Get Mystery Box with random crypto!

ከጥበብ እልፍኝ

የቴሌግራም ቻናል አርማ liulzemaryam — ከጥበብ እልፍኝ
የቴሌግራም ቻናል አርማ liulzemaryam — ከጥበብ እልፍኝ
የሰርጥ አድራሻ: @liulzemaryam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 905
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
አስደሳች ግጥሞች፦በድምፅ
በፅሁፍ
አስተማሪ ታሪኮች
ትረካዎች
ወግ
እና ሌሎች የጥበብ ስራዎች ያገኙበታል።
.
.
ምኞት አይከለከልም ያሉትን ሰምቼ
ሞቴን ተመኘውት መኖሬን ጠልቼ!
.
.
#💚💛❤
@jape16

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-02-13 10:55:50 ሰንበት-
* * * * *
የመመለስ መንገድ ባይሆንም ለጌታ
መጣል ግን አይከፋም "የነበርን" ቦታ፡፡
የሰንበት ቀንና ሰንበት ትምርትቤት
ትዝታ የሌለው ባይኖርም አንዳች ቤት
በልጅነት ድሮ
"አሾረው ነበረ" የደብሩን ከበሮ::
በጊዜ በዕድሜ እየደበዘዙ
"ዘምሬ ነበረ" ማለት የሚያበዙ
"ከነበር" ፉከራ ጀርባ ተቀምጠን
አታውቁም ከመባል ፍርሃት ሮጠን
ሰንበት ትምህርትቤት
መልዕክተ ዩሐንስን
መልክአ ኢየሱስን
"ዘልቄ ነበረ"
የሚለው ሰው ቁጥር ያውም በተውሶ
ሰንበት መማርና
ሰንበት ማክበር ቀረ "ነበርን" ከልሶ፡፡
"ነበርን" በንባብ
"ነበርን" በወርድ
"ነበርን" በዜማ
ስናጠና ከርመን እንደሠርግ ዘፈን
ለእግዜርም ለሰውም "ነበር" የተረፈን
ሙዳይ ምጽዋትን የመያዝ ትህትና
አሁን ቀይረነው
በሚይዙ ሰዎች ውስጣችን ሳይቀና
ልክ እንደጅልነት
ልክ እንደልጅነት
ሰፍረነው ሲያበቃ
"እኛም እንዲህ ነበር"ን ማለት ሆነ በቃ፡፡
ትህትናን ሰበርን
ትናንትን ቀበረን
ስናጠናው አለን መልክአ "ነበርን"፡፡



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
3.8K views07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-12 11:52:31 * * * * * * *
አንቺን በሰማሁት ብሰማው አምላኬን
ዓለም ባላወቀኝ ቁመትና መልኬን፡፡
የቀበርኩትን ልብ እንዳይነቃ በዛር
ናፍቀኸኛል ስትይ ነቃ እንዳላዛር
ነቅቼልሻለሁ
ቀጣዩ ምንድነው?
ናፈቀኸኛል
ናፍቀኸኛል
ናፍቀኸኛል መባል
ታውቂያለሽ ያባባል::
የወንድ ልጅ ነገር እስከዚህ ይሞኛል
አታምኚኝም እንጂ
ናፍቀኸኛል መባል ራሱ ናፍቆኛል፡፡
ልተኛበት አንዴ ቃልሽን መልሽው
እንቅልፌን ወስዶታል ናፈቀኸኛል ያልሽው፡፡


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
3.3K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-02 08:54:39 ብቸኛ ሰው የለም፡፡
ኤልያስ ሽታኹን
* * * * * *

ይሄ ሁሉ ሰው ስለብቸኝነት
የተዘፈነ የሚሰማው
የተገጠመ የሚያነበው
የተሳለ የሚቃርመው
ወዶ ይመስልሀል?
ከሰው ጋር የጠመመ በምንም ላይቀና
ከብቸኝነት ውሰጥ ምን ደስታ አለና?
ምንም:፡
ብቻ እንዲሁ
ከአብሮነት ስቃይ
ዕንባ ያላባባይ
በአብሮነት ተዛዝሎ
ከመክረም ተቋስሎ
እያለ አሸሸ
ስንቱ ራሱን ዋሸ?
ወዶ ይመስለሀል?
ከአድማስ እስከ አድማስ
ሰው ሀዘኑ ሲማስ
እንዲያው ከራሴ ጋር ልሁነው ልንደደው
ብቸኝነት ዜማን
ለሀገሩ በሙሉ ማነው ያስለመደው?

እንጂ
ዘር የሌለው
የሰው ደም ያልሳበው
ሳቅን ፍንጣቂ
የዕንባውን ጭማቂ
የሚያይለት ያጣ
ብቸኝነት ዕጣ
ብሶት ቆፈን ወርሶት
በየጥቃቅኑ ሆድ አንጀቱን ብሶት
ገና ፈገግ ሲል
ጠፍንጎ እየያዘው ብቸኝነት ከፍንጅ
ብቻውን ተፈጥሮ
ብቻውን የሞት የታለ የሰው ልጅ?

ብቸኛ ሚባለው
ወይ እኛ የተውነው
ቢወርደን ዕንባውን
ወይ እኛን ትተውን
እንደሆን ነውና
ብናበጥር ዘሩን
አውጥተን ብናየው ከሀዘኑ ቀለም
የተተወ እንጂ ብቸኛ ሰው የለም፡፡



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
3.3K views05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-15 14:42:58 #አንቺ ባለ ዶሮ

እስቲ ልጠይቅሽ ንገሪኝ ግድ የለም
ይሄ ሞያሽ ምንጩ ከእናትሽ አይደለም

መመጠን መከለስ
ማጠብ ማቁላላቱን በሙሉ ትተሽው
ማረዱን ብቻ
መገንጠሉን ብቻ.......ከወዴት ተማርሽው?


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
4.4K views11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 09:29:01 እኛም እንደ እረኞቹ በቤተልሔም መገኘትን ወደድን እንደ ሰብዓ ሰገል እጅ መንሻ ማቅረብን ሻትን እንደ ላም አህያ እስትንፋስ ብንለግሰው አልን እንደ ዮሴፍ በድንቅ የመላእክት ጉባዔ መታደምን ናፈቅን… እንዲሁ ወዶን ሳይፀየፈን በደላችንን ሊሽር ሰው ሆኖልናልና እንኳን ደስ አለን!

መልካም በዓል!


@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
4.4K views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-04 11:59:39
አበበና ጫላ


አጀንዳ ስታጣ ፣ በስም አትጣላ!
አንተም ጩቤ ጨብጥ ፣ አንተም በሶ ብላ
ጨቡዴ ሁን ሀጎስ ፣ አቶቴም ሁን ሺፋ
ማንም ይበሉህ ማን ፣ ሲጠሩህ አትጥፋ
አቤት በል በኩራት ፣ ክብርህን አትጣው
መልአክ ቢሆንም ፣ ስምን የሚያወጣው
እኛ ግን እኛ ነን ፣ ሀያል ያልበገረን
አለማወቅ እንጂ ፣ የሚያከራክረን
እንዳልተገዛን ነው ፣ ስማችን ሚነግረን።
።።።
አሁን ለምሳሌ
ምኒሊክ ተወልዶ ፣ ባይጠገን ቅስሜ
ምኒልክ ተወልዶ ፣ ባይፈታ ህልሜ
በላቶቪች ነበር ፣ በላይ ሚሉት ስሜ!


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
3.9K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-29 20:44:08 የመወለድ ናፍቆት!

ግፈፈው ጥላውን
አሁን ያጠላውን ...
ህዝቤ ይተራመስ ይሯሯጥ ለግፊያ
አይኔ አይቶ ይሳቅ ወዝ ያለው ገበያ
ይጢስብን እጣን.. .
ቁጣህ እንዳይነካን...
እንኳን አደረሰህ ይበለኝ ጎረቤት
ለሊት ላይ ይሰማኝ የመቅደስ ማህሌት
ይጩህ ደጄ ላይ በግ
ይድረስ የበዓል ወግ
ይከፋፈል ቅርጫ ቆሞ አባወራ
እናቶች ያስምሩት የማጀቱን ስራ
ተሰዶ የኖረው ይግባ ዲያስፖራ
ጦር የፈታው ወሬ ደርሶ አይወራ
ህፃናት ያውሱን የጃቸውን ምስል
ተወልደህ ውለደን አዲስ እንድንመስል
ገና ሆይ ልደት ሆይ
ይሄን ክፉ ዘመን መጥተህ አትሽርም ወይ?


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
4.2K views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-28 19:15:10 "ደህና ነህ አትበይኝ"

ደህና መሆን ማለት
በጭንቀት ተራራ በናፍቆት ቁልቁለት
ድካም በበዛብት በብቸኝነት ቤት
መዳከር አይደለም....

ደህና መሆን ማለት....

ሣቅሽ በሌለበት በተቆጣ ሀገር
ደሥታ በቸገረው በሚያሣዝን ሠፈር
መንደርተኛ ተብሎ መቆጠር አይደለም

ደህና መሆን ማለት.....

ከተትረፈረፈው ከሚማርክ ገላ
ወይም ከሚያሠክረው ከጠላው አተላ
አንችን እያሠቡ መጎንጨት አይደለም

ደህና መሆን ማለት....
የትም በማያደርሥ መንገድ መመላለሥ
በማታውቂው ሥፍራ ትኖሪያለሽ ብሎ
...... ..........ሀገር ምድሩን ማሠሥ
መቅበዝበዝ አይደለም.....

ደህና መሆን ማለት

ከ ጫጫታ መሀል...
ፍዝዝ ብሎ ቁሞ ድምፅሽን መናፈቅ
አንቺን እያሠቡ...
ውብ ተፈጥሮን ትቶ ፈራሽ ጣኦት ማድነቅ
መሥለምለም አይደለም..

እናማ የኔአለም..
ደህና ነህ?? እያልሽኝ ትመጫለሽ እያልኩ
አንቺን እየጠበኩ...
አንቺን ያሣፈረ መርከብ የሌለበት
ዕልፍ አባይ ጎረፈ
ጠረንሽን ያልያዘ ዕልፍ አየር ነፈሠ
ዕልፍ ቀን አለፈ

.
.
እናም ቃሌን ሥሚ
ደህና ነህ እያልሽኝ ዝምምምም ከሆነ መልሤ
ዝምታየን ሥሚ...
ደህና ባልሆነ ሀገር..
መቅረትሽ ሢጨመር...
ደህና ነኝ እያለ
እንዴት ልቤ ዋሽቶ ምላሤ ይናገር!!



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
3.4K views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-26 12:04:34 ትናንትና ማታ
(በዕውቀቱ ሥዩም)
ላሟሟሽ ሲገባኝ፣እንዳሞሌ አጥቤሽ
በመጨረስ ፋንታ
ለነገ ቆጥቤሽ
አስተርፌሽ ለሰው
የጸጸት ሱናሚ ፤ዓለሜን አመሰው፡፡
ምነው ቢቻል ኖሮ
ፈገግታሽን ቋጥሮ
ሙዳይ ውስጥ መደበቅ
ጃንደረባ ቀጥሮ
ጭንሽን ማስጠበቅ
ክፍት ልቤን ይዤ፤ ዝግ ደጅሽን ጠናሁ
በሰበብ ወድጄሽ ፤ያለሰበብ ቀናሁ፡፡
ፍቅር በተባለ፤ ግራ- ገቢ ነገር
ከጨመተው አገር
ከሰከነው ቀየ
መናፍቅ ይመስል፤ ባዋጅ ተነጥየ
እንደካፖርቴ ቁልፍ፤ ልቤን የትም ጥየ
የትም ስከተልሽ
የትም ሆኖ እድልሽ፤
ሁሉ ያንች ወዳጅ
ሁሉ ባላንጣየ
መፈቀር ሆኖ ጣሽ፤ መቅናት ሆኖ ጣየ
ላንቺ ብስል ፍሬ፤ ለኔ ገለባ ግርድ
ላንቺ እቅፍ አበባ፤ ለኔ እቅፍ ሙሉ ብርድ
ማነው የበየነው ፣ይህን ግፈኛ ፍርድ፡፡




➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
3.3K views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-23 15:34:43 ያንን ለሊት ልታነጊ ከድቅድቅ ስር
ስታመሺ
ጨዋነቱ መች ጎሎ ነው ዝም ያለሽን
ምትረብሺ
( አቤት አንቺስ )
ካፈጣጠር ብዙ እርቀሽ መመለስን
ስትሰውሪ
ክንፍም አለሽ አዎ አውቃለው በእርምጃ
ነው የምትበሪ

(አጀብ ለኔ)

ከጥላሽ ጋር ውል የገባው መገለጥሽ
ሚናፍቀኝ
ሁሉንሽም አወኩኝ ስል ፍፁምነት
ሚጨርሰኝ
አወይ ለኔ....
አንቺን ብዬ ዳር ለያዝኩኝ
መመለስሽን ፍለጋ መሄድሽን የቀጠርኩኝ
መጨረስ ነሽ ዝንተ አለሙን
የመንጠፍጠፍ መውረድ ደራሽ
ሊያሳይ ነው የከተብሽ ገነት አይደል
ያንቺ ስፍራሽ
የማለዳ የወፍ ዜማ ጉም የያዛት ነሽ
ወገግታ
የመሳካት ነሽ አንኳሩ የስለቴ ዋና ቦታ
ስፀልይ ነው የምጀግን ስረጭሽ ነው
ምበረታ
ፀበል ፈውስ ለድክመቴ የአምላክ ቃሉን
ማስታወሻ
የእኔ እምነት ትክክል ነው የክርክር
ማጣቀሻ
የመአበል የዝምታው የማለቆች
መንቀራፈፍ
ወጀብሽን ስታበዢ በኪዳንሽ የምንሳፈፍ
መውረድ ነፅቶ መበከልን እዛ ጥሎ
ከደግ ጋር እያወጉ ቅድ ስናን ተመስሎ
ደሞ ደርበብ መቀዛቀዝ
ከብዙ ጋር ምንም አለ በመድመቅ
ውስጥ ሚደበዝዝ
ከሰራሽኝ ሰው መሆን ላይ አፍቃሪነት
ሲሽኮረመም
የኔን ማለፍ ፈቅጄ ነው በጣሮች ውስጥ
አንቺን ማክም
****************
(ካሊድ አቅሉ)



➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam
3.1K views12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ