2022-01-06 05:05:53
"ምን እላለሁ፤
ምን እናገራለሁ፤
የጌታዬ ልደቱ ድንቅ ነው።
የአማኑኤል ልደቱ ድንቅ ነው።"*
፣
አለምን በቃሉ፥ የፈጠረ ጌታ፥
ሁላችንን ሊያድን ሊወስድ፥ የኛን ተርታ።
ያለም ጌታ ሆኖ፥ ያየነው በበረት፤
ምን አይነት ፍቅር ነው፥ ምን አይነት ደግነት።
፤
በናቱ እቅፍ ሆኖ፥ በሰማያት አለ፤
በሰማያት ሆኖ፥ በናቱ እቅፍ አለ።
ከኪሩቤል ጀርባ፥ ሳይወርድ ከዙፋኑ፤
ይገርማል ይደንቃል፥ በኛ መመስገኑ።
፥
ቅድመ አለም ያለ እናት ተወልዶ ከአባቱ
ድህረ አለም ያላአባት ወለደች እናቱ
ይህን ድንቅ ጥበብ፥ ፍጥረቱ ተማክሮ፤
ድንቅ ይባላል እንጂ፥ ማን ያውቃል መርምሮ።
፥
ነብያት የናፈቁት፥ ትንቢታቸው መጣ ፤
ከድንግል ማህፀን፥ ያለድካም ወጣ፤
መለኮት ሳይከፈል፥ ወደ አለም መጣ፤
የጽድቃችን ጸሀይ፥ ከሰማያት ወጣ።
++++++
እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ
*("ምን እላለሁ ምን እናገራለሁ..."
ሐይማኖተ አበው ዘቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ)
ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
t.me/Menfesawigetmoch
2.0K viewsedited 02:05