Get Mystery Box with random crypto!

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የሰርጥ አድራሻ: @ibnumunewor
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 77.25K
የሰርጥ መግለጫ

كناشة ابن منور

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-16 18:59:29 ከደቂቃዎች በኋላ የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
7.2K views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-15 17:47:03
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካቱሁ ይህ ወንድማችን ወሎ ቦረና ከላላ ወረዳ ልጓማ የምትባል አካባቢ ተወልዶ ያደገ ነዉ።
ተጨማሪ ስልክ
09 14 36 37 98
ወይንም
09 31 82 91 83

ሼር እያደረጋችሁ።
13.0K views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-15 17:07:50 ጠፍቶ የነበረው ወንድም ተገኝቷል አልሐምዱሊላህ። ሰበብ የሆናችሁ ጀዛኩሙላሁ ኸይረን።
11.3K viewsedited  14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-15 10:01:11 አንድ ነጥብ ለአስተውሎት
~
በጣም ከምንሸወድባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ በእውቀት የሚበልጡንን መሻይኾች ልንጠቀምባቸው አለመቻላችን ነው። በሃገራችን የመንሃጅ ግንዛቤ በጣም የሳሳ እንደሆነ ማንም የማይክደው ሐቅ ነው። ይሄ ክፍተት ደግሞ ብዙ መሻይኾች ላይ ይጎላል። ለወቅታዊ ኪታቦችና ለኢንተርኔት የቀረበው ወጣት #አንፃራዊ በሆነ መልኩ ትንሽ ሻል የሚልበት ሁኔታ አለ። በንፅፅር ነው እያወራሁ ያለሁት። ትንሽ እውቀት የራሱ ብዙ ድክመት አለበትና የማንክደው ብዙ ጣጣ እያመጣብን ነው። ሌሎችን ችግሮች ለጊዜው ልተውና በተነሳሁበት ጉዳይ ላይ ያለውን ላንሳ። ድርቅና (ዒናድ) ሳይሆን የግንዛቤ ችግር ያለባቸውን መሻይኾች መቅረብ እንጂ መራቅ ለሁሉም አይበጅም። ይሄ ማግለልና መግፋት ለነሱም፣ ለኛም፣ ለቆምንለት አላማም፣ ለወገናችንም የሚበጅ አይደለም፡፡ እና ተውሒድና ሱናን መውደድ፣ የሱና ዑለማዎችን ማክበር፣ ለደሊል እጅ መስጠት ካሸተትንባቸው ክፍተቶችን ብናይ እንኳ ከመራቅ ይልቅ መቅረባችን ነው የሚያተርፈን።

1ኛ:- ለነሱም ውለታ መዋል ነው። እኛ ችላ ስንላቸው በሌሎች ይጠለፋሉ። ይሄ ከዚህ ቀደም በስፋት ተከስቷል። እኛ ስንርቃቸው የሌሎች ሲሳይ ሆነዋል። በራሳችን ላይ ጠላት አብዝተናል። ካለፈው ልንማር በቃ ልንል ይገባል፡፡
2ኛ:- ለሰፊው ህዝበ ሙስሊም፦ እነዚህ መሻይኾች ህዝብ ዘንድ የተሻለ ቦታ ስለሚኖራቸው የነሱ መጠንከር ለህዝብ ይተርፋል፡፡ እኛ ባግባቡ ካልቀረብናቸው ግን ሌሎች አካላት የሱናን ደዕዋ በጥላቻና በስጋት እንዲመለከቱ አድርገው ይሞሏቸዋል። ይሄ ደግሞ ዞሮ ዞሮ ዳፋው ለህዝብ ነው የሚተርፈው።
3ኛው:- ጥቅም ለራሳችን ነው፡፡ እኛ ትንሽዬ የመንሃጅ ግንዛቤ አለችን ማለት (ያውም ከኖረ) ከነሱ በእውቀት በለጥን ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውም ከነጭራሹ እውቀት አለን ማለትም አይደለም። እነሱ ዘንድ መንሃጅ ላይ የግንዛቤ ክፍተት መታየቱ እውቀት የላቸውም ማለት አይደለም፡፡ ለሁለቱም ወገን የሚበጀው መቀራረቡ ነው። እነሱ ዘንድ ያለውን ክፍተት ከቻልን ኪታብ እየገዛንላቸው ፣ ካልሆነ እያዋስናቸው፣ የታላላቅ ዑለማዎችን ንግግር እያሰማናቸው፣ በአደብ እየተከራከርናቸው ለመሙላት መጣር አለብን። በተለይ ኪታብ መስጠት ያለው ዋጋ ቀላል አይደለምና በዚህ ላይ ልንረባረብ ይገባል። የኛን ጅህልና ደግሞ ቁጭ ብሎ በመማር መግፈፍ አለብን። ይህን ስናደርግ ለራሳችንም፣ ለመሻይኾቹም፣ ለወገናችንም ትልቅ ውለታ እንውላለን። ለደዕዋችን መፋፋትም ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡ የማወራው ከላይ እንደገለፅኩት ተውሒድና ሱናን መውደድ፣ የሱና ዑለማዎችን ማክበር፣ ለደሊል ራስን ዝቅ ማድረግ፣ ቅንነት ስለሚታይባቸው መሻይኾች ነው።
መቼም በርካታ መሻይኾችና ዱዓቶች ተሰውፍ እና ሌሎችም የተሳሳተ መስመር ውስጥ ከቆዩ በኋላ እንደተመለሱ ይታወቃል። ከአላህ በኋላ ለዚህ መመለሳቸው የተለያዩ ሰበቦች ይኖራሉ። ዛሬም እነዚህን ሰበቦች ችላ ልንላቸው አይገባም። ዛሬም ክፍተት ያለባቸው ሰዎች ሲገጥሙን በመወያየት፣ መረጃ በመለዋወጥ፣ በችግራቸው ከጎናቸው በመቆም ልናቀርባቸው ይገባል። አንተ ትላንት በተለያዩ መስመሮች ላይ አልፈህ መጥተህ ሌሎች ወደሱና እንዳይገቡ በር ለመከርቸም አትታገል። ያለፍክባቸውን አባጣ ጎባጣ መንገዶች መለስ ብለህ አስተውላቸው።
=

ግንቦት 28/2013

https://t.me/IbnuMunewor
13.9K views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-15 08:13:09 ቻናሌ ላይ በተደጋጋሚ ማስታወቂያ እየተለቀቀ እንደሆነ አሁን አንድ ወንድም አሳወቀኝ። በራሱ በቴሌግራም እንጂ እኔ እያሰራጨሁት እንዳልሆነ እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ። ቀደም ብዬ ያልጠቆምኩት ማስታወቂያው ለኔ ስለማይታየኝ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
12.0K viewsedited  05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-15 07:07:16 * ሰበብ እየፈለገ ሌሎችን ከሱና የሚያስወጣ አካል መጨረሻ ላይ ሌሎችን ባስወጣበት በር ራሱ ይወጣል።
* እወቅ! ሌሎች ላይ የመዘዝከው የኢልዛም ሰይፍ ወዳንተም ይዞራል። እቆርጥበታለሁ ያልከው ይቆርጥሃል።
* ሰለፊያ የወደድከውን የምታስገባበት፣ የጠላሀውን የምታስወጣበት ያ'ባትህ ግቢ አይደለም። ሰለፊያ ኢስላም ማለት እንጂ ሌላ ቡድን አይደለም። ይህንን ከቃላት ባሻገር በተግባር አስረግጥ።
* በዚህ ዘመን በመንሀጅ ስም ተጠቅልሎ ያለው አብዛኛው ጩኸት የአመል ችግር ነው። ያለበለዚያ ሰው እንዴት እስ'ካፍንጫው በተነከረበት ጥፋት ሌሎችን ሊከስ ይደፍራል?
* በሺርክና በቢድዐ መፈረጅ ከሺርክና ከቢድዐ የማስጠንቀቅ ያህል ቀላል አይደለም። ሁለተኛው ላይ ካለህ ትጋት ይልቅ የመጀመሪያውን መድፈርህ መታመምህን ነው የሚያሳየው። ሳይጠናብህ ታከመው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
15.0K views04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-14 14:48:59 ጭፍራው ቅርቃር ውስጥ ገብቷል
~
ቅልጥ እንደ ቅቤ - ፍርስ እንደ ሸክላ
ሁሉ ነገር እርቃን - እነ ሳይሞቅ ፈላ!

ይሄ ሰካራም ጭፍራ ብዙ እንደማይራመድ በጣም እርግጠኛ ነበርኩ። በዚህ ፍጥነት ድንብርብሩ ሲወጣ፣ ጉዱ ሲዝረከረክ ማየት ግን የጠበቅኩት አልነበረም። የዛሬን ሁለት ዓመት መሰለኝ ወራቤ ላይ አንድ ወንድም ዐብዱልሐሚድ ለተሞ አንድ መንሀጅ ላይ ሁለት አመት ታግሶ መቆየት አይችልም ጠብቁ ሲል ሰምቼው ነበር። ምናልባት የሆነ ያክል ተጋኖ ይሆን? አላውቅም። ንግግሩ ግን በውስጡ የሆነ እውነት አዝሏል። አሁን ላይ አንዳንድ ነገሮች ጫፋቸው እየዘለቀ ነው። እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ ይሄው እየጠራ መጣ። በየጊዜው እየወጡ ካሉ በርካታ የቪዲዮ እና የፎቶ ማስረጃዎች ውስጥ ለጊዜው አንድ ማሳያ ልጥቀስ፦

ጠሃ ኸዲር የዚህ የተንቀዠቀዠ ጭፍራ አጫፋሪ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ሶሻል ሚዲያ ላይ እየዘለቀ ሁለት ሶስት መስመር ስድብ መፃፍን ቁም ነገር ያደረገ በተግባር ግን በተለያየ ቦታ የተለያየ ፊት የሚጠቀም ሰው ነው።
* ሳዑዲ ውስጥ ጤነኛ ያልሆኑ ሰዎች ዘንድ ቁጭ ብሎ ለአመታት ይማራል። እዚህ ደግሞ እነ እከሌ ከእነ እከሌ ጋር ተቀመጡ እያለ ፎቶ ይለጥፋል። የሳዑዲ ኤምባሲ ሲጋብዛቸው ራሱም ጭፍራዎቹም ከነዚያው ከሚያወግዛቸው አካላት ጋር አንድ ላይ ይጣዳሉ። በተለያዩ ቦታዎች የተለያየ ፊት ማሳየትን ተክኖበታል።
* መሻይኾች ዘንድ ሌላ ሰው ነው። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ደግሞ ሌላ።
* ሳዑዲ ውስጥ ሌላ ሰው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ።
* እንደ ባህሩና ሑሴን ያሉ ተናካሽ ጓዶቹ ጋር ሲሆን ሌላ ነው። አቃቂር እያወጡ፣ ቅጥፈት እየለጠፉ የሚናከሱ አውሬዎች ናቸው። እያደናነቀ የሚያስተዋውቃቸው የሀረር አካባቢ ጭፍራዎቹ ደግሞ እሱ በሚስላቸው 'ሙስተዋ' ላይ አይደሉም። ያያያዝኩት ቪዲዮ ለዚህ አንድ ምስክር ነው።
በቪዲዮው ላይ የጠሀ ጭፍራ የሆኑት (የነበሩት ብለው ይሻል ይሆን?) እነ ኢልያስ ዐባስ እና አሕመድ ሙሐመድ (ጭሮ?) ከነ ዶክተር ጀይላን ጋር ተቀማምጠው የአንድነት መግለጫ ያወጡበት ጉባዔ ነው። ቪዲዮው ላይ ከሰፈረው ቃል ቀንጨብ ላድርግ፦

1- የዶክተር ጀይላን ንግግር፦

"የሀረር ዑለማኦች ህብረት እና የኦሮሚያ ዑለማኦች ህብረት ከኢትዮጵያ ዑለማኦች ህብረት ጋር አንድ ሆነው ሲወያዩ ውለዋል። በፊርቃ ስም የሚሰጣጡ፣ ወደዛ ወደዚህ እያሉ አንዱ ባንዱ ላይ የሚፅፉ፣ በዑለማእ ስም የሚነግዱ ስላሉ፤ ሸይኾች ሸይኽ ኢልያስ ዐባስና ሸይኽ አሕመድ ከዑለማኦች ጋር አንድ ሆነዋል። ከአህለ ሱና ወልጀማዐ ዑለማኦች ጋር፣ ከመጅሊስ ዑለማኦች ጋር እጅና ጓንት ሆነን አንድ ላይ ሆነን እንሰራለን ብለው (ቃል) ገብተውልናል።
በስማቸው ከሚነግዱባቸው ሰዎች ራሳቸውን ነፃ ያድርጉ።"

ከዚያ እነ ጠሀ በስማቸው የሚነግዱባቸው ሁለቱ ሰዎች ራሳቸውን ነፃ አድርገው ተናገሩ። ይሄውና፡

2- የኢልያስ ዐባስ ንግግር፦

"እኛ ዓሊሞቻችን ሸይኾቻችን ሸይኽ ሙሳ እና ዶክተር ጀይላን እንዲሁም ሌሎችም አሉ። ድሮም የተጣላነው ነገር የለም። አብረን ነበር። አሁንም አብረን ነን። ከዚህም በኋላ አብረን ነን፣ እስከ ዘላለም። ዓሊሞችን ከሚሳደብ የጠራን ነን።"

3- የአሕመድ ሙሐመድ ንግግር:-

"እኛ ከታላላቅ ሸይኾቻችን ጋር ነን። ድሮም ከነሱ ጋር ነበርን። አሁንም ከነሱ ጋር ነን። እነሱን ከሚሳደብ ሰው ድሮም አሁንም ንፁህ ነን።"

ልብ በሉ! ጠሀ ኸዲር እነዚህን ሁለቱን ሰዎች (ማለትም ኢልያስ ዐባስ እና አሕመድ ሙሐመድ) ሞቅ አድርጎ ያወድሳል። ያሰራጭላቸዋልም፡፡ ለምሳሌ ያክል በቅርቡ እንዲህ ሲል ፅፏል:-

"أشد على أيديكم يا أبطال شرق هرر فضيلة الشيخ Sheek Iliyaas Abbaas
وفضيلة الشيخ Shekh Ahmade Muhammed
زادكم الله قوة إلى قوتكم
فقد أقضت جهودكم المضاجع وألهبت المشاعر وأسهرت وهزت ولن يهنأ منهم أحد مهما كان بعدما التهبت الأحشاء واضطرمت!"

እነዚህ የጠሀ ጀግኖች ግን፡

1ኛ፦ ከነ ዶክተር ጀይላን ጋር፣ እንዲሁም በጠቅላላ ከመጅሊስ ሰዎች ጋር አንድ እንደሆኑ ድሮም፣ አሁንም በመካከላቸው ልዩነት እንደሌለ ገልፀዋል። እስከ ዘላለም ከነሱ እንደማይለዩም አስረግጠው ተናግረዋል።
2ኛ:- እነሱን (እነ ዶክተር ጀይላንን) ከሚሳደቡ አካላት ድሮም አሁንም ንፁህ ነን። ፈፅሞ እነሱን ከሚሳደቡ ጋር አንሆንም ማለታቸውን ያዙ። እዚህ ላይ ቁጥር አንድ ተጠቃሹ ጠሀ ኸዲር ነው። አሞሌው አልሰራም።

ከዚህ በኋላ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።

1ኛው ምርጫ፦ ወይ እንደ ግለቱ እያዩ ሲያሻቸው "እኛ ድሮም ጀምሮ መንሀጅ ገብቶናል፣ ለ20፣ ለ30 አመታት ሰለፊያን (የነሱን ቨርዥን) ስናስተምር ነው የኖርነው፣ ከኢኽዋን የጠራን ነን፣ ..." እያሉ መሞገት፤ ሲላቸው ደግሞ ከነዚያው ኢኽዋን ከሚሏቸው ሰዎች "ድሮም አሁንም አንድ ነን፣ ዘላለም አንለያይም" እያሉ የጋራ መግለጫ እያወጡ መቀጠል ነው። በተለያየ መመዘኛ እየመዘኑ፣ የተለያየ ፊት እያሳዩ መሄድ ለጠሀ ከባድ አይመስለኝም። ይሄ ግን የሰለፊ መገለጫ አይደለም። ሸይኽ ሙቅቢል እንዲህ ይላሉ፦
فالحزبي مستعد أن يكون له خمسة أوجه. والنبي ﷺ يقول: إن من شر الناس ذا الوجهين الذي يأتي هـولاء بوجه وهؤلاء بوجه.
أما السني فإنه متمسك بدينه سواء رضي فلان أو لم يرضَ بخلاف الحزبيين.
"ቡድንተኛ ሰው አምስት ፊት ሊኖረው ዝግጁ ነው። ነብዩ ﷺ 'ከክፉ ሰዎች ውስጥ የሆነው ባለ ሁለት ፊት ነው። ያ እነዚያ ዘንድ በአንድ ፊት፣ ሌሎቹን ደግሞ በሌላ ፊት የሚቀርበው።' ሱኒይ የሆነ ሰው ግን እከሌ ቢወድም ሆነ ቢጠላ ዲኑን አጥብቆ የሚይዝ ነው። ከቡድንተኞች በተለየ።" [ቱሕፈቱል ሙጂብ፡ 290]

2ኛው ምርጫ፦ ከነዚህ ሲያወድሳቸው ከነበሩ አካላት መለያየቱን ማወጅ ነው። እንደለመዱት ከሙብተዲዕ ጋር የሚቀማመጡ፣ ህብረት የሚፈጥሩ፣ ሰለፊዮችን የሚገፉ፣ ለሙብተዲዕ የሚከላከሉ ሙብተዲዎች ናቸው የሚል መግለጫ ማውጣት። ሰውየው ተቃራኒ ነገሮችን ባንድ ላይ የማስተናገድ ልምድ ቢኖረውም ይሄኛው ግን ለመሸፈን የሚመች አይደለም። "ግመል ሰርቆ አጎንብሶ" የማይሆን ነገር ነው። ስለዚህ መለያየትን ከማወጅ ውጭ ምርጫ አይኖርም። ይህ ሲሆን ደግሞ ህብረቱ ይናዳል።

ካ'ህያ ቆዳ የተሰራ ቤት
ይበታተናል ጅብ የጮኸ 'ለት!

የነዚህ ሰዎች ጉድ ይሄ ብቻ አይደለም። አለ ገና!
ستُبْدي لكَ الأيّامُ ما كنتَ جاهلاً - ويأتِيكَ بالأخبارِ مَن لم تُزَوِّدِ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
18.3K viewsedited  11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-14 14:48:52
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
16.1K viewsedited  11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-14 09:40:19 ኢብኑ ቁዳማ አልመቅዲሲይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"አብዛኞቹ ሰዎች የጠፉት የሰዎችን ውግዘት በመፍራት እና ሙገሳቸውን በመሻት ነው። በዚህ የተነሳ እንቅስቃሴያቸው እንዳለ ሰዎችን ከማስደሰት ጋር በሚገጥም መልኩ ይሆናል። ይህም ሙገሳን በመሻትና ውግዘትን በመፍራት ነው። ይሄ አጥፊ ስለሆነ ሊታከም ግድ ይላል።"
"ሙኽተሶሩ መንሃጂል ቃሲዲን፡ 212]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
14.1K views06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-14 08:32:22 https://t.me/online_market4525
13.3K views05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ