Get Mystery Box with random crypto!

* * * * * * * አንቺን በሰማሁት ብሰማው አምላኬን | ከጥበብ እልፍኝ

* * * * * * *
አንቺን በሰማሁት ብሰማው አምላኬን
ዓለም ባላወቀኝ ቁመትና መልኬን፡፡
የቀበርኩትን ልብ እንዳይነቃ በዛር
ናፍቀኸኛል ስትይ ነቃ እንዳላዛር
ነቅቼልሻለሁ
ቀጣዩ ምንድነው?
ናፈቀኸኛል
ናፍቀኸኛል
ናፍቀኸኛል መባል
ታውቂያለሽ ያባባል::
የወንድ ልጅ ነገር እስከዚህ ይሞኛል
አታምኚኝም እንጂ
ናፍቀኸኛል መባል ራሱ ናፍቆኛል፡፡
ልተኛበት አንዴ ቃልሽን መልሽው
እንቅልፌን ወስዶታል ናፈቀኸኛል ያልሽው፡፡


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam