Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ክብሮም

የቴሌግራም ቻናል አርማ kebrom01 — ዘማሪ ክብሮም
የቴሌግራም ቻናል አርማ kebrom01 — ዘማሪ ክብሮም
የሰርጥ አድራሻ: @kebrom01
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 224

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-01-06 20:03:43
73 views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 20:03:39 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
"ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ። ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ።" ሉቃ 2፥11
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
መላው ኦርቶዶክሳውያን ይህ በዓለ ልደተ እግዚእ ታላቅ በዓል እንደመሆኑ መጠን በዓሉን ስናከብር በዓሉ የሰላም፣ እርቅ፣ የፍቅር፣ የስጦታ የምስጋና መሆኑን በመረዳት በሁከት ሳይሆን በሰላም፣ ጥላቻ ሳይሆን በፍቅር፣ በስስት ሳይሆን በስጦታ፣ በመገፋፋት ሳይሆን በመረዳዳት፣ በዘፈን ሳይሆን በማኅሌት በቅዳሴ በምሥጋና ልናከብር ይገባል፡፡
መልካም በዓል ያድርግልን ያድርግላችሁ
፧፧፧፧፧፧፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
72 views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 11:52:41
46 views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 11:52:38 በመጨረሻም
በተከሠተው አለመግባባት በአጠቃላይ በሕዝባችን ላይ የደረሰው ስብራት ከባድ በመሆኑ የዓለም ማኅበረ ሰብ የተቻለውን ድጋፍ ሁሉ በማድረግ ሕዝባችንን እንዲያግዝ፣ መንግሥታችንና ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎችም የተጀመረውን የሰላም ጉዞ እንዳይቀለበስ በከፍተኛ ኃላፊነት እንዲሰሩ፣ ኢትዮጵያውያን የሆናችሁ ልጆቻችንም በተለመደው የመተጋገዝ ቅዱስ ባህላችን መሠረት እርስ በርስ በመረዳዳት ይህንን ፈተና እንድናልፈው በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን ከአደራ ጋር እናስተላልፋለን፤

መልካም በዓለ ልደት ያድርግልን
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
ዘአኩስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ታሕሣሥ ፳፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም.
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
42 views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 11:52:37 ቅዱስነታቸው የ2015 ዓ.ም በዓለ ልደትን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

° በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
° ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ ፣
° የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፋ የቆማችሁ፣
° በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣
° እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤት የምትገኙ ° ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን በሙሉ፣
በዕለተ ልደቱ ሰማያውያንንና ምድራውያንን በአንድነት አገናኝቶ ስለ ሰላም እንዲዘምሩ ያደረገ የሰላም አለቃ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ አምስት ዓመተ ልደቱ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡

“ወይከውን ሰላም በመዋዕሊሁ፤ በዘመኑም ሰላም ይሆናል” (ዘካ.፱፥፲)
በአበሳው ምክንያት ከፈጣሪው ተለይቶ በሰቆቃ ይኖር የነበረው የሰው ልጅ መንፈሳዊ ሰላሙ ከተናጋ ብዙ ዘመናትን አስቆጥሮአል፤ የሰላሙ መናጋት የጀመረውም ከእግዚአብሔር ከተለየበት ቀን አንሥቶ ነው፣ መቼም ቢሆን መለያየት ጉዳትን እንጂ ጥቅምን አያስገኝምና ሰው ከእግዚአብሔርና የእግዚአብሔር ከሆነው ሁሉ በመለየቱ ጉዳቱ የበረታ ሆነ፤ ኑሮውም ደፈረሰበት፤ ጣዕመ ሕይወቱም ወደ እሬት ተለወጠበት፤ በዚህም ምክንያት ሰው በጨለማና በሞት ጥላ የተዋጠ ምስኪን ፍጡር ሆኖ ኑሮውን ቀጠለ፤

ይሁን እንጂ ፍቅርና ርኅራኄ ቸርነትና አዘኔታ ምሕረትና ይቅርታ ገንዘቡ የሆነ አምላካችን እግዚአብሔር፣ ሰውን በምሕረትና በይቅርታ ሊቀበለው ወደደ፤ ይህንም በልዩ ልዩ ዓይነተ ነገር ገለፀ፤ እግዚአብሔር የሰው ልጅን መንፈሳዊ ሰላም በእርግጠኝነት እንደሚመልስ ከገለፀባቸው ቃላተ ትንቢት አንዱ “በዘመኑ ሰላም ይሆናል” የሚል ቃለ ሰላም ይገኝበታል፤ የዚህ ቃለ ሰላም መሠረተ ሐሳብ ሲታይ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሚሰጠው ዘላቂና ፍጹም ሰላም በመሢሑ በኩል በሚሆነው ቤዛነት እንደሆነ ነው፣ ከዚህ አኳያ እግዚአብሔር የመሢሑን መምጣት ከመጀመሪያው ሰው ከአዳም ጀምሮ ሲገልፅ ቆይቶአል፣ ዘመኑ ሲደርስም መሢሑ በዚህ ዓለም ተገልፆአል፤ መሢሑ በዚህ ዓለም የተገለፀው በብሥራተ ገብርኤልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰውነትን ተዋሕዶ ነው፤

ወልደ እግዚአብሔር በተዋሐደው ሰውነት በቤተ ልሔም ሲወለድ፣ ሠራዊተ መላእክት “ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ፤ ለሰው ልጅ ውድ ነገር የሆነው ሰላም በምድር ላይ ሆነ” በማለት ዘምረዋል፤ መላእክት በዚህ መዝሙራቸው የተወለደው ሕፃን ከብዙ ዘመናት በፊት ለሰላሙ ፍጻሜ የለውም ፤በዘመኑም ሰላም ይሆናል” ተብሎ የተነገረለት የሰላም አለቃ መሆኑን ለዓለም አበሰሩ፤ እረኞችም በተወለደበት ቦታ ተገኝተው የሰላሙን መዝሙር ተካፋይ ሆኑ፤

የጥበብ ሰዎች የሆኑ የምሥራቅ ነገሥታትም አምላክነቱን ለመግለፅ ዕጣንን፣ንጉሥነቱን ለመግለፅ ወርቅን፣አዳኝነቱን ለመግለፅ ከርቤን እጅ መንሻ አድርገው ገበሩለት፤ ለአምላክነቱም ከምድር ወድቀው ሰገዱለት ፤

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!!

እግዚአብሔር ከሰው ጋር ሰላም መፍጠሩን የገለፀው በትንቢት ወይም በምሳሌ ወይም በቃል ብቻ አልነበረም፤ እጅግ በሚያስደንቅ የተዋሕዶ ተግባርም እንጂ፤በአበሳ ኃጢአት መነሻነት በጠላትነት ተፈርጆ የነበረውን የሰው ልጅ መውደዱ ብቻ ሳይሆን፣ ጭራሽ ሰውነቱን ሰውነት አድርጎ ወይም አካሉን አካል አድርጎ መገለጡ፣ የሰላሙ ጥልቀትና ምጥቀት ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ የሚያስገነዝብ ነው፤ የሰማይ ሠራዊትም “የሰው ልጅን እጅግ ወደደው” በማለት በከፍተኛ አድናቆት የዘመሩለት የሰውን ሰውነት ተዋሕዶና የራሱን አካል አድርጎ በመንበረ ጸባኦት እንዲቀመጥ አድርጎት በማየታቸው ነው፤

ይህ የዕርቀ ሰላም ውጤት ነው፤ ዕርቀ ሰላም የማይፈታው ችግር እንደሌለ ይህ አምላካዊ ዕርቅ ግዙፍ ማስረጃ ነው፤ እግዚአብሔር ሰውን የታረቀው በምሕረትና በይቅርታ ብቻ አይደለም፤ ወይም ላቅ ያለ ቁሳዊ ስጦታ በመስጠትም አይደለም፤እግዚአብሔር ሰውን የታረቀው “ሰው በመሆን” ነው፤ በዚህ ምሥጢረ ተዋሕዶ እግዚአብሔር ሰው ሲሆን ሰውም እግዚአብሔርን የመሆን ዕድል በማግኘቱ በውጤቱ ሰው በተዋሕዶተ ቃል በመንበረ ጸባኦት ተቀምጦ ሰማያውያን መላእክትን ጨምሮ የፍጥረታት ሁሉ ገዥ ሊሆን ችሎአል፤
ቅዱስ መጽሐፍ ይህንን ሲገልፅ “ክብረ ወስብሐተ ከለልኮ፤ ወሤምኮ ውስተ ኲሉ ግብረ እደዊከ፤ ወኲሎ አግረርከ ሎቱ ታሕተ እገሪሁ፤ የክብርና የምስጋና ዘውድን ጫንህለት፤ በእጆችህም ስራ ላይ ሾምኸው፤ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፤ እርሱ መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ” ይላል ፤

በመሆኑም የተወለደው ሕፃን በዘመኑ ዘላቂና ፍጹም የሆነ መንፈሳዊ ሰላምን ያስገኘ ብቻ ሳይሆን በተዋሕዶተ ቃል በመንበረ ጸባኦት ተቀምጦ የመላእክትና የፍጥረት ሁሉ ገዥ ስለሆነ ከምንም ሁሉ በላይ መሆኑን እናስተውላለን፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናትና ምእመናት!!

እግዚአብሔር እጅግ የሚወደን መሆኑን የምናውቀው “እኛን መስሎ ሳይሆን እኛን ሆኖ በመካከላችን በመገኘቱ” ነው፤ታዲያ እግዚአብሔር እኛን ይህን ያህል ከቀረበንና ከወደደን እኛም በዚሁ መጠን ልንዋደድ አይገባንምን? እንድናደርገውና እንድንፈጽመው የሰጠን አደራስ ለሰው ሁሉ እንዲህ ያለ ፍቅር እንዲኖረን አልነበረምን? ሰዎች በየትም እንኑር በየት እርስ በርስ በመፈቃቀርና በመዋደድ በሰላም የመኖር አምላካዊ ግዴታ እንዳለብንስ ዘነጋነውን? በሰላምና በፍቅር የመኖር ጉዳይ ለሰዎች እንደመብት ሳይሆን እንደ ግዴታ ነው፤ ምክንያቱም የነገርየው ውስጠ ይዘት የመኖርና ያለመኖር አንድምታ አለውና ነው፤

እግዚአብሔር በሕይወት እንድንኖር እኛን ፈጥሮአል፤ ይህ የእግዚአብሔር ቀዋሚ ፈቃዱ ነው ፤በመሆኑም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማክበር ለሰው ልጆች ሁሉ የውዴታ ሳይሆን የግዴታ ኃላፊነት አለብን ፤ይልቁኑም በመንፈሳዊውም ሆነ በዓለማዊው አመራር የምንገኝ ኃላፊዎች ከሁሉም በላይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማክበር ይጠበቅብናል፤ የሰውን ሕይወት ለመጠበቅ የሰው ሕይወት መጥፋት አለበት የሚል የተሳሳተ አካሄድ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት የለውም፤
ምክንያቱም በአንድ በኩል እያጠፉ በሌላ በኩል እጠብቃለሁ የሚል አካሄድ ከኪሣራና ከጥፋት ነጻ አያደርግምና ነው፤ በዚህ ስሑት አስተሳሰብ ዓለም በሽቅድምድም እያመረተችው ያለው የፍጥረተ እግዚአብሔር ማጥፊያ መሣሪያ ከአጥፊነት በቀር የአልሚነት ሚና አለው ብሎ መናገር ፈጽሞ አይቻልም፤

በዚህ አጥፊ መሣሪያ የእግዚአብሔር ፈቃድ ተጥሶ ሕፃናትና እናቶች ፣ዓቅመ ደካሞችና አረጋውያን በሕይወት የመኖር ዕድል አጥተዋል፤ ይሁንና ቸርነቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር አምላክ በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን የተከሠተው ችግር በከፊልም ቢሆን ረገብ ብሎ የሰላም ጭላንጭል እንድናይ አድርጎናል፤ ይህ ሰላም የእግዚአብሔር ስጦታ ነውና ልንወደው ልናከብረውና ልንጠብቀው ይገባል፤

ሰላም በጠፋ ጊዜ በወገኖቻችን ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ በዓይናችን አይተናል፤ ይህ ዓይነቱ ክሥተት ሊቆም እንጂ ሊቀጥል አይገባም፤ ስለዚህ የተገኘው የሰላም ጭላንጭል ወደ ፍጹም አስተማማኝ ደረጃ በሙሉነት እንዲያድግ ሁላችንም በኃላፊነት እንድንሰራ በዚህ አጋጣሚ በአጽንዖት አደራ እንላለን፤
37 views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 23:11:21 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስትያን ስብከተ ወንጌል ከደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት እና ከቅዱስ ኡራኤል አካባቢ ወጣቶች መንፈሳዊ የአገልግሎት ማህበር ጋር በመቀናጀት የተዘጋጀ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ታህሳስ 25 / 2015
50 views20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-03 23:11:18
46 views20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 21:46:15
18 views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 21:45:51 ድንቅ የበረከት ስፍራ በዕለተ ሰንበት

#ከማሕበረ_ፅጌ_ማርያም ጋር #በደብረብርሃን_ወህኒ_ቤት

እንደሚታወቀው #ማሕበረ_ፅጌ_ማርያም በመላው ኢትዮጵያ ማለት ይቻላል ለብዙ ዓመታት በየወህኒ ቤቱ የተለያዩ እርዳታዎችን ማለትም እንደ #መንፈሳዊ_መፅሐፍትን #የንፅህና_መጠበቂያ ፣ሌላም ሌላም .......ከማድረግም በዘለለ የምሳ መርሐ ግብራትን ከመንፈሳዊና ዘለዓለማዊ ምግብ ጋር በማድረግ የሚያከናውኑት በጎ ተግባር ለሌሎችም ማሕበራት ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነዉና በርቱ ተበራቱ ለማለት እወዳለሁ
18 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 19:03:02
30 views16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ