Get Mystery Box with random crypto!

አበበና ጫላ አጀንዳ ስታጣ ፣ በስም አትጣላ! አንተም ጩቤ ጨብጥ ፣ አንተም በሶ ብላ ጨቡዴ ሁ | ከጥበብ እልፍኝ

አበበና ጫላ


አጀንዳ ስታጣ ፣ በስም አትጣላ!
አንተም ጩቤ ጨብጥ ፣ አንተም በሶ ብላ
ጨቡዴ ሁን ሀጎስ ፣ አቶቴም ሁን ሺፋ
ማንም ይበሉህ ማን ፣ ሲጠሩህ አትጥፋ
አቤት በል በኩራት ፣ ክብርህን አትጣው
መልአክ ቢሆንም ፣ ስምን የሚያወጣው
እኛ ግን እኛ ነን ፣ ሀያል ያልበገረን
አለማወቅ እንጂ ፣ የሚያከራክረን
እንዳልተገዛን ነው ፣ ስማችን ሚነግረን።
።።።
አሁን ለምሳሌ
ምኒሊክ ተወልዶ ፣ ባይጠገን ቅስሜ
ምኒልክ ተወልዶ ፣ ባይፈታ ህልሜ
በላቶቪች ነበር ፣ በላይ ሚሉት ስሜ!


➤ከወደዱት በቅንነት ይቀላቀሉን!

@liulzemaryam
@liulzemaryam
@liulzemaryam