Get Mystery Box with random crypto!

እጅ ሰጠሁ ለአላህ ይቅር በለን አላህ ማረን ያከሪሙ ወንጀላቺን በዝቶ እራቅን ከኢልሙ አላህን እ | ፍቅር እስከ ጀነት 📝 🅡𝙖𝙢𝙖𝙨 𝙖𝙡-𝙝𝙖𝙣𝙖𝙣𝙞 🌹

እጅ ሰጠሁ ለአላህ

ይቅር በለን አላህ ማረን ያከሪሙ
ወንጀላቺን በዝቶ እራቅን ከኢልሙ

አላህን እረስተን ለነብስያ እያደርን
በወንጀል በመዝቀጥ ከአላህ ተጣላን

አላህ ይፈትናል የሚወደው ባርያውን
ወደሱ ለማቅረብ ለባሪያው ሊያዝን ፡፡

መሀሪ አዛኝ ነው ለተመላሽ ባሮቺ
እኛም እንመለስ ምንም ሳንሰለቺ

አላህ ጌታችን ነው የአለማት ንጉስ
መመለሳቺን አይቀር ሰዓታችን ሲደርስ

እናማ እጅ ሰጥቻለሁ ማረኝ ያረሂሙ
ዳግም እንዳልመለስ ጠብቀኝ ከሪሙ

https://telegram.me/FKR_ESKE_JENET