Get Mystery Box with random crypto!

ገና ክብረ በዓል ቀን እንዴት ተወሰነ? ጄራርድ እና ፖትሪሷያ ዴልፊ 'The Christmas Alm | www.metshafkdus@gmail.com📚

ገና ክብረ በዓል ቀን እንዴት ተወሰነ?

ጄራርድ እና ፖትሪሷያ ዴልፊ "The Christmas Almanac " በተሰኘው መጽሃፋቸው አውሮፓውያኑ ታህሳስ ፪፭ እንዴት ቀስ በቀስ የሮማውያን ባህል እንደሆነ ሲተርኩ የሚከተለውን ብለዋል " ከበፊቱም የሳቱርሊና እና የአዲስ ጨረቃ ( Kalends) ክብረ በዓላት በክርስቲያኖች ዘንድ የተገለጡ ነበሩ ። ነገር ግን ታህሳስ ፪፭ን የእየሱስ ልደት ብሎ ማክበር የተጀመረው ከሮማውያን አህዛባዊ እምነት በመዋስ ነበር ።
" ሚትራ ( Mithra) የፋርሶች " የብርሃን አምላክ ሲሆን የተወለደውም በታህሳስ ፪፭ ቀን ከቋጥኝ ድንጋይ ነበር ተብሎ በተከታዮቹ ይታመናል ፤ ሮም እንግዳና አዳዲስ አማልክትን በማስገባትና በማምለክ የታወቀች አገር ስትሆን በ፫ኛው መቶ ክ/ዘ በ፪፯፬ ዓ.ም ፀረ ክርስትና የነበረው የሮማዊው ንጉስ ኦውሪኸን ( Aurehan) ይህንኑ የአምልኮ ቀን በአገሩ ላይ " የተሸነፈችው ፀሃይ ቀን " ( Dies inuicti Solis) በማለት በታህሳስ ፪፭ ቀን እንዲከበር አደረገ።
ሚትራ ፀሐይ የለበሰ ፣ ፀሐይ የተዋሃደ አምላካችን ነው ብለው ስለሚያምኑ ቀኑ በሚትራይዝም እምነት ተከታዮች ዘንድ እጅግ ታላቅ ነበር ። በኋላም ይህ ቀን በኦውሪኸን አስመጪነት በሮማውያን ዘንድ ታላቅ የሕዝብ በዓል መሆን ቻለ። ንጉስ ቁስጠንጢኖስ ክርስትናን እስከተቀበለበት ቀን ድረስም ሚትራየዝምን ይከተል እንደነበር ይታመናል። ምናልባትም ንጉስ ቁስጠንጢኖስ (Constantine) የአሮጌ እምነቱን በዓል ወደ አዲሱ እምነቱ እንዲገባ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ ሊሆን ይችላል ( The Christmas Almanac, 1979)
የፈረንጆቹ ታህሳስ ፪፭ ለመጀመሪያ ግዜ የገና ወይም የልደት በዓል ሆኖ የተከበረበትን እርግጠኛ ዓመት ማወቅ ባይቻልም የቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚጠቁመው ግን ጊዜው ፬ኛው መቶ ክ.ዘ ወይም ቤተክርስቲያን ከተመሰረተች ከ፫መቶ ዓመታት በኋላ መሆኑ እርግጥ ነው ። ይህ ደግሞ እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ እጅግ የዘገየ ግዜ ነበር። በቄሳሮች ግዛት ዋና ከተማ ሮምን ጨምሮ ጌታ ከሞተ ከ፫መቶ ዓመታት በኋላ የጌታ ልደት የሚባል በዓል በክርስቲያኖች ዘንድ ፈጽሞ አይታወቅም ነበር ። ይህ ደግሞ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ለዚህ ልምምድ ወይም ትምህርት መነሻ እንዳይደለች ያሳየናል። የገና ( Christmas) በዓል ከመነሻው ጀምሮ " ለቅዱሳን ፈጽሞ አንዴ ከተሰጠ ኃይማኖት ( እምነት) / ይሁዳ.3/ጋር ፈጽሞ ግንኙነት የለውም።
....
የገና ክብረ በዓል ቀን እንዴት ተወሰነ?
............ካለፈው የቀጠለ
በገና አከባበር ባህል ላይ የአውሮፓውያን ተጽዕኖ እና የገና ዛፍ

ከመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በተጨማሪም በምዕራቡ የነበሩት አህዛባዊ ክብረ በዓላትም ዛሬ ላለው የገና ባህላዊ አከባበር አስተዋፅኦ አድርገዋል ። ከእነዚህም አንዱ " የአስራ ሁለቱ ምሽቶች የቴውቶኒክ " በዓል በመባል የሚታወቅ ሲሆን የሚከበረውም በአውሮፓውያኑ ከታህሳስ ፪፭ እስከ ጥር ፮ ነበር ። ይህም ክብረ በዓል የሚደገሰው በተፈጥሮ ኃይሎች መካከል በሚደረገው ጦርነት ላይ በተመሰረተ ትረካ ላይ ሲሆን ይኸውም ሞትን ይወክላል በማለት " ታላቁ በረዶ" ( The ice giant ) መካከልና ሕይወትን ይወክላል ተብሎ በሚታሰበው " የፀሃይ አምላክ መካከል የሚካሄድ ጦርነት ነው።" የዊንተር ሶልስቲስ ( Winter Solistice) / ፀሃይ ከምድር ወገብ የምታልፍበት ወቅት / እስኪቃረብ ድረስ ታላቁ በረዶ / ሞት/ በሚያቀዘቅዘው ኃይሉ ሲያሸንፍ ይሰነብትና ከዚያ በኋላ ግን የፀሃይ አምላክ / ሕይወት/ ድል እየተቀዳጀ መምጣት ይጀምራል በማለት ያምኑ ነበር።
ክርስትና ወደ ሰሜን አውሮፓ በተስፋፋበት ግዜ በታህሳስ ወር ውስጥ የሚከበሩ ተመሳሳይ የሆኑ የፀሃይ መወለድ ክብረ በዓላት ገጥመውት ነበር። ለምሳሌ በስካንዲኒቪያን ሕዝቦች የሚከበር የዮሌ ክብረ በዓል ( Yule feast) ነበር ። ይህም በዓል በተከታታይ ለ፩፪ ቀናት የሚከበር ሲሆን በበዓልም ወቅት ሰዎች የፀሃይን ማሸነፍ ለማገዝና ለማበረታታት በታላቅ ሁኔታ እሳት ያቀጣጥሉና ያበሩ እንደነበር እንዲሁ መቃብሮችንና የተቀደሱ የሚሏቸውን ሥፍራዎች በወይን ቅጠሎች እንደዚሁ ሁሉ ድሪዮድስ ( Druids -ጥንታውያን ፈረንሳዮች) እና ሴልትስ ( Celts - ጥንታውያን እንግሊዞችና አየርላንዶች) የተባሉት ሕዝቦች የጣዖት ካህናቶቻቸው መቅደሶቻቸውን የተቀደሱ በሚሏቸው በቅጠሎች ያስውቡ ነበር ። በጀርመናውያን ዘንድም የብሉይ ዛፍ ( Oak tree) አዲን ለተባለ " የጦርነት አምላካቸው " የተቀደሰ ዛፍ ነው ብለው ስለሚያምኑ እንደ ስጦታ / መስዋዕት/ በማድረግ ያቀርቡለት ነበር ። ይህንንም የዛፍ ስጦታ እስከ ፰ኛው መቶ ክ.ዘ.ቦኒፌስ ( Boniface) የተባለው ሰባኪ በዘዴ ወደ ክርስቶስ ዛፍነት እንዲቀይሩትና ለእየሱስ ልደት ክብር እንዲለውጡት አድርጓል ። ይህ ባህልም ከጀርመን ተነስቶ እስከ አሜሪካ ሊደርስ ቻለ ( L.w Cowie and j
የገና ክብረ በዓል ቀን እንዴት ተወሰነ?
የመጨረሻ ክፍል
ክርስቶስ መቼ ተወለደ? /ታህሳስ 29/ ?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታ የተወለደበትን ወር በቀጥታ ተጽፎ አናገኝም ምክንያቱም ለአማኝ የጌታን የልደት ቀን ማወቅ ስለማያስፈልገው ነው ቢሆንም አስተዋይ የሆኑ ክርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ ወቅቱን ሊያውቁ ይችላሉ ይኽም ቢሆን እንኳን የልደት በዓል እንዲከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትዕዛዝ ስለሌለ ጥቅሙ ለእውቀትና ለጥንቃቄ ያህል ብቻ ይሆናል።

የልደት ቀኑን ስናሰላው

፩ .ጌታ እየሱስ የተጸነሰው አጥማቂው ዮሐንስ በተጸነሰ በስድስተኛው ወር ነበር።/ሉቃ.1:26/

፪. ዮሐንስ የተጸነሰው ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የማገልገሉ ወራት ሲፈጸም ነበር ።/ሉቃ.1:5፣8፣23-25/

፫. በንጉስ ዳዊት በወጣው የ24ቱ የእስራኤል የካህናት ቤተሰብ አገልግሎት ተራ የአብያ ክፍል 8ኛው ነበር። ሁለት ቤተሰቦች በአንድ ወር ውስጥ ግማሽ ግማሹን / 15 ቀናት/ ተካፍለው ያገለግሉ ነበር /1ዜና.24:10/ ስለሆነም የአብያ ቤተሰብ በ4ኛው የእስራኤላውያን ወር ሁለተኛው አጋማሽ 15 ቀናት ያገለግል ነበር።

፬. የእስራኤል የመጀመሪያ ወራቸው ኒሳን / አቢብ/ ሲሆን / አስቴር 3:7/ ይህም በእኛ የመጋቢት ወር ማለት ነውና አራተኛው ወራቸው ደግሞ ታሙዝ ሲሆን በእኛ የሰኔ ወር ማለት ነው።

፭. እንግዲህ የዘካርያስ / የአብያ ቤተሰብ/ የአገልግሎት ተራ በሰኔ ወር ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ሲሆን ከዚህ የአገልግሎት ወራት መፈጸም በኋላ ዘካርያስ ወደቤቱ ሄደ ሚስቱም ጸነሰች። /ሉቃ. 1:23-25/

፮. ይህም ማለት በሐምሌ ወር የመጀመሪያዎቹ ሰሞናት ኤልሳቤጥ ዮሐንስን ጸንሳ ነበር ። ከዚህ ተነስተን ስድስት ወራት ወደፊት ስንቆጥር ጌታ እየሱስ የተጸነሰበትን የታህሳስ ወር እናገኛለን።

፯. ከታህሳስ ወር ጀምረን ዘጠኝ ወራትን ወደፊት ስንቆጥር ደግሞ የተወለደበትን የነሐሴን የመጨረሻ ቀናት ወይም የምስክር ምን የመጀመርያ ቀናት እናገኛለን።

ምንጭ:- እውነት ጋዜጣ ቁ.21