Get Mystery Box with random crypto!

ዕለተ አርብ ዓርብ ነግህ(ከጠዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት)ጌታ ለፍርድ ቀረበ የዓለሙ ሁሉ ፈጣሪ የዓለ | የአህዛብና የመናፍቃን ጥያቄዎችና መልሶቻቸው!!

ዕለተ አርብ

ዓርብ ነግህ(ከጠዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት)ጌታ ለፍርድ ቀረበ

የዓለሙ ሁሉ ፈጣሪ የዓለሙ ፈራጅ እውነተኛው ዳኛ ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ በሐሰት ተከሶ ለፍርድ በጲላጦስ አደባባይ ችሎት ቆመ። ጲላጦስም ጌታን መርምሮ ለሞት የሚያበቃ አንዳች ጥፋት ቢያጣበት ሊፈታው ፈለገ። ከሳሾቹ ግን ጌታን ስቀለው ወንጀለኛውን በርባንን ፍታልን ብለው ጮሁ። የጲላጦስ ሚስት የነበረችው አብሮቅላ ግን በህልም ብዙ መከራ እና ስትቀበል ስታይ አድራለችና ለባሏ በዚህ ሰው ላይ አንዳች ክፉ ነገር እንዳታደርግ ብላ መልዕክት ለባሏ ላከችበት። በፈራጅነት የተቀመጠው ጲላጦስም ክርስቶስ የገሊላ ሰው መሆኑን ሲረዳ ጌታችንን በጊዜው የገሊላ ገዥ ወደ ሆነው ሄሮድስ እንዲሄድ አደረገው። ጲላጦስና ሄሮድስ በሥልጣን ዘመናቸው እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ፣ እኔ ልግዛ እኔ ልግዛ እያሉ በዳኝነት ይጣሉ ነበር አሁን ግን በጌታ ሞት የተነሳ ሁለቱ የሥልጣን ጥመኛ ጠላቶች ታረቁ። ሄሮድስም ጌታን ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው። ለእስራኤላውያን የፋሲካ በዓል ከግብጽ ባርነት ነጻ የወጡበት መታሰቢያ ነውና በየዓመቱ የሚፈልጉትን እስረኛ ሊፈታላቸው ልማድ ስለነበራቸው በርባን የተባለውን ወንበዴ እንዲፈታላቸው ጠየቁት እርሱ ግን ኢየሱስን ልፍታላችሁ ወይስ በርባንን ቢላቸው ወንበዴዎን በርባንን መረጡ። ወንበዴው በርባን ከእስር ተፈትቶ ንፁሁ ጌታ ታስሮ ለሞት መዳረጉ ጌታ ስለበደለኞች ስለኃጢአተኞች ሊሞት እና የነሱ እጣ የሆነውን ቅጣት እና መከራ ሊቀበል የመጣ መሆኑን የሚያጠይቅ ነው። (ማቴ ፳፯፡ ፩-፲ ማር ፲፭፡፩-፭ ፤ ሉቃ ፳፫፡ ፩-፶፮ ዮሐ ፲፰፡ ፳፰-፴፰)

ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጌታ ተገረፈ

ጲላጦስም ጌታን መርምሮ አንዳችም ለሞት የሚያበቃ በደል አላገኘበትም። እሱም ሊፈታው ፈለገ ህዝቡ ግን “ስቀለው ስቀለው” እያሉ አብዝተው ጮሁ። ጲላጦስም ምናልባት ቢገረፍ እሱ ይበቃዋል ብለው ይገደል የሚለውን ጥያቄያቸው ይተዋሉ ብሎ በማሰብ ለመገረፍ አሳልፎ ሰጠው። በልማዳቸው የተገረፈ አይሰቀልም እና። እነርሱ ግን ልባቸው በጭካኔ የደነደነ ነበር እና እየተፈራረቁ ክንዳቸው እስኪዝል ድረስ አርባ ብቻ ሊገረፍ የተፈረደበትን ቁጥር ያሳሳቱ በማስመሰል ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪታይ ድረስ ስድስት ሺህ ስድሥት መቶ ስልሳ ስድስት (፮፼፮፻፷፮) ጊዜ ገረፉት። ጌታ እንዲሰቀል የህዝቡ ጩኸት በበረታ ጊዜም ጲላጦስ ከዘመኑ ንጉስ ከቄሳር ጋር እንዳያጣሉት ለሥልጣኑ በመስጋት እኔ ከደሙ ንጹህ ነኝ ብሎ በውሃ እጁን ታጠበና ጌታን እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው።(ማቴ ፳፯፡፳፬-፳፮ ፤ ማር ፲፭፡፮-፲፭ ፤ ሉቃ ፳፫፡፩-፳፮ ፤ ዮሐ ፲፰፡፳፰-፴፰)።

እኩለ ቀን - ከቀኑ ስድስት ሰዓት ጌታ ተሰቀለ

ለዝንተ ዓለም መላእክት፣ ሊቃነ መላእክት፣ ሱራፌል እና ኪሩቤል ሳያቋርጡ ምስጋና የሚያቀርቡለት ንጉሥ የክፉዎች አይሁድ መዘበቻ ሆነ። ቅዱሳን መላእክት በፍርሐት የሚሰግዱለትን ጌታ በመቃን ራሱን መቱት። መጀመሪያ ለመዘባበት ሲሉ ያለበሱትን ቀይ ግምጃ ገፈው አውልቀው ወደሚሰቅሉበት ቀራንዮ ተራራ ከባድ እጸ መስቀል አሸክመው እያዳፉ ወሰዱት። ከባዱን ዕፀ መስቀል መሸከሙ ከባዱን ኃጢአታችንን እንደተሸከመልን የሚያጠይቅ ነው ቅዱስ ጴጥሮስ “ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ” እንዳለ ፩ኛ ጴጥ ፪፡፳፪።
ስምዖን የተባለውን የቀሬና ሰው በመንገድ አገኙትና የጌታን መስቀል ይሸከም ዘንድ አስገደዱት (ማቴ ፳፯፡፴፪)። የስምዖን መሸከም ግን ጌታ ከመስቀሉ በረከት እንዲሳተፍ ስለፈለገ ነው።
ጌታን ወንበዴ ነው ብለው ስሙን ለማጥፋት እንዲመቻቸው በሰው አመለካከትም ወንበዴውን ነው የሰቀሉት እንዲባል ስለፈለጉ ንፁሁን ሥጋን የተዋሐደ አምላክ በሁለት ወንጀለኛ ወንበዴዎች መካከል እንዲሰቀል አደረጉት። ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ “ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥” (ኢሳ ፶፫፡፲፬) ያለው ይፈጸም ዘንድም ጌታ በፈያታዊ ዘየማን እና በፈያታዊ ዘጸጋም መካከል ተሰቀለ።
ጌታችን በፍጹም ያፈቀረውን የሰውን ልጅ ከመራራው የኃጢአት ሞት ሊያድነው ፍቅር አስገድዶት መጥቷልና ዕጸ በለስ ለመብላት የተዘረጉ የአዳም እጆችን ወደ እጸበለስ የገሰገሱ የአዳም እግሮችን ለመቤዠት ሲል እጆቹን እና እግሮቹን በችንካር ተቸነከረ። የበለስ ፍሬን በመብላት አዳም የተጎነጨውን መራር ሞት ለማጠየቅ ጌታ ውሃ ጠማኝ ብሎ ቢጠይቅ የሰጡትን መራር ሆምጣጤ እና ሀሞት ቀመሰ።
ጲላጦስም አይሁድ በቅንዓት ለሞት አሳልፈው ጌታን እንደሰጡት ያውቅ ነበር እና “ይህ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው” የሚል የክሱን ጽሕፈት ከራሱ በላይ በሦስት ቋንቋ በጽርዕ (ግሪክ) ፣ በዕብራይስጥ ፣ በሮማይስጥ በመጻፍ እንዲቀመጥ አስደረገ። ማቴ ፳፮፡፴፯ ፤ ማር ፲፭፡፳፯ ፤ ሉቃ ፳፫፡፴፰ ፤ ዮሐ ፲፱፡፲፱-፳፪።

ዘጠኝ ሰዓት ጌታ በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ለየ - ሞተ

ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስራ ሦስት ሕማማተ መስቀልን ከተቀበለ በኋላ የሰው ልጅ ባለመታዘዝ ያጣውን ሕይወት በሞቱ ለመካስ መራራ ሞትን በፈቃዱ ተቀበለ። ነቢዩ በኢሳይያስ “የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል? በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል። መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም። የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም። በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ። ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።” የተባለው ይፈጸም ዘንድ (ኢሳ ፶፫፡፩-፱) ይህ ሆነ። ጌታም “መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።” (ዮሐ ፲፡፲፬-፲፭) ያለው ፈጸም ዘንድ ስለበጎቹ መልካም እረኛ ነፍሱን ሰጠ በሞቱ ሞታችንን ለወጠ። ጌታም ነፍሱን ከሥጋው በፈቃዱ ሲለይ “አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ።”” ይህንንም ብሎ ጌታ በፈቃዱ የሞት ጽዋን ጠጣ።
ጌታችንም ነፍሱ አሳልፎ ከመስጠቱ አስቀድሞ ሰባቱን አጽርሐ መስቀል ተናግሯል። ሰባቱ አጽርሐ መስቀል ወይንም ሰባቱ በመስቀል ላይ የተናገራቸው ከዚህ የተከተሉት ናቸው፡

፩. “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ” (አምላኬ ለምን ተውኸኝ) ማቴ ፳፯፡፴፮ ጌታችን እንዲህ ማለቱ እርሱ ደካማ ስለሆነ ወይንም በደካማነት ወይም መለኮት ስለተለየው ሳይሆን ለኛ አብነት ይሆነን ዘንድ መከራ ሲገጥመን ምን ብለን መለመን፣ መማጸን፣ መጸለይ እንዳለብን ለማስተማር ነው። አንድም ጠላት ዲያብሎስ በአካለ ከይሲ ተሰው