Get Mystery Box with random crypto!

ጭፍራው ቅርቃር ውስጥ ገብቷል ~ ቅልጥ እንደ ቅቤ - ፍርስ እንደ ሸክላ ሁሉ ነገር እርቃን - እነ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ጭፍራው ቅርቃር ውስጥ ገብቷል
~
ቅልጥ እንደ ቅቤ - ፍርስ እንደ ሸክላ
ሁሉ ነገር እርቃን - እነ ሳይሞቅ ፈላ!

ይሄ ሰካራም ጭፍራ ብዙ እንደማይራመድ በጣም እርግጠኛ ነበርኩ። በዚህ ፍጥነት ድንብርብሩ ሲወጣ፣ ጉዱ ሲዝረከረክ ማየት ግን የጠበቅኩት አልነበረም። የዛሬን ሁለት ዓመት መሰለኝ ወራቤ ላይ አንድ ወንድም ዐብዱልሐሚድ ለተሞ አንድ መንሀጅ ላይ ሁለት አመት ታግሶ መቆየት አይችልም ጠብቁ ሲል ሰምቼው ነበር። ምናልባት የሆነ ያክል ተጋኖ ይሆን? አላውቅም። ንግግሩ ግን በውስጡ የሆነ እውነት አዝሏል። አሁን ላይ አንዳንድ ነገሮች ጫፋቸው እየዘለቀ ነው። እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ ይሄው እየጠራ መጣ። በየጊዜው እየወጡ ካሉ በርካታ የቪዲዮ እና የፎቶ ማስረጃዎች ውስጥ ለጊዜው አንድ ማሳያ ልጥቀስ፦

ጠሃ ኸዲር የዚህ የተንቀዠቀዠ ጭፍራ አጫፋሪ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ሶሻል ሚዲያ ላይ እየዘለቀ ሁለት ሶስት መስመር ስድብ መፃፍን ቁም ነገር ያደረገ በተግባር ግን በተለያየ ቦታ የተለያየ ፊት የሚጠቀም ሰው ነው።
* ሳዑዲ ውስጥ ጤነኛ ያልሆኑ ሰዎች ዘንድ ቁጭ ብሎ ለአመታት ይማራል። እዚህ ደግሞ እነ እከሌ ከእነ እከሌ ጋር ተቀመጡ እያለ ፎቶ ይለጥፋል። የሳዑዲ ኤምባሲ ሲጋብዛቸው ራሱም ጭፍራዎቹም ከነዚያው ከሚያወግዛቸው አካላት ጋር አንድ ላይ ይጣዳሉ። በተለያዩ ቦታዎች የተለያየ ፊት ማሳየትን ተክኖበታል።
* መሻይኾች ዘንድ ሌላ ሰው ነው። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ደግሞ ሌላ።
* ሳዑዲ ውስጥ ሌላ ሰው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ።
* እንደ ባህሩና ሑሴን ያሉ ተናካሽ ጓዶቹ ጋር ሲሆን ሌላ ነው። አቃቂር እያወጡ፣ ቅጥፈት እየለጠፉ የሚናከሱ አውሬዎች ናቸው። እያደናነቀ የሚያስተዋውቃቸው የሀረር አካባቢ ጭፍራዎቹ ደግሞ እሱ በሚስላቸው 'ሙስተዋ' ላይ አይደሉም። ያያያዝኩት ቪዲዮ ለዚህ አንድ ምስክር ነው።
በቪዲዮው ላይ የጠሀ ጭፍራ የሆኑት (የነበሩት ብለው ይሻል ይሆን?) እነ ኢልያስ ዐባስ እና አሕመድ ሙሐመድ (ጭሮ?) ከነ ዶክተር ጀይላን ጋር ተቀማምጠው የአንድነት መግለጫ ያወጡበት ጉባዔ ነው። ቪዲዮው ላይ ከሰፈረው ቃል ቀንጨብ ላድርግ፦

1- የዶክተር ጀይላን ንግግር፦

"የሀረር ዑለማኦች ህብረት እና የኦሮሚያ ዑለማኦች ህብረት ከኢትዮጵያ ዑለማኦች ህብረት ጋር አንድ ሆነው ሲወያዩ ውለዋል። በፊርቃ ስም የሚሰጣጡ፣ ወደዛ ወደዚህ እያሉ አንዱ ባንዱ ላይ የሚፅፉ፣ በዑለማእ ስም የሚነግዱ ስላሉ፤ ሸይኾች ሸይኽ ኢልያስ ዐባስና ሸይኽ አሕመድ ከዑለማኦች ጋር አንድ ሆነዋል። ከአህለ ሱና ወልጀማዐ ዑለማኦች ጋር፣ ከመጅሊስ ዑለማኦች ጋር እጅና ጓንት ሆነን አንድ ላይ ሆነን እንሰራለን ብለው (ቃል) ገብተውልናል።
በስማቸው ከሚነግዱባቸው ሰዎች ራሳቸውን ነፃ ያድርጉ።"

ከዚያ እነ ጠሀ በስማቸው የሚነግዱባቸው ሁለቱ ሰዎች ራሳቸውን ነፃ አድርገው ተናገሩ። ይሄውና፡

2- የኢልያስ ዐባስ ንግግር፦

"እኛ ዓሊሞቻችን ሸይኾቻችን ሸይኽ ሙሳ እና ዶክተር ጀይላን እንዲሁም ሌሎችም አሉ። ድሮም የተጣላነው ነገር የለም። አብረን ነበር። አሁንም አብረን ነን። ከዚህም በኋላ አብረን ነን፣ እስከ ዘላለም። ዓሊሞችን ከሚሳደብ የጠራን ነን።"

3- የአሕመድ ሙሐመድ ንግግር:-

"እኛ ከታላላቅ ሸይኾቻችን ጋር ነን። ድሮም ከነሱ ጋር ነበርን። አሁንም ከነሱ ጋር ነን። እነሱን ከሚሳደብ ሰው ድሮም አሁንም ንፁህ ነን።"

ልብ በሉ! ጠሀ ኸዲር እነዚህን ሁለቱን ሰዎች (ማለትም ኢልያስ ዐባስ እና አሕመድ ሙሐመድ) ሞቅ አድርጎ ያወድሳል። ያሰራጭላቸዋልም፡፡ ለምሳሌ ያክል በቅርቡ እንዲህ ሲል ፅፏል:-

"أشد على أيديكم يا أبطال شرق هرر فضيلة الشيخ Sheek Iliyaas Abbaas
وفضيلة الشيخ Shekh Ahmade Muhammed
زادكم الله قوة إلى قوتكم
فقد أقضت جهودكم المضاجع وألهبت المشاعر وأسهرت وهزت ولن يهنأ منهم أحد مهما كان بعدما التهبت الأحشاء واضطرمت!"

እነዚህ የጠሀ ጀግኖች ግን፡

1ኛ፦ ከነ ዶክተር ጀይላን ጋር፣ እንዲሁም በጠቅላላ ከመጅሊስ ሰዎች ጋር አንድ እንደሆኑ ድሮም፣ አሁንም በመካከላቸው ልዩነት እንደሌለ ገልፀዋል። እስከ ዘላለም ከነሱ እንደማይለዩም አስረግጠው ተናግረዋል።
2ኛ:- እነሱን (እነ ዶክተር ጀይላንን) ከሚሳደቡ አካላት ድሮም አሁንም ንፁህ ነን። ፈፅሞ እነሱን ከሚሳደቡ ጋር አንሆንም ማለታቸውን ያዙ። እዚህ ላይ ቁጥር አንድ ተጠቃሹ ጠሀ ኸዲር ነው። አሞሌው አልሰራም።

ከዚህ በኋላ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።

1ኛው ምርጫ፦ ወይ እንደ ግለቱ እያዩ ሲያሻቸው "እኛ ድሮም ጀምሮ መንሀጅ ገብቶናል፣ ለ20፣ ለ30 አመታት ሰለፊያን (የነሱን ቨርዥን) ስናስተምር ነው የኖርነው፣ ከኢኽዋን የጠራን ነን፣ ..." እያሉ መሞገት፤ ሲላቸው ደግሞ ከነዚያው ኢኽዋን ከሚሏቸው ሰዎች "ድሮም አሁንም አንድ ነን፣ ዘላለም አንለያይም" እያሉ የጋራ መግለጫ እያወጡ መቀጠል ነው። በተለያየ መመዘኛ እየመዘኑ፣ የተለያየ ፊት እያሳዩ መሄድ ለጠሀ ከባድ አይመስለኝም። ይሄ ግን የሰለፊ መገለጫ አይደለም። ሸይኽ ሙቅቢል እንዲህ ይላሉ፦
فالحزبي مستعد أن يكون له خمسة أوجه. والنبي ﷺ يقول: إن من شر الناس ذا الوجهين الذي يأتي هـولاء بوجه وهؤلاء بوجه.
أما السني فإنه متمسك بدينه سواء رضي فلان أو لم يرضَ بخلاف الحزبيين.
"ቡድንተኛ ሰው አምስት ፊት ሊኖረው ዝግጁ ነው። ነብዩ ﷺ 'ከክፉ ሰዎች ውስጥ የሆነው ባለ ሁለት ፊት ነው። ያ እነዚያ ዘንድ በአንድ ፊት፣ ሌሎቹን ደግሞ በሌላ ፊት የሚቀርበው።' ሱኒይ የሆነ ሰው ግን እከሌ ቢወድም ሆነ ቢጠላ ዲኑን አጥብቆ የሚይዝ ነው። ከቡድንተኞች በተለየ።" [ቱሕፈቱል ሙጂብ፡ 290]

2ኛው ምርጫ፦ ከነዚህ ሲያወድሳቸው ከነበሩ አካላት መለያየቱን ማወጅ ነው። እንደለመዱት ከሙብተዲዕ ጋር የሚቀማመጡ፣ ህብረት የሚፈጥሩ፣ ሰለፊዮችን የሚገፉ፣ ለሙብተዲዕ የሚከላከሉ ሙብተዲዎች ናቸው የሚል መግለጫ ማውጣት። ሰውየው ተቃራኒ ነገሮችን ባንድ ላይ የማስተናገድ ልምድ ቢኖረውም ይሄኛው ግን ለመሸፈን የሚመች አይደለም። "ግመል ሰርቆ አጎንብሶ" የማይሆን ነገር ነው። ስለዚህ መለያየትን ከማወጅ ውጭ ምርጫ አይኖርም። ይህ ሲሆን ደግሞ ህብረቱ ይናዳል።

ካ'ህያ ቆዳ የተሰራ ቤት
ይበታተናል ጅብ የጮኸ 'ለት!

የነዚህ ሰዎች ጉድ ይሄ ብቻ አይደለም። አለ ገና!
ستُبْدي لكَ الأيّامُ ما كنتَ جاهلاً - ويأتِيكَ بالأخبارِ مَن لم تُزَوِّدِ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor