Get Mystery Box with random crypto!

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! ክርስቶስ ተንስአ እሙታን በዓብይ ዐይ | የአህዛብና የመናፍቃን ጥያቄዎችና መልሶቻቸው!!

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
በዓብይ ዐይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም እምይዜሰ ኮነ
ፍስሐ ወሰላም

ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደቷ ቀን መታሰቢያ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!!

#እስኪ_ስለ_ልደታ_ለማርያም_የሆነ_ነገር_እንበላችሁ!!

#የግንቦት ልደታ በዓልና "ባዕድ አምልኮ"

ግንቦት የሚለው ቃል የግእዝ ቃል ሲሆን “ገነበ” ከተባለ ግስ የወጣ ነው፡፡ ትርጉሙም ገነባ ግንብ ማለት ነው፡፡የግንቦት ወር አንድም የክረምት መግቢያ የክረምት ጎረቤት ይባላል፡፡ ይህ ወር የእመቤታችንን ልደት ጨምሮ ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት፣ጠቢቡ ሰሎሞን ጻድቁ ኢዮብ ሐዋርያው ቅዱስ
ቶማስ ንግስት እሌኒ አቡነ ይምዓታ ያረፉበትና ከአምላካችን ዐበይት በዓላትም መካል ሁለቱ በዓለ እርገትና በዓለ ጰራቅሊጦስ የሚውሉበት ታላቅና የተባረከ ወር ነው፡፡

በሀገራችንም ታሪክ በአፄ ዮሐንስ ዘመን በወሎ ቦሩ ሜዳ ቅባትና ፀጋ ከተባሉ የመናፍቃን ቡድኖች ጋር ሃይማኖታዊ ክርክር የተካሄደበት ወር ነው፡፡ ይሁንና ጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ በነዚህ ታላላቅ በዓላትን በያዙ ታሪኮች ተገን አድርጎ ሃይማኖታዊ እውቀት ብዙም የሌላቸውን ሰዎች ሲያስት ይስተዋላል፡፡ በተለይ በእመቤታችን የልደት ቀን ሰበብ ስለበዓሉና ትውፊታዊ አከባበሩ ምንም ግንዛቤ የሌላቸው ወገኖች በዓሉን ከባዕድ አምልኮ ጋር በማቆራኘት የማይገባ ነገርን እንዲፈጽሙ ያደርጋቸዋል፡፡

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትዉፊት መሰረት ሐና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ፡፡ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ይህንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡

ነገር ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መካከል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳዊ በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ (የእመቤታችን የልደት በዓል) ነዉ፡፡ በዚህ ዕለት አንዳንዶች ባለማወቅ ሌሎች ደግሞ በድፍረት ‹‹ለአድባር አዉጋር ነዉ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ›› እያሉ ለማያውቁት አምልኮ ንፍሮ የሚበትኑ ቡና የሚረጩ ቅቤ የሚቀቡ የከብት ደም የሚያፈሱ አሉ፡፡

እውነታው እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን እነዚህን የሃይማኖት ለዋጮች ሥራቸውን እንጸየፋለን፡፡ ስለሆነም ከእንደዚህ ዓይነቱ ባዕድ አምልኮ በመለየት ይህንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር ልናከብረው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሰረት በቀናች በተዋሕዶ እምነት ሆነን በምሕረቱ የጎበኘንን
አምላካችንን ብቻ እያመለክን የድኅነታችን ምክንያት የሆነችውን ድንግል ማርያምን እያመሰገንን ልናከብረው ይገባል፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤቷን ፍቅሯን ያሳድርብን!!

ይቆየን!!

@kidestaresema
@kidestaresema
@kidestaresema