Get Mystery Box with random crypto!

የአህዛብና የመናፍቃን ጥያቄዎችና መልሶቻቸው!!

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidestaresema — የአህዛብና የመናፍቃን ጥያቄዎችና መልሶቻቸው!!
የቴሌግራም ቻናል አርማ kidestaresema — የአህዛብና የመናፍቃን ጥያቄዎችና መልሶቻቸው!!
የሰርጥ አድራሻ: @kidestaresema
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.52K
የሰርጥ መግለጫ

☞ በዚህ ቻናላችን የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን በቤተክርስቲያናችን የሚነሱ ጥያቄዎች በመናፍቃን በአህዛብ የሚጠየቁትን በአጠቃላይ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ የሚነሱትን ጥያቄዎች የማያዳግም መልስ መልሰን ለኦርቶዶክሳውያንና ለህዝቡ መልስ የምንሰጥ ይሆናል! #join & #share
ለግሩፕ 👉 @kidestaresema6
ለቻናል 👉 @kidestaresema
ለማንኛውም ጥያቄ 👉 @tiotokos_bot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-09 22:56:42
...............በዚህ ቻናል ውስጥ............

አዳዲስ እና ቆየት ያሉ ልብን የሚገዙ ለንስሃ የሚያበቁ ለፀሎት የሚያነሳሱ መዝሙሮች ያገኙበታል

መንፈሳዊ ትምርቶች የአበው ቅዱሳን ምክሮች እና አስተምሮዎች የተጋድሎ ጥበብ የህይወት ታሪክ

እንዲሁም የዜማ መሣሪያ ድህፆ ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ለሚኖሩ የዜማ መሳሪያ ፈላጊዎች በሙሉ ለሀገር ውስጥ በገና ክራር መሰቆ እኛጋ ማግኘት ይችላሉ።

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ


https://t.me/+arFiCwCIAVs1M2Jk
https://t.me/+arFiCwCIAVs1M2Jk
https://t.me/+arFiCwCIAVs1M2Jk


ከስር ባለው ስልክ ቁጥር ልታገኙን ትችላላችሁ

0901570787
23 viewsመንፈሳዊ 1K, 19:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-12 22:10:11 በኢትዮጵያ የተሰወሩ ፒራሚዶች ያሉበት ቦታ ታወቀ !



እነዚህ ፒራሚዶች እና ቤተ መቅደሶች የሚገለጡበት ዘመን ታወቀ


እውነት በኢትዮጵያ መሬት በሰማያዊ ሀይል ተቀብረው የሚገኙ ፒራሚዶች እና ቤተ መቅደሶች አሉ ? እንዴትስ ተሰሩ ?

ስለ እነዚህ ፒራሚዶችና ቤተመቅደሶች አስገራሚ ምስጢሮች


በቅዱሳን አባቶቻችን ስለተሰወረው ድንቅ መፅሐፍ


እነዚህን እና ሌሎች ሚስጢራትን ስለ ኢትዮጵያ ስውር ቤተ መቅደሶች እንዲሁም ፒራሚዶች ማወቅ ከፈለጉ በ Youtube ቻናላችን ሙሉ ትምህርቱን ማግኘት ትችላላቹ ከስር ያለውን Open የሚለውን ተጭነው ! እንዲሁም ሌሎች ድንቅ ፕሮግራሞችንም ማግኘት ይችላሉ በዛውም የ Youtube ቻናላችንንም Subscribe ያርጉ !




ይህን ይጫኑት ... ይህን ይጫኑት
.
█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
4.6K viewsመንፈሳዊ 1K, 19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-22 09:30:35 የአህዛብና የመናፍቃን ጥያቄዎችና መልሶቻቸው!! pinned «አጭር መልእክት ሰላም ለእናንተ ይሁን የተዋህዶ ልጆች እንዴት ከርማችዋል እንዴትስ ሰንብታችዋል እግዚአብሔር ይመስገን እኛ ደህና ነን በዚህ ቻናላችን ላይ እየለቀቅን አይደለም ያው በጉዳዮች ምክኒያት ስላልተመቸን ነው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለጠየቃችሁት ጥያቄዎች በሙሉ ምላሽ ይዘን ከሕማማት በኋላ የምንመለስ ይሆናል እስከዛ ግን እስካሁን የተመለሱ ምላሾችን በመመልከት ራሳችሁን እንድታጸኑ ስንል እናሳስባለን።…»
06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-09 09:08:44 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! ክርስቶስ ተንስአ እሙታን በዓብይ ዐይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደቷ ቀን መታሰቢያ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!! #እስኪ_ስለ_ልደታ_ለማርያም_የሆነ_ነገር_እንበላችሁ!! #የግንቦት ልደታ በዓልና "ባዕድ አምልኮ" ግንቦት…
10.9K viewsMicky, 06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-09 09:08:36
ልደትሽ ልደታችን ነው

''ዮም ፍስሃ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም'''
እንኳን አደረሳችሁ
8.4K viewsMicky, 06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-09 09:08:36
7.6K viewsMicky, 06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-09 09:08:12 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
በዓብይ ዐይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም እምይዜሰ ኮነ
ፍስሐ ወሰላም

ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደቷ ቀን መታሰቢያ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!!

#እስኪ_ስለ_ልደታ_ለማርያም_የሆነ_ነገር_እንበላችሁ!!

#የግንቦት ልደታ በዓልና "ባዕድ አምልኮ"

ግንቦት የሚለው ቃል የግእዝ ቃል ሲሆን “ገነበ” ከተባለ ግስ የወጣ ነው፡፡ ትርጉሙም ገነባ ግንብ ማለት ነው፡፡የግንቦት ወር አንድም የክረምት መግቢያ የክረምት ጎረቤት ይባላል፡፡ ይህ ወር የእመቤታችንን ልደት ጨምሮ ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት፣ጠቢቡ ሰሎሞን ጻድቁ ኢዮብ ሐዋርያው ቅዱስ
ቶማስ ንግስት እሌኒ አቡነ ይምዓታ ያረፉበትና ከአምላካችን ዐበይት በዓላትም መካል ሁለቱ በዓለ እርገትና በዓለ ጰራቅሊጦስ የሚውሉበት ታላቅና የተባረከ ወር ነው፡፡

በሀገራችንም ታሪክ በአፄ ዮሐንስ ዘመን በወሎ ቦሩ ሜዳ ቅባትና ፀጋ ከተባሉ የመናፍቃን ቡድኖች ጋር ሃይማኖታዊ ክርክር የተካሄደበት ወር ነው፡፡ ይሁንና ጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ በነዚህ ታላላቅ በዓላትን በያዙ ታሪኮች ተገን አድርጎ ሃይማኖታዊ እውቀት ብዙም የሌላቸውን ሰዎች ሲያስት ይስተዋላል፡፡ በተለይ በእመቤታችን የልደት ቀን ሰበብ ስለበዓሉና ትውፊታዊ አከባበሩ ምንም ግንዛቤ የሌላቸው ወገኖች በዓሉን ከባዕድ አምልኮ ጋር በማቆራኘት የማይገባ ነገርን እንዲፈጽሙ ያደርጋቸዋል፡፡

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትዉፊት መሰረት ሐና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ፡፡ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ይህንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡

ነገር ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መካከል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳዊ በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ (የእመቤታችን የልደት በዓል) ነዉ፡፡ በዚህ ዕለት አንዳንዶች ባለማወቅ ሌሎች ደግሞ በድፍረት ‹‹ለአድባር አዉጋር ነዉ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ›› እያሉ ለማያውቁት አምልኮ ንፍሮ የሚበትኑ ቡና የሚረጩ ቅቤ የሚቀቡ የከብት ደም የሚያፈሱ አሉ፡፡

እውነታው እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን እነዚህን የሃይማኖት ለዋጮች ሥራቸውን እንጸየፋለን፡፡ ስለሆነም ከእንደዚህ ዓይነቱ ባዕድ አምልኮ በመለየት ይህንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር ልናከብረው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሰረት በቀናች በተዋሕዶ እምነት ሆነን በምሕረቱ የጎበኘንን
አምላካችንን ብቻ እያመለክን የድኅነታችን ምክንያት የሆነችውን ድንግል ማርያምን እያመሰገንን ልናከብረው ይገባል፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤቷን ፍቅሯን ያሳድርብን!!

ይቆየን!!

@kidestaresema
@kidestaresema
@kidestaresema
8.4K viewsMicky, 06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-30 14:14:43
6.9K viewsMicky, 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-30 14:14:40
5.3K viewsMicky, 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-30 11:06:20 የእመቤታችን ለቅሶ

ልመናዋ ክብሯ ለዘላለሙ ከእኛ ጋር ይኑርና ፤ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምኖ የብህንሳ ኤጲስ ቆጶስ አባ ሕርያቆስ ድንግል ማርያም እመቤታችን ስላለቀሰችው ልቅሶ በዛሬው ቀን የደረሰው ይህ ነው አሜን።

ወደ ዮሐንስ ቤትም በደረሰች ጊዜ አልዘገየችም ወደቀራንዮ ተመልሳ ልትሄድ የተወዳጅ ልጅዋን የመከራውን ፍጻሜ ታይ ዘንድ ቸኮለች እንጂ። በመስቀል ላይ ነፍሱን በፈቃዱ ሰጥቶ ዝም በአለ ጊዜ በምድር ላይ ስለሆነው ንውጽውጽውታና በሰማይም ስለተደረጉ አስደናቂ ተአምራቶች ሀገሪቱ ሁሉ ተሸበረች ፤ ድንግል እመቤታችንም ምድር ስትናወጽ ጨለማም በምድር ሁሉ ስትሰለጥን አይታ እነሆ እነዚህ ተአምራቶች የልጄ የሞቱ ምልክቶች ናቸው ብላ ጮኸች።

እንዲህ ስትልም ዳግመኛ ዮሐንስ ደርሶ
እያለቀሰ ከእርሷ ዘንድ ቆመ።
ድንግል እመቤታችንም ዮሐንስ ሆይ በመስቀል ላይ ልጄ በእውነት ሞተን? አለችው።እርሱም ራሱን ዝቅ አድርጎ እናቴ ሆይ አዎን ሞተ አላት።

ከዚህም በኋላ ታላቅ ልቅሶ ሆነ በዚያችም ሰዓት ድንግል እመቤታችንን ፍጹም ጩኸትና ልቅሶ ጸናባት ፤ በመረረ ልቅሶም እየጮኸች ልጄ ሆይ ከዚህ ካገኘህ የሞት ፃዕር የተነሣ ግፌን የሚመለከትልኝ ሹም ወይም በሐዘን የተሰበረውን ልቤን አይቶ በማስተዋል የሚፈርድልኝ ዳኛ አላገኘሁም አለች። መኮንን ሆይ እንደ ሕጉ የምትፈርድስ ቢሆን ኖሮ ንጉሥ ልጄን እንደራበው እንደጠማው የአይሁድ ወገኖች ባልሰቀሉትም ነበር።

አንተም ሊቀ ካህናት በዕውነት ፈራጅ ብትሆን ባርያ በጌታው ፈንታ መሞት በተገባው ነበር።ቨሹም ሆይ በቅን የምትፈርድ ብትሆን ልጄን በበርባን ፈንታ ባልሰቀልከውም ነበር። አንተም ሊቀ ካህናት በዕውነት የምትፈርድ ብትሆን ከልጄ ይልቅ ይሁዳ ለሞት የተገባ በሆነ ነበር።

ሹም ሆይ ፍርድን የምታውቅ ቢሆን ልጄን ሥጋውን አራቁተህ መስቀል ባልተገባህም ነበር። ሊቀ ካህናት ሆይ በቅን የምትፈርድ ብትሆን ወንበዴውን አድነህ ጻድቁን ባልገደልከውም ነበር።
ዳኛ ሆይ መልካም ፍርድን የምታውቅ ብትሆን ኑሮ ጦሮች በላይህ ላይ ሲያንጃንብቡ ጽኑዕ የሆነውን ባልገደልከውም ነበር። አንተም ሊቀ ካህናት በቅን የምትፈርድ ብትሆን የጌታህን ፊት ባፈርክ ነበር።

እኔ ስለጦርነት ሰልፍ ስሰማ የንጉሥ ልጅ በጦርነቱ ውስጥ የተያዘ እንደሆነ እንዳይሞት ስለእርሱ እጅግ በርትተው እየተዋጉ ወደ አባቱ በፍጹም ጌትነትና ክብር እስከ አደረሱት ድረስ ይጠብቁታል።

ሊቀ ካህናት ሆይ ለምን እንዲህ ሆነ ብለህ በጠየቅኸው ጊዜ ዕውነቱን አስረዳህ ፤ ግን በአንተ ዘንድ የተጠላ ሆነ። ሐሰትን ወደድክ ፤ እምነትህንም በሐሰቱ ላይ አጸናህ ፤ እንግዲህ ከእውነተኛው ከእርሱ በስተቀር ማንን ትጠይቃለህ።

በፊትህ የቆመው እርሱ እውነተኛ እንደሆነ አታውቅምን? እርሱም በእውነት ሕይወት ነው።

ንጽሕት ድንግል ሆይ በኢየሩሳሌም ከተማ በዚህ ትውልድ መካከል የሆነውን ታላቅ ግፍ እዪ ፤ እነሆ ከእነርሱ በሚበልጠው ላይ ተሰብስበው ለሞት ፍርድ ሰጥተውታልና። ከዚህ ሁሉ በኋላ ክርስቶስ በመስቀል ላይ እንደሆነ ነበር ፤ የመቶ አለቃውም በዕውነት ይህ ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ አመነ ፤ እሊህ ተአምራቶቹ በሁሉ ዘንድ ታመኑ።
በዕንጨት መስቀል ላይ ሳለ ምእመናን ሁሉ በአንድነት አለቀሱለት።

ስለ ጌታ ስቅለት ከሄሮድስ ዘንድ ወደ መጣው የመቶ አለቃ ጲላጦስ ልኮ አስመጥቶ ወደ ቤቱ አስገብቶ ወንድሜ ሆይ ይህን ጻድቅ ሰው አይሁድና ሄሮድስ ያደረጉትን አየህን? ይህ ሁሉ ተአምራት በምድር እስኪሆን ድረስ በግፍ ሰቀሉት።
ወንድሜ ሆይ በእውነት እነግርሃለሁ ፤ እነዚህ ክፋቶች ሁሉ የተፈጸሙት በሄሮድስ ምክር እንጂ በእኔ ፈቃድ አይደለም ፤ እኔ እንዳይሞት ልተወው ወደድኩ ፤ ነገር ግን ሄሮድስ በዚህ ደስ እንደማይለው ባየሁ ጊዜ ይሰቅሉት ዘንድ ለአይሁድ ሰጠኋቸው እንጂ።

ተመልከት አሁን ለእግዚአብሔር ስለሰቀልነው ልጁ ምን ብድርን እንከፍለዋለን? አለው ፤ የመቶ አለቃውና ባለጦሩ ከጲላጦስ ጋር ደሙ በሄሮድስና በካህናት አለቆች ላይ ነው እያሉ መራራ ልቅሶ አለቀሱ። በዚያን ጊዜ ጲላጦስ ልኮ የካህናት አለቆች ቀያፋና ሐናን ወደ ጉባዔው አስጠርቶ እናንተ በግፍ ደምን የምትጠጡ ተኵላዎችና ቀበሮዎች በዕንጨት መስቀል ላይ ወደሞተው የናዝሬት ሰው አሁን ተመልከቱ ደሙም በእናንተና በልጆቻችሁ ላይ ይሁን አላቸው።

እነርሱ ግን ደስ በመሰኘት እያፌዙ ደረታቸውን እየደቁ ፊታቸውንም እየነጩ እስከ ሽህ ትውልድ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን አሉ። ጲላጦስም ይህ ሁሉ ተአምር በሰማይና በምድር ከተገለጠ በኋላ ዛሬም ከሕዝቡ ሁሉ ጋር አትፈሩምን? ፣ አትደነግጡምን? አላቸው።

እነርሱም እንደ ሕጋችን ፈጽመናል ስለምን እንፈራለን? እንደነግጣለን? አሉት።
ጲላጦስም የሐሰት ሕግ ፈጸማችሁ እንጂ ይህ ሕግ አይደለም አለ ፤ አንተም ሊቀ ካህናት የተባልከው እነሆ ልብሶችህ ተቀደዋል። ሕጉም ሊቀ ካህናቱ ልብሶቹን በቀደደ ጊዜ ከክህነት አገልግሎት ይከልከል ይላል።

ቀያፋም እኔ ልብሴን የቀደድኩት እርሱ በእግዚአብሔርና በሕጋችን ላይ የስድብ ቃል ስለተናገረ ነው ብሎ መለሰለት።
ጲላጦስ እንግዲህ በሊቅ ካህናት ሥርዓት ወደ መቅደስ እንድትገባ አልፈቅድልህም እንደ ሕግ አፍራሽ እንጂ። አንተ ወደ መቅደስ እንደገባህ ሌላው ቢነግረኝ ቸብቸቦህን ከአንተ ላይ እቆርጣለሁ አለው።

ቀያፋም ከአንተ በፊት ብዙ ጊዜ አልፎአል ፤ ብዙዎች ሹማምንት የሚቀድሙህ አሉ እስከ ዛሬ የካህናት አለቆችን ወደ መቅደስ መግባትን የከለከላቸው አለን? ብሎ መለሰለት። ይህንም ያለ የሄሮድስን ሥልጣን በመተማመን ነበር ፤ ጲላጦስም ይህን ሁሉ ተአምር ስታይ ከሕዝቡ ሁሉ ጋር አሁንም ልብህ አያምንምን? አለው።

ሊቀ ካህናት የተባለ ቀያፋም አንተስ በዚች አገር አዲስ ተክል ነህ ይህ ምልክት የሆነበትን ነገርና የተደረገውን አታውቅም። ይህ ይቅርታ የሚደረግበት የመጋቢት ወር ፀሐይና ጨረቃ ዑደታቸውን ፈጽመው ተራክቦ የሚያደርጉበት ሲሆን በዚሁ ወር መሠርያኖች ጨረቃን እንደ ደም የሚሆንበትን ያደርጋሉ ፤ የፀሐይንም ብርሃን በሥራይ ኃይል ይስባሉ።
የአግዓዝያንንም ተግባር ይመርምራሉ ፤ የስንዴውን የወይንንና የዘይትን ፍሬዎች በማዘጋጀት ይህን የመሰለውን ቀያፋ በሐሰት ይናገር ነበር።

ጲላጦስም ከወንበሩ ላይ ተነስቶ አንተ እርሱን ከመጥላትህ የተነሣ በዓለሙ ሁሉ ላይ መዐትን ልታመጣ ትወዳለህ? ብሎ ከቆዳ በተሠራ በደረቀ በትር ደበደበው ፤ ጽሕሙንም ነጨው። የመቶ አለቃውና ባለጦሩ ከሕይወት ይልቅ ሞት ይገባሃል እያሉ ያንን ሊቀ ካህናት ይዘልፉት ነበር።
በአንድነት ከዘለፉትም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ይዘውት ሄዱ ወደ ንጉሥም ይወስዱት ዘንድ ተስማሙ።

የድንግል ማርያም በረከት የተወዳጅ ልጅዋም ምሕረት ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ይደርብን አሜን።
6.4K viewsMicky, 08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ