Get Mystery Box with random crypto!

[ Audio file : @Metshafkidus– እንደ ፍቃድህ ] እንደፍቃድህ አውለኝ በምህረትህ | www.metshafkdus@gmail.com📚

[ Audio file : @Metshafkidus– እንደ ፍቃድህ ]
እንደፍቃድህ አውለኝ
በምህረትህ ጥላ ከልለኝ
በመልካሙ መስክ አሰማራኝ

እንደፍቃድህ
መውጣት መግባቴ መዋል ማደሬ
ላንተ ሰጠሁኝ እድሜ ዘመኔን
ከኔ የሆነው ከቶ ምን አለ
ሁሉም የአንተ ነው ታደርገዋለ

አንተ ነህና የእኔ አቅጣጫዬ
በሕይወት ቅደም ቅዱስ ጌታዬ

እንደፍቃድህ
ከሌለህበት አማኑ እረኛ
የኔው ይሆናል ወይኑ መናኛ
አንተ ስትገባ ከልቤ ቤት
ባዶ ጋን ሞላ በበረከት

እንደፍቃድህ
አይሞላልኝ ልቤ የሚያስበው
ጥብርያዶስን ነው እኔ ምመኘው
ስለዚህ አንተን አስቀድሚያለሁ
ኑሮዬን ሁሉ ይሁን ብያለሁ
├───────────
│አንተ የመድኃኒቴ አምላክ
│ነህና በእውነትህ ምራኝ፥
│አስተምረኝም፤ ቀኑን ሁሉ
│አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።
│ ❏ መዝ 25፥5
├───────────
├⊙ዘማሪ ዲያቆን መባ
├───────────
├ Metshafkidus