Get Mystery Box with random crypto!

#ትንሽ_ብቻ ሮበርት በአንድ የአሜሪካ ከተማ የሚኖር ከባድ የአእምሮ ህመም ያለበት ሰው ነው። ስራ | 15:53

#ትንሽ_ብቻ

ሮበርት በአንድ የአሜሪካ ከተማ የሚኖር ከባድ የአእምሮ ህመም ያለበት ሰው ነው። ስራ አይሰራም፤ ከቤት አይወጣም ከመጠን ባለፈ ሁኔታ ሬዲዮ እያዳመጠ ነው የሚውለው። አንዲት የማህበራዊ ድጋፍ ተማሪ ቤቱ ሄዳ አይታው ሪፖርት እንድትፅፍ በአስተማሪዋ ትታዘዛለች።

አይታው ስትመለስ አስተማሪዋ "ሮበርት እንዴት ነው?" ብላ ትጠይቃለች።
ተማሪዋም "በጣም የሚገርም ችሎታ ያለው ሰው ነው።" ብላ ትመልሳለች።
"የምን ችሎታ?!"
"ሬዲዮ የማዳመጥ ችሎታ። እንደሱ በትእግስት ማዳመጥ የሚችል ሰው የለም።"....

ከቀናት በኋላ ተማሪዋ አንድ የሬዲዮ ጣቢያ ሄዳ "የሚተላለፉቱን ዝግጅቶችና ማስታወቂያዎች በነፃ የሚመዘግብ ሰው ትፈልጋላችሁ?" ብላ ስትጠይቅ የጣቢያው ባለቤቶች ተስማሙ። ሮበርት ያለ ክፍያ በጣቢያው የሚተላለፉትን ዝግጅቶች እና ማስተወቂያዎች መመዝገብ ጀመረ። ሮበርት ጥንቅቅ አድርጎ ነው የሚመዘግበው። የሬዲዮ ጣቢያው ባለቤቶች ተደስተው ደሞዝ ይከፍሉት ጀመረ። ሮበርት የመጀመሪያ ደሞዙን ሲያገኝ ለማህበራዊ ድጋፍ ተማሪዋ "ለብዙ አመታት ከቤት ውጭ ምግብ በልቼ አላውቅም። ዛሬ ሀብታም ሆኛለሁ። ውጭ ነው የምበላው ደግሞ ብቻየን አልሄድም። እባክሽ ምሳ ልጋብዝሽ።" አላትና ሬስቶራንት ሄዱ።

ምሳ እየበሉ "በህይወቴ ትልቅ ለውጥ ነው ያመጣሽልኝ። አሁን ስራ አለኝ፣ ደሞዝ አለኝ፣ የማገኛቸው ሰዎች አሉ።" አላት።

እሷም "ኧረ እኔ ምን አደረኩልህ?" አለችው....

እይታችንን ትንሽ ብንለውጥ (ትንሽ ብቻ) ቢያንስ በአንድ ሰው ህይወት ላይ ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንችላለን።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ከዶ/ር ዮናስ ላቀው
@lifein1553