2022-07-10 18:47:54
ጁለይቢብ رضي الله عنهم .
...ማደርያ የሌለው ልብሱ የተበጣጠሰ ከረሀብ መፈራረቅ ብዛት ሆዱ ከጀርባው የተጣበቀ ድህነት አጎሣቁሎ ያጠወለገው ቢጠፋ የት ሄደ የማይባል ቢኖር
የማይስተዋል ስሙን ታሪክ ያጎላው የረሱል ኋዲም ጁለይቢብ ነው እሱ አላህ መልካም ስራውንይውደድለት ከእለታት በአንዱ ቀን ነብያችን(صلى الله عليه وسلم ) ዘንድ ዞርዞር እያለነበር ረሱልም ጠርተው ጁለይቢብ ሆይ! አታገባምን?
በማለት ጠየቁት እርሱም ያ! ረሱለሏህ ማነው ልጁን ሚድርልኝ በማለት መለሰላቸው በሌላ ቀንም ጁለይቢብ ሆይ!!አታገባምን?በማለት ዳግም
ጠየቁት ጁለይቢብምጨ ያ! ረሱለሏህ ገንዘም ሆነ የማድርበት ቤት የለኝ እሷን
የማለብሳት ይቅርና ለራሴም የምለብሰው ብጣሽ ጨርቅ
የማላገኝ ከመልክ መልከ ጥፉ ማነው ልጁን የሚድርልኝ በማለት በሚያሳዝንና ልብ በሚነካ አንደበት ብሶቱን
ገለፀላቸው
ረሱልም(صلى الله عليه وسلم)በሌላ ጊዜ ለሶስተኛ ጊዜ ከጠየቁት
በኋላ ምላሹ ተመሳሳይ ሲሆን<<እኔ እድርሀለው>> አሉት
ጁለይቢብም በህብረተሰቡ ውስጥ ቦታና ተሰሚነት እንደሌለው ስለሚያውቅ ብዙም ተስፋ ሳያደርግ ቁጭቱን
ዋጥ አድርጎ ኑሮውን ቀጠለ
አንድ የመዲና ሰው ወደ መስጂል ነበዊ በመምጣት ልጁን እንዲያገቡለት ለረሱል ጠየቀ ነብያችንም እሺ አሉት
የልጅቷ አባት ከቦታው ተነስቶ በደስታ ተፍለቀለቀ አስከተሉና ለእኔ አይደለም ለጁለይቢብ ነው አሉት የልጅቷ
አባት ኩምሽሽ አለ ማመን አቃተው በጣም የሚወዳትን ልጁን ለጁለይቢብ!!? እስቲ እናቷን ላማክርና መልሱን ይዤ እመለሳለሁ ብሎ ወጣ
እናቷ ዘንድ ሄደና ረሱል ልጅሽን አጭተዋል ሊድሯት ፍላጎት አላቸው አላት ማንነው ልጁን ነብይ እንድታገባ የማይፈልገው ብላ ተደሰተች ነገር ግን ረሱል ልጅሽን
የፈለጓት ለራሳቸው አይደለም ለጁለይቢብ ነው ሲላት የሚለውን ቃል ማመን ተሳናት በሀሳብ ተከዘች ለዚህ ምስኪን መዳሩ አሳሰባት ልጃችንን ከጁለይቢብ የተሻለ
ጠይቆ ስንቱን መልሰናል አሁን ደግሞ ለጁለይቢብ ልንድር ፈፅሞ አይሆንም በማለት ስትናገር ባሏ ትቷት እናት አልተስማማችም ብሎ ለረሱል አሚን
ሊነግር ወጣ ይህን ሁሉ ተደብቃ ስትሰማና ስትታዘብ የነበረችው በጥሩ
ስነምግባር የታነፀችው ድህነትን እንደ ወላጆቿ የማትፈራዋ እንስት ትእግስቷ አልቆ ድምጿን ከፍ አድርጋ አባታም
እናታም በጆሮአቸው ሳይሆን በልባቸው እንዲሰሟት የአላህ መልዕክተኛ ውዴታና ፍቅር አይኗን ብቻ ሳይሆን ቆዳዋንም
፥ስጋዋን፥አጥንቷንና የደም ስሯን እንኳን ሳይቀር እንዲያነባ ባስገደደው ስሜቷ ማነው እኔን ያጨኝ በማለት አባቷን
ጠየቀች አባታም ረሱል በማለት መለሰላት
ታዲያ የረሱልን እጩ ትመልሳላችሁን!? እኔ ተስማምቻለሁ ረሱል የወደዱልኝን ተቀብያለሁ በማለት ተናገረች ወደ ረሱል ተያይዘው ሄዱ በመዲና በኑሮ ደረጃው የመጨረሻው ከሆነው ሰው ጁለይቢብ ጋር ተጋባች
የአላህ መልዕክተኛም እጃቸውን ወደ ሰማይ ዘርግተው ያ!
አላህ ኸይራትን በላያቸው ላይ አፍስባቸው ኑሮአቸውንም
ችጋር አታድርገው በማለት ዱዐ አደረጉላቸው ጁለይቢብ ባገባት በጥቂት ቀናት ጂሀድ ታወጀ ወደ ጦር ግንባር ዘመተ ከጠላት ጋር ገጠመ ጦርነቱ እንደተጠናቀቀ
ሁሉም ሰሃባ የዘመድ ጋደኛውን ሬሳ ይፈልጋል ነገር ግን የጁለይቢብን ሬሳ የሚፈልግ አልነበረም ረሱል
አሚን ጠጋ ብለው ማንን እየፈለጋችሁ ነው ብለው ሲጠይቁ እገሌ እገሌን በማለት ስም ዝርዝር ሲጠቅሱ
ጁለይቢብን ማንም አላስታወሰውም ረሱል(صلى الله عليه وسلم )
የተቦጫጨቀው የጁለይቢብ ጀናዛ ላይ ቆመው <<አንተ
ከኔ ነህ እኔም ካንተ ነኝ>>አሉ
አነስ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ሲናገሩ ቀብሩን ቆፍሩለት ብለው አዘዙን እስክንቆፍር ድረስ መሬት ላይ ተቀመጡ የጁለይቢብን ጀናዛ በሁለት ክንዶቻቸው ደግፈው ይዘውት ነበር ከጁለይቢብ ጋር የፍቅር ጊዜዋን በአግባቡ ያላጣጣመችው ሚስት ዒዳዋን እንደጨረሰች ትላልቅ
ሰሀባዎች ሊያገቧት ሢሻሙባት ነበር ብሏል ሱብሀን አሏህ አንቱ የትልቁ የትንሹ የወፍራሙ የቀጭኑ የጥቁር የነጩ የሰውዘር በሙሉ እኩልነትን ያሰፈኑ ታላቅ ነብይ ሆይ የአሏህ ሶላትና ሰላም ባንቱ ላይ ይስፈን ።
ከዚህ በታች ያለውን ሊንካችንን በመጫን ይቀላቀላሉ
https://t.me/FKR_ESKE_JENET
2.5K viewsedited 15:47