Get Mystery Box with random crypto!

ሮ አዳምን እንዳሳተው ሁሉ ክርስቶስም ደካማውን የአዳምን ሥጋ ለብሶ በደካማነቱ ቢጠጋው ድል እንደነ | የአህዛብና የመናፍቃን ጥያቄዎችና መልሶቻቸው!!

ሮ አዳምን እንዳሳተው ሁሉ ክርስቶስም ደካማውን የአዳምን ሥጋ ለብሶ በደካማነቱ ቢጠጋው ድል እንደነሳው ለማስተማር ነው።

፪. “አባ ሥረይ ሎሙ እስመ በዘኢየአምሩ ይገብሩ” (አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው) ሉቃ ፳፫፡፳፬ ጌታችን ይህንን ማለቱ የበደሉንን ይቅር ማለትን ሲያስተምር እና ከስቅለቱ ሳያውቁ የተሳተፉም ስለነበሩ እና አሉና እነሱን ከስቅለቱ ሲለይ ይህንን ተናገረ።

፫. “ዮም ትሄሉ ምስሌየ ወስተ ገነት” (ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ) ሉቃ ፳፫፡፴፫ ይህንንም የተናገረው በቀኙ የተሰቀለው ወንበዴ የጌታችንን የባህርይ አምላክነት አምኖ “በመንግስትህ አስበኝ” ቢለው እሱም ከሁሉ ቀድሞ ገነት የመግባት እድልን ሲያጎናጽፈው ነው።

፬. “አባ አመሐፅን ነፍስየ ውስተ እዴከ” (አባት ሆይ ነፍሴን በ እጅህ አደራ እሰጣለሁ) ሉቃ ፳፫፡፵፮

፭. “ነዋ ወልድኪ ነያ እምከ” (እነሆ ልጅሽ እነኋት እናትህ) ዮሐ ፲፱፡፳፮-፳፯ በዚህም ጌታችን ለደቀ መዝሙሩ እመቤታችንን እናት አድርጎ ሲሰጠው ለሁላችንም እናት እንድትሆነን መስጠቱን ሲያጠይቅ ነው።

፮. “ከመ ይብጻሕ ቃለ መጽሐፍ ዘይቤ ጻማዕኩ” (መጽሐፍ በመብሌ ውስጥ ሐሞት ጨመሩበት) መዝ ፷፰፡፳፩ ይህም የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ ተጠማሁ አለ። የሰቀሉትም መራራ ሀሞትን እና ኮምጣጤን ይጠጣ ዘንድ ሰጡት ዮሐ ፲፱፡፳፰።

፯. “ወይቤ ተፈጸመ ኩሉ” የተነገረው ተስፋ የመሰለው ምሳሌ የተተነበየው ትንቢት ደረሰ ተፈጸመ ሲል ተፈጸመ አለ። ዮሐ ፲፱፡፴።
ከዚህ በኋላ ቅድስት ነፍሱ ከቅዱስ ሥጋው ስትለይ አምላክነቱን ለመግለጽ በምድር አራት በሰማይ ሦስት ተአምራት ታይተዋል ፡፡
እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፦

በምድር
፩-የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀደደ፣
፪-ምድር ተናወጠች፣
፫-አለቶች ተሰነጣጠቁ፣
፬-መቃብሮች ተከፈቱ ፣ ሙታን ተነሱ። ማቴ27፤51-53
በሰማይ
፩- ፀሐይ ጨለመች፣
፪-ጨረቃም ደም ሆነች፣
፫-ከዋክብት እረገፉ። ማቴ ፳፯፡፴፭
አስራ አንድ ሰዓት ጌታ ወደ መቃብር ወረደ ተቀበረ ጌታን የሰቀሉት አይሁድ የፋሲካ በዓላቸው ቀርቦ ነበር እና ሥጋቸው በመስቀል እንዳይውል የሰቀሏቸውን ሰዎች ጭናቸው ተሰብሮ እንዲሞቱ ጲላጦስን ለመኑት እርሱም ፈቀደላቸው። ጌታን ሊሰብሩት ሲመጡ ሞቶ አገኙት በዚህ ጊዜ ሌንጊኖስ የሚባል ወታደር መሞቱን ሊያጣራ ጎኑን በጦር ቢወጋው ከጎኑ ደምና ውሃ ፈሰሰ ይህም የምንጠመቅበት ማየ ገቦ ነው። በሥውር የጌታ ተማሪ የሆኑት የአርማትያሱ ዮሴፍና የአይሁድ አለቃ ኒቆዲሞስ ጲላጦስን ለምነው በማስፈቀድ እንደ አይሁድ የአገናነዝ ሥርዓት የጌታን ሥጋ በሽቶ ጋር በተልባ እግር አልብሰው “ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት” እያሉ ገንዘው ማንም ባልተቀበረበት አዲስ መቃበር ቀበሩት። ምነው ቅዱሳን ነቢያት ባረፉበት መቃበር ያልተቀበረ ቢባል ኋላ በትንሳኤው ሲነሳ የነቢያት አጽም አስነሳው (ለምሳሌ ያህል የነቢዩ ኤልሳዕ አጥንት ሙት አስነስቷል ፪ ነገሥ ፲፫፡፳፩) እንጂ መቼ በሥልጣኑ ተነሳ ብለው አይሁድ ይሞግቱ ነበር እና እንዲያ እንዳይሉ በአዲስ መቃበር ተቀበረ። ማቴ ፳፯፡፶፯-፷፩ ፤ ማር ፲፭፡፵፪-፵፯ ፤ ሉቃ ፳፫፡፶-፶፮ ፤ ዮሐ ፲፱፡፴፪-፵።
በዕለተ ስቅለት በጸሎታችን ወቅት ሲባል እንደሰማችሁት “ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ” ሞትን በሥጋው ቀመሰ። የማይሞተው ሞተ። በቀራንዮ የተከፈለልንን ዋጋ እያሰብን እንደቃሉ እንኖር ዘንድ፣ ከበደል እና ከኃጢአት ተጠብቀን በንስሐ ነጽተን፣ በቅዱስ ሥጋው እና ክቡር ደሙ ዘለዓለማዊ ሕይወትን እናገኝ ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን።