Get Mystery Box with random crypto!

ማርያምን ተረከ… ጽጋን የተሞላች የጌታዬ እናቱ የአዳም ተስፋ ናት ኪዳን የምህረቱ፡፡ በደም የነጠ | መንፈሳዊ ግጥሞች ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

ማርያምን ተረከ…

ጽጋን የተሞላች የጌታዬ እናቱ
የአዳም ተስፋ ናት ኪዳን የምህረቱ፡፡
በደም የነጠቀ ከዘላለም ሲቃ
ማረፊያ ነው ልጇ የሰላም አለቃ፡፡

እርሻችን አሸተ ደመናው ተከፍቶ
እንጀራን ጠገብን ጎተራችን ሞልቶ፡፡
የዘራነው ሁሉ በወቅቱ ደረሰ
የአይኖቻችን እንባ በልጇ ታበሰ፡፡

የወይኑን እንስራ ይሞላል ምልጃዋ
በታሪክ መካከል ያበራል ስራዋ፡፡

ያዘነ ተጽናና ደካማው በረታ
ታላቅ ለታናሹ ለቀቀለት ቦታ፡፡
ትውልድ ተረጋጋ ዘመን ተባረከ
ብራና መጻፉ ማርያምን ተረከ፡፡
++++++
ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
t.me/Menfesawigetmoch