Get Mystery Box with random crypto!

ግሩም አባባሎች 'ያለምክንያት የሚወድህን አምላክ እያሰብክ ያለምክንያት የሚጠሉህን ሰዎች እርሳቸው | 15:53

ግሩም አባባሎች

"ያለምክንያት የሚወድህን አምላክ እያሰብክ ያለምክንያት የሚጠሉህን ሰዎች እርሳቸው።"

"እያንዳንዱ ቀን ትንሽ ህይወት ነው ከእያንዳንዱ ህይወት ቀን ጀርባ አዲስ ህይወት አለ፣እያንዳንዱ ጠዋት ትንሽ ወጣት እያንዳንዱ የሌለት እንቅልፍ ትንሽ መሞት ነው።"
አርተር ሾፐን ሀወር


"ፍቅርን ማያዉቁ ሰዎች ፍቅር እዉር ነዉ ይላሉ፤ እኔ እላለሁ አይን ያለዉ ብቸኛ ነገር ፍቅር ብቻ ነዉ፤ ከፍቅር ዉጭ ሁሉንም ነገር እዉር ነዉ።"
ኦሾ

"የተሳሳቱ ሰዎች ሃይማኖትን በተሳሳተ መንገድ ይጠቀማሉ ፡፡ በዚህ ምክንያት ሃይማኖት ለላቀ ተጋድሎ እና ለከፋ መከፋፈል አስተዋጽኦ ያደርጋል ፡፡"
ዳላይ ላማ

"ዛሬን ለሰይጣን ነገን ደግሞ ለእግዚአብሔር አትስጡ።"
ቅዱስ ጎሮጎርዮስ

"ጥሩ ምላስ ስውር ማህተብ ያላት የዘመኑ ሰርተፊኬት ናት"

"መስታወቱን መስበር ከፊቱ የቆመውን እውነት አይቀይረውም"

" ጨዋ ሰው በሌሎች ሰዎች መጎሳቆል ላይ የራሱን ምቾት አይገነባም እርሱ የሌሎችን ሰዎች ምቾት ለማደላደል የራሱን ምቾት ይረሳልና "
አቡነ ሺኖዳ

"ህይወትህ ቀላል እንዲሆንልህ አትፀልይ፡፡ ጥንካሬ እንድታገኝ ፀልይ እንጂ፡፡ በአቅም ልትሰራው የምትችለውን ነገር ለማግኘት አትፀልይ፡፡ ልትሰራው ካሰብከው ነገር ጋር የሚመጣጠን ሀይልን እንድታገኝ ፀልይ፡፡ከዚያ አስደናቂው ነገር 'የሰራህው ስራ' ሳይሆን 'አንተ' ትሆናለህ፡፡"
ፊሊፕ ብረክስ

."በዓመቱ ውስጥ ምንም ሊከናወን የማይችልበት ቀን ሁለት ቀናት ብቻ ናቸው ፡፡ አንደኛው ትናንት ሌላኛው ደግሞ ነገ ይባላል ፡፡ ዛሬ ለመውደድ ፣ ለማደግ እና ከሁሉም በላይ ለመኖር ትክክለኛው ቀን ዛሬ ነው።"
ዳላይ ላማ

የስብዕና ልህቀት
@lifein1553