአብሔር የሥርዓት አምላክ ነው እንጂ የመመሪያና የኃይማኖታዊ ሥርዓት አምላክ አይደለም። እርሱ የረጅም ጊዜ ጸሎት እንድንሞክር ሰዓት እንድጨርስ፣ በሥርዓት የተሞላ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት የሌለበት የረጅም ሰዓትና የተወሰነ ኃይማኖታዊ ገጽታ ያለውን ጸሎት አይፈልግም። ይህ ዓይነት የጸሎት ልምምድ ወደ ወግ አጥባቂ ህጋዊነትና ከእግዚአብሔር ጋር ካለን ህብረት የሚገኘውን ህይወት ይወስድብናል። «ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል» (2ኛቆሮ.3።6)።

እኛ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ስንከተል፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት በህይወት የተሞላ ይሆናል። ብዙ ሰዎች እንደሚያደርጉት የጸሎት ሰዓትን ለማሟላት የእጅ ሰዓታችንን አሁንም አሁንም መመልከት አያስፈልገንም። እግዚአብሔርን ለመነጋገርና ለመስማት ስንቀርብ እንደ ግዴታና እንደ ሥጋችን ሥራ ስናደርግና ስንቀርብ፣ የአምስት ደቂቃ ጸሎት እንደ ሰዓታት ይቆጠርብናል። ነገር ግን ጸሎታችን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የተሞላ ሲሆን ለሰዓታት የምንጸልየው ጸሎት አምስት ደቂቃ የጸለይን አይመስለንም። እኔ የምፈልገው ውስጤ ሙሉ ሆኖ ጥግብ እስኪልና እስኪረካ ድረስ መጸለይና ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድረግ እወዳለሁ። ከእግዚአብሔር ጋር ያለህ ህብረት የተመቸህና ደስተኛ እንዲያደርግ ለማድረግ ሞክር፣ እርሱ ደግሞ ላንተ የተሰጠህ ደመወዝህ (ዋጋህ) ነው።

ላንተ የሆነው የዛሬው የእግዚአብሔር ቃል፡ እንደ ልጅነት ለመሆን ጥረት አድርግ አንጂ ህጻን አትሁን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
165 viewsNathan ሰው ብቻ እንደተፈጠረው አይደለም, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 20:54:07 * ቆይ ግን ከየትኛው ዓለም ነህ/ሽ/ኝ? *

> ዘንድሮ ሰይጣን በክርስቲያኑ ዘንድ ብዙ ያተረፈ ይመስለኛል! በተለይም በሶሻል ሚዲያውማ ጥሩ ተሳክቶለታል ያስብላል!

#ነገሩ ግር ብሎት "እንዴት?" ብሎ የሚጠይቅ ይኖርን?

> ነገሩስ ግልፅ ነው። ተደጋግሞ ቢነገረን አልሰማ አልን እንጂ! ሰይጣን ክርስቲያኑን በማይመለከተው የፓለቲካ መንደር ጠርቶ በማመስ፣ ከየትኛው ዓለም እንደሆነ ግራ አጋብቶታል!

#መፅሐፍ ቅዱስ ስለ ሶስት ዓለሞች ይናገራል

~ አንደኛው የቀደመው ዓለም የሚለው ሲሆን፣ ይህም ከአዳም እስከ ኖህ ያለ ዘመን ነበር(2ጴጥ፡2÷5)። እግዚአብሔርን በአሳባቸውም ሆነ በድርጊታቸው የበደሉት የዚያ ዘመነ ነዋሪዎች ከስምንት ሰው በቀር በሙሉ በውሃ ሰጥመው ጠፍተዋል(2ጴጥ፡3÷6)።

~ ሁለተኛው የአሁኑ ዓለም የተባለውና ከኖህ ጀምሮ የእኛን ዘመን ጨምሮ ከቤ/ን መነጠቅ በኋላ የሚመጡትን ሰባት የመከራ ዓመታትን የሚያጠቃልለው ነው።

> ይህ ዓለም ከቀድሞ ያልተለየና ምናልባትም የከፋ፣ በአጭሩ "ክፉ" የተባለ ነው(ገላ፡1÷4)። መጨረሻውም በክርስቶስ መምጣት በፍርድ የሚጠናቀቅ ነው (ራዕ፡16ና19)።

~ሶስተኛው የሚመጣው ዓለም የተባለው ሲሆን ይህም ክርስቶስ በምድር ሰላምን አምጥቶ የፅድቅ መንግስት የሚመሰርትበትና ከቤተክርስቲያን ጋር የሚነግስበት፣ በምድር ያሉትም የሚባረኩበት ወቅት ነው(ዕብ፡2÷5፣ሮሜ፡14÷17)።

#ታዲያ ይኽ እውነት በመፅሐፍ ቅዱስ ተቀምጦልን ሳለ፣ በዚህን ወቅት እንደ ክርስቲያን ፓለቲካ ውስጥ ገብተን ስንፋጭ ማየት፣ በእውነት በእግዚአብሔር ፊት በንስዓ ልንወድቅበት የሚገባ ኃጢአት ነው።

> አውቃለሁ! እንደ ሰው ስሜት አለን! ጉዳቶች ሊያገኙን ይችላሉ። ከአፋችንም የሆነ ነገር ሊወጣ ይችላል። ነገር ግን ፓለቲካውን ቁርስ፣ ምሳና እራት ስናደርገው፣ አልፎም የሶሻል ሚዲያው ፓስትና ክርክር ቋሚ ደንበኛ ስንሆን ምን ማለት ነው? እረ ጎራ ይዞም መፏከት ሁሉ እያየን ነው!

#ቆይ ከመፅሐፉ ይልቅ አዋቂ ነንን? ወይስ ሳይታወቀን ቃሉ አልፎበታል እያልን ነው? አልያስ ለእንደዚህ አይነት ጉዳይ ቃሉ ምሪት የለውም?

> መንግስትን በተመለከተ "ሀ" እና "ለ" ሳንልን ክርስቲያን የሆንን ሁሉ ሥልጣናቸው ከእግዚአብሔር መሆኑንን በማወቅና ለእነርሱ በመገዛት እንድንፀልይላቸው (ሮሜ፡13÷1-7፣ 1ጢሞ፡2÷1-4…) የመከረን እርሱ አይደለምን? ከዚህ ውጭ ምርጫ አለንን?

> እኛን ደግሞ በጠቅላላ ሲታይና ክርስቶስን ከገፋው ከአሁኑ ክፉ አለም አይደላችሁም(ዮሐ፡17÷14)፣ ክርስቶስ በሚነግስበት በሚመጣው ዓለም ትነግሳላችሁ አልተባልንምን(2ጢሞ፡2÷11)?

# እረ ጳውሎስ ቢኖር ለዴማስ "የአሁኑን ዓለም ወዶ" (2ጢሞ፡4÷10)፣ እንዳለው እኛን ደግሞ "በአሁኑ ዓለም ፓለቲካ ተጠምደው ይውላሉ" አይለንም ነበርን?

> "ከነገድ፣ ከቋንቋ፣ ከወገን፣ ከሕዝብም" ተዋጅተናል የምንልና ያንን የዘመርን ወገኖች ስፍራችን እንለይ፤ ከስሜት የወይን ጠጅ ስካር እንውጣ! እግዚአብሔር ምህረቱን ያብዛልን። አሜን
144 viewsNathan ሰው ብቻ እንደተፈጠረው አይደለም, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-17 15:03:54
ዓላማ
111 viewsNathan ሰው ብቻ እንደተፈጠረው አይደለም, 12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-14 22:21:26 [ Audio file : @Metshafkidus– እንደ ፍቃድህ ]
እንደፍቃድህ አውለኝ
በምህረትህ ጥላ ከልለኝ
በመልካሙ መስክ አሰማራኝ

እንደፍቃድህ
መውጣት መግባቴ መዋል ማደሬ
ላንተ ሰጠሁኝ እድሜ ዘመኔን
ከኔ የሆነው ከቶ ምን አለ
ሁሉም የአንተ ነው ታደርገዋለ

አንተ ነህና የእኔ አቅጣጫዬ
በሕይወት ቅደም ቅዱስ ጌታዬ

እንደፍቃድህ
ከሌለህበት አማኑ እረኛ
የኔው ይሆናል ወይኑ መናኛ
አንተ ስትገባ ከልቤ ቤት
ባዶ ጋን ሞላ በበረከት

እንደፍቃድህ
አይሞላልኝ ልቤ የሚያስበው
ጥብርያዶስን ነው እኔ ምመኘው
ስለዚህ አንተን አስቀድሚያለሁ
ኑሮዬን ሁሉ ይሁን ብያለሁ
├───────────
│አንተ የመድኃኒቴ አምላክ
│ነህና በእውነትህ ምራኝ፥
│አስተምረኝም፤ ቀኑን ሁሉ
│አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።
│ ❏ መዝ 25፥5
├───────────
├⊙ዘማሪ ዲያቆን መባ
├───────────
├ Metshafkidus
135 viewsNathan ሰው ብቻ እንደተፈጠረው አይደለም, 19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 12:22:31 ገና ክብረ በዓል ቀን እንዴት ተወሰነ?

ጄራርድ እና ፖትሪሷያ ዴልፊ "The Christmas Almanac " በተሰኘው መጽሃፋቸው አውሮፓውያኑ ታህሳስ ፪፭ እንዴት ቀስ በቀስ የሮማውያን ባህል እንደሆነ ሲተርኩ የሚከተለውን ብለዋል " ከበፊቱም የሳቱርሊና እና የአዲስ ጨረቃ ( Kalends) ክብረ በዓላት በክርስቲያኖች ዘንድ የተገለጡ ነበሩ ። ነገር ግን ታህሳስ ፪፭ን የእየሱስ ልደት ብሎ ማክበር የተጀመረው ከሮማውያን አህዛባዊ እምነት በመዋስ ነበር ።
" ሚትራ ( Mithra) የፋርሶች " የብርሃን አምላክ ሲሆን የተወለደውም በታህሳስ ፪፭ ቀን ከቋጥኝ ድንጋይ ነበር ተብሎ በተከታዮቹ ይታመናል ፤ ሮም እንግዳና አዳዲስ አማልክትን በማስገባትና በማምለክ የታወቀች አገር ስትሆን በ፫ኛው መቶ ክ/ዘ በ፪፯፬ ዓ.ም ፀረ ክርስትና የነበረው የሮማዊው ንጉስ ኦውሪኸን ( Aurehan) ይህንኑ የአምልኮ ቀን በአገሩ ላይ " የተሸነፈችው ፀሃይ ቀን " ( Dies inuicti Solis) በማለት በታህሳስ ፪፭ ቀን እንዲከበር አደረገ።
ሚትራ ፀሐይ የለበሰ ፣ ፀሐይ የተዋሃደ አምላካችን ነው ብለው ስለሚያምኑ ቀኑ በሚትራይዝም እምነት ተከታዮች ዘንድ እጅግ ታላቅ ነበር ። በኋላም ይህ ቀን በኦውሪኸን አስመጪነት በሮማውያን ዘንድ ታላቅ የሕዝብ በዓል መሆን ቻለ። ንጉስ ቁስጠንጢኖስ ክርስትናን እስከተቀበለበት ቀን ድረስም ሚትራየዝምን ይከተል እንደነበር ይታመናል። ምናልባትም ንጉስ ቁስጠንጢኖስ (Constantine) የአሮጌ እምነቱን በዓል ወደ አዲሱ እምነቱ እንዲገባ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ ሊሆን ይችላል ( The Christmas Almanac, 1979)
የፈረንጆቹ ታህሳስ ፪፭ ለመጀመሪያ ግዜ የገና ወይም የልደት በዓል ሆኖ የተከበረበትን እርግጠኛ ዓመት ማወቅ ባይቻልም የቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚጠቁመው ግን ጊዜው ፬ኛው መቶ ክ.ዘ ወይም ቤተክርስቲያን ከተመሰረተች ከ፫መቶ ዓመታት በኋላ መሆኑ እርግጥ ነው ። ይህ ደግሞ እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ እጅግ የዘገየ ግዜ ነበር። በቄሳሮች ግዛት ዋና ከተማ ሮምን ጨምሮ ጌታ ከሞተ ከ፫መቶ ዓመታት በኋላ የጌታ ልደት የሚባል በዓል በክርስቲያኖች ዘንድ ፈጽሞ አይታወቅም ነበር ። ይህ ደግሞ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ለዚህ ልምምድ ወይም ትምህርት መነሻ እንዳይደለች ያሳየናል። የገና ( Christmas) በዓል ከመነሻው ጀምሮ " ለቅዱሳን ፈጽሞ አንዴ ከተሰጠ ኃይማኖት ( እምነት) / ይሁዳ.3/ጋር ፈጽሞ ግንኙነት የለውም።
....
የገና ክብረ በዓል ቀን እንዴት ተወሰነ?
............ካለፈው የቀጠለ
በገና አከባበር ባህል ላይ የአውሮፓውያን ተጽዕኖ እና የገና ዛፍ

ከመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በተጨማሪም በምዕራቡ የነበሩት አህዛባዊ ክብረ በዓላትም ዛሬ ላለው የገና ባህላዊ አከባበር አስተዋፅኦ አድርገዋል ። ከእነዚህም አንዱ " የአስራ ሁለቱ ምሽቶች የቴውቶኒክ " በዓል በመባል የሚታወቅ ሲሆን የሚከበረውም በአውሮፓውያኑ ከታህሳስ ፪፭ እስከ ጥር ፮ ነበር ። ይህም ክብረ በዓል የሚደገሰው በተፈጥሮ ኃይሎች መካከል በሚደረገው ጦርነት ላይ በተመሰረተ ትረካ ላይ ሲሆን ይኸውም ሞትን ይወክላል በማለት " ታላቁ በረዶ" ( The ice giant ) መካከልና ሕይወትን ይወክላል ተብሎ በሚታሰበው " የፀሃይ አምላክ መካከል የሚካሄድ ጦርነት ነው።" የዊንተር ሶልስቲስ ( Winter Solistice) / ፀሃይ ከምድር ወገብ የምታልፍበት ወቅት / እስኪቃረብ ድረስ ታላቁ በረዶ / ሞት/ በሚያቀዘቅዘው ኃይሉ ሲያሸንፍ ይሰነብትና ከዚያ በኋላ ግን የፀሃይ አምላክ / ሕይወት/ ድል እየተቀዳጀ መምጣት ይጀምራል በማለት ያምኑ ነበር።
ክርስትና ወደ ሰሜን አውሮፓ በተስፋፋበት ግዜ በታህሳስ ወር ውስጥ የሚከበሩ ተመሳሳይ የሆኑ የፀሃይ መወለድ ክብረ በዓላት ገጥመውት ነበር። ለምሳሌ በስካንዲኒቪያን ሕዝቦች የሚከበር የዮሌ ክብረ በዓል ( Yule feast) ነበር ። ይህም በዓል በተከታታይ ለ፩፪ ቀናት የሚከበር ሲሆን በበዓልም ወቅት ሰዎች የፀሃይን ማሸነፍ ለማገዝና ለማበረታታት በታላቅ ሁኔታ እሳት ያቀጣጥሉና ያበሩ እንደነበር እንዲሁ መቃብሮችንና የተቀደሱ የሚሏቸውን ሥፍራዎች በወይን ቅጠሎች እንደዚሁ ሁሉ ድሪዮድስ ( Druids -ጥንታውያን ፈረንሳዮች) እና ሴልትስ ( Celts - ጥንታውያን እንግሊዞችና አየርላንዶች) የተባሉት ሕዝቦች የጣዖት ካህናቶቻቸው መቅደሶቻቸውን የተቀደሱ በሚሏቸው በቅጠሎች ያስውቡ ነበር ። በጀርመናውያን ዘንድም የብሉይ ዛፍ ( Oak tree) አዲን ለተባለ " የጦርነት አምላካቸው " የተቀደሰ ዛፍ ነው ብለው ስለሚያምኑ እንደ ስጦታ / መስዋዕት/ በማድረግ ያቀርቡለት ነበር ። ይህንንም የዛፍ ስጦታ እስከ ፰ኛው መቶ ክ.ዘ.ቦኒፌስ ( Boniface) የተባለው ሰባኪ በዘዴ ወደ ክርስቶስ ዛፍነት እንዲቀይሩትና ለእየሱስ ልደት ክብር እንዲለውጡት አድርጓል ። ይህ ባህልም ከጀርመን ተነስቶ እስከ አሜሪካ ሊደርስ ቻለ ( L.w Cowie and j
የገና ክብረ በዓል ቀን እንዴት ተወሰነ?
የመጨረሻ ክፍል
ክርስቶስ መቼ ተወለደ? /ታህሳስ 29/ ?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታ የተወለደበትን ወር በቀጥታ ተጽፎ አናገኝም ምክንያቱም ለአማኝ የጌታን የልደት ቀን ማወቅ ስለማያስፈልገው ነው ቢሆንም አስተዋይ የሆኑ ክርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ ወቅቱን ሊያውቁ ይችላሉ ይኽም ቢሆን እንኳን የልደት በዓል እንዲከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትዕዛዝ ስለሌለ ጥቅሙ ለእውቀትና ለጥንቃቄ ያህል ብቻ ይሆናል።

የልደት ቀኑን ስናሰላው

፩ .ጌታ እየሱስ የተጸነሰው አጥማቂው ዮሐንስ በተጸነሰ በስድስተኛው ወር ነበር።/ሉቃ.1:26/

፪. ዮሐንስ የተጸነሰው ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የማገልገሉ ወራት ሲፈጸም ነበር ።/ሉቃ.1:5፣8፣23-25/

፫. በንጉስ ዳዊት በወጣው የ24ቱ የእስራኤል የካህናት ቤተሰብ አገልግሎት ተራ የአብያ ክፍል 8ኛው ነበር። ሁለት ቤተሰቦች በአንድ ወር ውስጥ ግማሽ ግማሹን / 15 ቀናት/ ተካፍለው ያገለግሉ ነበር /1ዜና.24:10/ ስለሆነም የአብያ ቤተሰብ በ4ኛው የእስራኤላውያን ወር ሁለተኛው አጋማሽ 15 ቀናት ያገለግል ነበር።

፬. የእስራኤል የመጀመሪያ ወራቸው ኒሳን / አቢብ/ ሲሆን / አስቴር 3:7/ ይህም በእኛ የመጋቢት ወር ማለት ነውና አራተኛው ወራቸው ደግሞ ታሙዝ ሲሆን በእኛ የሰኔ ወር ማለት ነው።

፭. እንግዲህ የዘካርያስ / የአብያ ቤተሰብ/ የአገልግሎት ተራ በሰኔ ወር ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ሲሆን ከዚህ የአገልግሎት ወራት መፈጸም በኋላ ዘካርያስ ወደቤቱ ሄደ ሚስቱም ጸነሰች። /ሉቃ. 1:23-25/

፮. ይህም ማለት በሐምሌ ወር የመጀመሪያዎቹ ሰሞናት ኤልሳቤጥ ዮሐንስን ጸንሳ ነበር ። ከዚህ ተነስተን ስድስት ወራት ወደፊት ስንቆጥር ጌታ እየሱስ የተጸነሰበትን የታህሳስ ወር እናገኛለን።

፯. ከታህሳስ ወር ጀምረን ዘጠኝ ወራትን ወደፊት ስንቆጥር ደግሞ የተወለደበትን የነሐሴን የመጨረሻ ቀናት ወይም የምስክር ምን የመጀመርያ ቀናት እናገኛለን።

ምንጭ:- እውነት ጋዜጣ ቁ.21
136 viewsፍፁም ፍቅር, 09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-04 21:05:19 *christmas*
ክፍል 1

ስለ ኢየሱስ የውልደት ቦታ፤ ጊዜ ፤ሁኔታ በአለም ደረጃ ብዙ እንደሚባል እናውቃለን። ታድያ ይህንን ለማሳየት አሊያም ለማሰብ ተብሎ እንደ በኃል የሚቆጠረው የገና በኃል ወይንም "christmas" አንዱ ነው።

ስለ"christmas" የተፋለሱ አመለካከቶች ወይንም ልማዶች ውስጥ ሰፋ ያለ መረጃ ለማቅረብ የማቀርብበት መንገድ ቢገድበኝም አንዳንድ እውነታዎችን ግን እነሆ ልበላቹ

"christmas"

ቃሉ የመጣው "christ" እና "mass" ከሚል ሁለት ስሞች ነው ሆኖም ትርጉሙ ከ"catholic church" ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ሰፋ ያለ ሀሳብ አለው። ሆኖም ግን ከሚከበርበት ወቅት በመነሳት እስከ አከባበሩ አንዳንድ ነገሮችን ልንገራችሁ


"christmas" በአውሮፓ የሚከበረው "December 25 ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ በ29 ነው በእርግጥ "february" ላይም የሚያከብሩ እንዳለ ሆኖ በስፋት የሚታወቁት ግን እነዚህ ቀናቶች ናቸው።

ጥያቄ 1: እውን ጌታ"december 25 አሊያም "december 29" ተልዷልን?

መፅሐፍ ቅዱስ መቼ እንደተወለደ ፈፅሞ አይናገርም ሆኖም ግን ከሉቃስ 1:5 ላይ በሚሰጠን መረጃ እንዲሁም ከሉቃስ 1:23_39 በምናገኘው እውነታ ልናሰላው እንቸላለን ሆኖም ግን ፈፅሞ "december"(ታህሳስ) አይደለም።

"december 25 ወይም 29 ያልሆነበት ምክንያቶች

1: በሉቃስ 2:8 ላይ እረኞች መንጋቸውን ሲጠብቁ ሌሊቱን በሜዳ እንዳደሩ ይነግረናል። የ "december" ወር ደግሞ ዝናባማ እና ቀዝቃዛ አየር ያለበት በመሆኑ እረኞች ያውም በሜዳ ብሎም በሞሽት የሚያድሩበት ወር አይደለም

2: በሉቃስ 2:1 መሰረት የህዝብ ቆጠራ እንዲካሄድ እንደታወጀ ይነግረናል ይህን በ"december" ነው ካልን ደግሞ በዚህ ጊዜ ማለትም በ"december" ወር ላይ የህዝብ ቆጠራ ለማካሄድ ፈፅሞ የማይቻል ነው ምክንያቱም ወቅቱ ከላይ እንደጠቀስኩት ዝናባማ እና ብርዳማ በሆኑ ከጤንነት አኳያ ፤ ከትራንስፓርትም አኳያ(ግመል አህያ የመሳሰሉት ለትራንስፓርት ያገለግሉ ነበር) አስቸጋሪ በመሆኑ ቆጠራ የሚካሄድበት ወቅት አይደለም

3:………………ይቀጥላል
102 viewsፍፁም ፍቅር, edited  18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ