Get Mystery Box with random crypto!

#ቅምሻ አንድ ካምፓኒ ሰራተኛቸው አመታዊ የጉዞ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ወደ አዞ እርባታ | 15:53

#ቅምሻ


አንድ ካምፓኒ ሰራተኛቸው አመታዊ የጉዞ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ወደ አዞ እርባታ ቦታ ወሰዳቸው፡፡ ጉዟቸውን እንደቀጠሉ አንድ በአዞዎች የተሞላ ሀይቅ ጋር ሲደርሱ የካምፓኒው ባለቤት አንድ ሀሳብ አቀረቡ....

"እዚህ ሀይቅ ውስጥ ገብቶ ከአዞዎቹ ተርፎ የወጣ ሰው አምስት ሚልየን ብር ይሸለማል ... ምናልባት በአዞዎቹ ተበልቶ ከሞተ ደግመሞ ለቤተሰቦቹ ሁለት ሚልየን ብር እንደሚሰጥ ቃል እገባለው" አለ...

ለረዥም ሰአት ደፍሮ ሀይቁ ውስጥ የገባሰው አልታየም በመሀል ሳይታሰብ አንድ ሰው ወደ ሀይቁ ዘሎ ገባ ከዚያም ሰውየው ከሀይቁ ለመውጣት ያለ የሌለ ሀይሉን ተጠቅሞ ተወራጨ በመጨረሻም እድለኛ ሆኖ ከሀይቆ ወጣ
እንደወጣም ትንፋሹ እየተቆራረጠ...

"ማማነነው የገገፈተረኝ ?" ብሎ ጠየቀ
ሁሉም ወደሚስቱ ጠቆሙት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዝነኛው
" ከስኬታማ ወንድ ጀርባ አንድ ሴት አለች" የሚለው አባባል ተፈጠረ

መልካም ቀን

@lifein1553