Get Mystery Box with random crypto!

ከምንጩ እንቅዳ! ======================= ~ እንደሚባለው የእግዚአብሔር ቃል ከመግቢ | www.metshafkdus@gmail.com📚

ከምንጩ እንቅዳ!
=======================
~ <<ነገርን ከሥሩ ውኃን ከጥሩ>> እንደሚባለው የእግዚአብሔር ቃል ከመግቢያ እስከ ማጠቃለያ፣ ከአርእስት እስከ ኅዳግ ሲነበብ አሳቡ ይገኛል፣ ሲተረጐም ምሥጢሩ ይበራል፣ ሲብራራ ስፋቱ ይለካል፣ ሲተነተን ተመሥጦው ከፍ ይላል፡፡

~ የእግዚአብሔር ቃል፡-
-> የሚነበብ
-> የሚጠና
-> የሚተነተንና
-> ከሕይወት ጋር የሚዛመድ መስተዋት ነው፡፡

~ የእግዚአብሔር ቃል ዕለታዊ ዜና አይደለም፣ ዜና ከዕለቱ ሲያልፍ በማግሥቱ የወሬ ቋንጣ ይሆናል፡፡

~ የእግዚአብሔር ቃል ግን በዘመናት አዲስ፣ ሕይወትን የሚሰጥ መንፈሳዊ እንጀራ ነው፡፡

~ የእግዚአብሔር ቃል ማስታወቂያ አይደለም፤ ማስታወቂያ በቅጽበተ ዓይን ዓይተነው እናልፈዋለን፡፡ ከማስታወቂዎቹ የማይመለከተን ይበዛል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ግን በአድራሻችን የተላከ መልእክታችን ነው፡፡

~ ስለዚህ ሁላችንን ይመለከተናል፡፡ አንድን ፅሁፍ አንብበን ምን ለማለት እንደ አልገባ ቢለን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ፅሁፉን ከፃፈው የበለጠ የሚተነትንልን ማንም የለም፡፡

~ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቃል ከባለቤቱ ከመንፈስ ቅዱስ መረዳት ከምንጩ እንደ መቅዳት ነው፡፡ ስለዚህ ቃሉን ለመረዳት ጸሎትና ጽሞና ያስፈልጋል፡፡ ያልደፈረሰውን፣ ያልተበከለውን የሕይወት ውኃ ከምንጩ ከመንፈስ ቅዱስ፣ ከምንጩ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንድንረዳ በጸሎትና በተዘጋጀ ልቡና መቅረብ ያስፈልገናል፡፡

-->> ልብ አድርጉ፡- እግዚአብሔር ቃሉን የሰጠው ለሊቃውንት ሳይሆን ለልጆቹ ነው፡፡ ስለዚህ ቃሉ እኔን አይገባኝም ማለት የለብንም፡፡ ካልደፈረሰው፣ ካልተበረዘው ተቀድቶ ከማያልቀው ህያው ከሆነው ምንጭ ከመንፈስ ቅዱስ፣ መፅሐፍ ቅዱስ እንቅዳ።ብሩክ ሁኑልኝ!

< ክብር እስከ ሞት ድረስ ለወደደን::