Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር መንገድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ fkr2727 — የፍቅር መንገድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ fkr2727 — የፍቅር መንገድ
የሰርጥ አድራሻ: @fkr2727
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 450

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-15 22:51:18 ​​​​​​┄┉✽‌ ✿ምኞቴ ‌✽‌┉┄
    
       ▬▬▬❁ ክፍል ሁለት ❁▬▬▬

....የፍቅርን ሸማ ለብሶ ለኤዲ መዉደድን አጉርሶ በመኖር የተካነዉ ቢኒያም ይሄ ፍቅር
አሰጣጡ ረድኤት እንድትወደዉ አድርጓታል፡፡
ሁሌም ስለሱ ታስባለች ከቤት የሚወጣበትን ሰዓት እየጠበቀች ታየዋለች... ወደ ስራ ሲሄድ
እሷም እንደ ኤዲ ከአይኗ እስኪጠፋ ድረስ በአይኗ ትሸኘዋለች!፡፡
... ቀኑ እሁድ ቀን ነበር ረፋድ አከባቢ የረድኤት እናትና አባት ከቤታቸዉ በረንዳ ላይ በልጃቸዉ
ፍላጎት ቡና እየጠጡ ነዉ፡፡ ጨዋታዉ ደምቋል፡፡ የረድኤት እናት (እማማ በለጡ) የልጅነት
ቁንጅናቸዉ ዛሬም አለ፡፡ ፊታቸዉ ላይ ፈገግታቸዉ ያሳብቅባቸዋል፡፡ እሳቸዉን አይቶ ረድኤትን
"ልጃችሁ ናት?" ማለት አስፈላጊ አይደለም፡፡ ረድኤትን በካርቦን አስደግፈዉ የሳሏት እንጂ
አምጠዉ የወለዷት ብቻ አትመስልም፡፡
... ኤዲ አስከዛሬ ብቻዋን የምሰራዉን ስራ ዛሬ በቢኒ አጋዥነት ቤታቸዉ በረንዳ ላይ እቃ
ያጥባሉ፡፡ የነ ረድኤት ቤትና የነ ቢኒ ቤት ፊት ለፊት ስለሆነ ከቤት ዉጭ የሚደረጉ ነገሮች
እያንዳንዳቸዉ ይተያያሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ረድኤት ቡና ማፍላቷን ረስታ በነሱ ፍቅር ተስባ
በመተዛዘናቸዉ ተደምማ ዛሬም 'ኧረ የኔ በሆነ" አይነት ስሜት ታያቸዋለች፡፡
... ቢኒ በስራቸዉ መካከል ሚስቱን ዉሃ ረጨት እያረገ ይቀልዳታል፤ በመሃል ደሞ
ስራቸዉን ረስተዉ ይተያያሉ፡፡ በስስት ያያታል ሳያወሩ በአይን ይግባባሉ፡፡ እሷን ሲመለከት
ልቡ ቦታዉን ለቆ አይኑ ላይ የመጣ ይመስላል፤ የአይኖቹ ብሌን ልብ ቅርፅ ይሰራሉ ምንም
አይነጋገሩም ግን በአይኖቻቸዉ ፍቅርን ያዜማሉ፡፡
... የሚገርመዉ ግን ሶስተኛ አይንም ነበረ፡፡ ረድኤት! ... ረድኤትም በኤዲ ቦታ ራሷን ተክታ
ቢኒን ታየዋለች የራሷ ባል አስኪመስላት በስስት ታየዋለች፡፡ በሃሳብ ተጉዛ ራሷን ከቢኒ
ጋር አርጋ ነዉ የምታስበዉ፡፡ እናቷ ሲጠሯት እንኳ አሰማም፡፡ እማማ በለጡ ተጣሩ "ረድኤት"
ዝም መልስ የለም እሷ ክንፍ አዉጥታ በራለች ዘመናትን ተሻግራ ከቢኒ ጋር ተጋብታ፤
ቆንጅዬ ልጆችን ወልዳ........... በሀሳብ ጭ.... ልጥ ብላች፡፡
እናቷ እየተጣሩ ነዉ፡፡ "ረድኤት" "ኧረ ረድኤት" ብለዉ ሲጮሁ ደንግጣ ከሃሳቧ ብትት
ከእንቅልፏ ንቅት አለች፡፡ ነገሩ የእማማ በለጡ አጠራር የልጃቸዉን ብቻ ሳይሆን
ጥንዶቹንም አስደንግጧቸዋል፡፡
ቢኒ በስስት ኤዲን እየተመለከታት "አንቺ ባትኖሪኮ ምን እንደምሆን ሳስበዉ..." ብሎ
ሳይጨርሰዉ ኤዲም "ከእኔ የተሻለች ፈጣሪ ይሰጥህ ነበር" አለችዉ፡፡
ቢኒ ሁሌም ቢሆን "ከኔ የተሻለች..." ስትል አይወድም፡፡ ምክንያቱ ደሞ ከእሷ የተሻለች
ሴት አለ ብሎ ማሰብ ስለማይፈልግ፡፡

..."ፈቲዬ አንቺ ደሞ በዚች ቃል ሁሌ ታናጅኛለሻ?" እሷም ወሬ ለማስቀየር... "የኔ ማር..."
ስትለዉ "እንደዉም ካንቺ የተሻለች አገባለሁ" ሲላት ንዴቱ ወደራሷ ዞረና "ሂድ" ብላ ዉሃ
ረጨችበትና አኮረፈች፡፡
ኤዲ ስትስቅም ስታኮርፍም በጣም ዉብ ናት፡፡ ካኮረፈች ደግሞ እንደ ህፃን ልጅ ያረጋታል ፡፡
ቢኒም ማባበል ጀመረ ቶሎ እንደማትስቅ ስለገባዉ ልመናዉን ተወና ለቅጣቱ ተዘጋጀ፡፡....
እሷ አታወራም አኩርፋለች "ዛሬ ራሴን ራሴ ነኝና የምቀጣዉ፡፡ ተመልከቺኝ ..." ብሎ እንደ
ህፃን ልጅ ተንበረከከ እጁንም ወደላይ አርገበገበ፡፡ አሁንም እንዳኮረፈች ናት ከዚያ
አጎበደደና ጆሮዉን ሲይዝ ኤዲ በሳቅ ፍርስ አለች፡፡
... ረድኤትና ቤተሰቦቿም "ምንድነዉ ያሳቃት?" ብለዉ ሲመለከቱ... 


          አስተማሪ የፍቅር ታሪክ
             
ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል ካነበባቹ በኋላ #SHARE ሳታደርጉ አትለፉ::
  
ክፍል 3..... ይቀጥላል

ክፍል 2 እንዲለቀቅ ሸር በማረግ ተባበሩን....
#የፍቅርመንገድ @የፍቅር_መንገድ @Fkr2727
97 viewsedited  19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 09:02:14
ማደግህን አታቁም!
(የፍቅር መንገድ)

አጋጣሚዎችን መፍጠር ፣ የተለያዩ አማራጮችን መሞከር ፣ እራስን ማብቃት ፣ እራስን ማሳደግ ፣ ከፍ ማለት የየለት ተግባሩ የሆነ ሰው ሁሌም እድገቱ ይቀጥላል ፤ ነገዎቹ በሙሉ ከዛሬ የተሻሉ ናቸው ። ነገር ግን ማሰብና መመኘት ብቻውን ምንም ላያመጣለት ይችላል ።

አዎ! የአንድ ሰው ትልቁ እስር ቤት አዕምሮው እንደሆነ ይታወቃል ። ከለመደው ሰራ ሊወጣ ቢፈልግ ፣ ከለመዳቸው ሰዎች መለየት ቢያስብ ፣ አዲስ ነገር መሞከር ቢፈልግ ፣ የመጀመራው እንቅፋቱ የገዛ እሳቤው ነው ። ዛሬ ከሚኖረው ህይወት የተሻለ ሌላ ህይወት መኖሩን አንዲያስብ አይፈቅድለትም ፤ ቢያስብም እንቅስቃሴ እንዲጀምር አያደርገውም ። የስራው በሃሪ ከእራሱ አስተሳሰብ ጋር ተደምሮ ከሳጥን /box/ ውጪ እንዳይመለከት ያደርገዋል ።

አዎ! አብዛኛው ሰው የሚሰራውን ስራ ፣ የሚኖረውን ኑሮና እለት እለት የሚያሳልፈውን ድግግሞሽ አይወደውም ። ከዛ የመላቀቅ ድፍረቱና ቆራጥነቱ ስለጎደለው ብቻ ያልተመቸውን እንደተመቸው ፣ ያልተስማማውን እንደተስማማው ፣ ያላስደሰተውን እንዳስደሰተው በማሰብ ይኖረዋል ።

አዎ! ጀግናዬ..! ማደግህን አታቁም!ከአዕምሮህ አጥር ውጪ መመልከት ጀምር ፤ የዛሬውን ያለመመቸት ከመመቻቸትና ከመላመድ ይልቅ የተሻለውን ምቾት ወደመፈለግ ግባ ፤ የትም ብትሆን ፣ ምንም ብትሰራ ያንተ ህይወት ሃላፊነት የእራስህ ብቻ ነው ። ላለማደግህ ፣ ላለመቀየርህ ፣ ላለማወቅህ ፣ ላለመደሰትህ ፣ ላለመርካትህ ካንተ ውጪ ሌላ ተጠያቂ አካል የለም ። ተደላድሎ የተቀመጠን ማንም አይረዳውም ፤ ተመቻችቶ የተኛውን ማንም አይቀሰቅሰውም ፤ እንዳልደላህ በመልፋት አሳይ ፤ እንዳልተመቸህም በመንቃት አሳይ የሚያግዝህ የሚረዳህም የእራሱን ድርሻ እንዲወጣ አድርግ
114 views06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 20:41:11 ሁለት ሰዎች ናቸው አሉ,,,,,,, አሉ ነው ደሞ!!!!!

መንገድ እየሄዱ ድንገት የሆነ ቆሻሻ ነገር መሬት ላይ ያያሉ,,,,,

ምንድነው?? ሲሉ ተፋጠጡ

አር ነው,,,,, አለ አንደኛው

አይደለም ሲል ሞገተ ሌላኛው,,,,

ነው!!!
አይደለም!!!

የሚል ክርክር ገጥመው ቆዩና ቀምሰው ምንነቱን ለማረጋገጥ ተስማሙ,,,,

እናም በቅምሻቸው ያዩት ነገር አር መሆኑን ሲገነዘቡ ሁለቱም እኩል,,,,,,

እነኳንም አረገጥነው!!! ሲሉ ፈነጩ

እና ምን ለማለት ነው ጎበዝ,,,,,

ከአፋችን ለሚወጣውም ሆነ ወደ አፋችን ለምናስገባው ነገር ጥንቃቄን እንውሰድ

ስድብ እኮ የእገሌ ልጅ አያስብልም!!!

ሰናይ ቅዳሚት ውዶቼ!!!
103 views17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 20:40:48
እያንዳንዱን ምሽት ተከትሎ መንጋቱ የማይቀር ነው!!!!

የፀሀይን ግባት ተከትላ ጨረቃ መውጣቷ የተፈጥሮ ሂደት ነው!!!!

ማንም ቢተኛ ተፈጥሮ እስካልገደበችው ድረስ መንቃቱ ግድ ነው!!!

በርግጥ ተስፈኞች ከሞት በኋላም ህይወት መኖሩን ያምናሉ!!!!!

የቱንም ያህል ቢሆን ጥልቀቱ ሀዘን ያጎሳቆለው,,,, በእንባ ብዛት አይኑ የሟሸሸ ሰው ፈገግታን የሚለግሰው ቢያገኝ ጥርሱ ነጭ ነው!!

"ብለነው ብለነው ካልሆነ ነገሩ
መተኛት ደግ ነው በሉ ደህና እደሩ!!!"
98 views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 17:05:25
የአንዳንድ ሴቶች ሚስጥራዊ ፖስቶችና ፍቻቸው 2
(የፍቅር መንገድ)

‹‹እግዚአብሔር ደቡብ ክልልን እንዴት እንደባረከው ተመልከቱ…. ከተፋቀርን አገራችን ምድራዊ ገነት ናት ...ፍቅር ይስጠን ›› ከሚል ካፕሽን ጋር በሚያማምሩ ጣቶች ማንጎ ይዛ እጅና ማንጎው ብቻ የሚታይበት ፎቶ ከለጠፈች ! ብራዘር ኮሜንት ላይ ‹‹ዋው ማንጎው እንዴት ያስጎመዣል መግመጥ ነበር ›› ብለህ ከፃፍክ …. እመነኝ ልጅቱ ብሎክ ከማድረጓ በፊት በሆዷ ‹‹ጅብ ይግመጥህ ሆዳም ድሮም ወንዶች የሆዳቸው ነገር ….›› እንደምትል አትጠራጠር! አንተኮ ስለደቡብ ክልል አቀማመጥ ስለሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ምናምን ትዘባርቅ ይሆናል ኧረ በፈጠረህ ! …ጉዳዩ ወዲህ ነው …

ጥፍሯን ስንትና ስንት ብር ሆጭ አድርጋ ተሰርታ ያለ የሌለ ሎሽን ተቀብታ ...ማታ ቫዝሊን ተቀብታና በኩርቱ ፌስታል ጠቅልላ ቦክሰኛ መስላ ተኝታ ሁሉ ...እንዲሁም ውድ የቃልኪዳን ቀለበት አድርጋ ፎቶ የለጠፈችው ማንጎ ለማስተዋወቅ አይደለም …(እንዴ ምን ነካህ) …የጣቶቿን አለንጋነት የማድነቅ አበሻዊ የቅኔ ሊቅነት ይጠበቅብሃል ፣ ቀለበቷን አድንቀህ እንዴት ፕሮፖዝ መደረግሽን ሳትነግሪን ምናምን ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ በል ! የግድ ስለማንጎ ማውራት ከፈለክ ግን ‹‹እንዴት እድለኛ ማንጎ ነው በእነዚህ ውብ ጣቶች የተከበበ ›› ማለት አትርሳ ….እመነኝ ከዛ በኋላ የሰፈርህ ልጅ የአጎቱ ሚስት በእርጅና ምክንያት እንደሞቱ ገልፀህ ፖስት ብታደርግ ሁሉ ፕሮፋይል ፒክቸሯን ለሶስት ቀን ጥቁር የምታደርግ ጓደኛ ታፈራለህ ! ማን ያውቃል ቀለበቱም እንዲሁ ለሰው አይን ሊሆን ይችላል ፎቶ አትይ ፎቶ አንብብ!!
99 views14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 07:42:38 ​​​​┄┉✽̶ ✿ምኞቴ ̶̥✽̶┉┄
    
       ▬▬▬❁ክፍል አንድ▬▬▬

           ... ረድኤት ከረፋዱ አራት ሰዓት አከባቢ የቤታቸዉን በረንዳ በማፅዳት ላይ ሳለች የግቢያቸዉ
በር ተንኳኳ፡፡ ማን ሊሆን ይችላል? ብላ እያሰበች ወደ በሩ ተጠጋች "አባዬና እማዬ ዛሬ የስራ
ቀን ስላልሆነ ቤት ዉስጥ ናቸዉ፡፡" እና ማን ነዉ? እያለች የግቢዉን በር ጠጋ አለችና "ማን
ነዉ?" አለች "እኔ ነኝ" የሚል ለስላሳ ድምፅ ከዉጭ የተሰጣት መልስ ነበር፡፡ ድምፁን
ከዚህ በፊት ባታዉቀዉም ሰላም ያለ ሰዉ እንደሆነ በድምፁ ስለተረዳች በሩን ከፈተችለት፡፡
በጣም ቆንጅዬ ወጣት ነበር፡፡  "ደህና ነሽ" አላት፡፡ እሷም "ደህና ነኝ" ብላ
ስትመልስለት "የሚከራይ ቤት አለ ብለዉኝ ነበር... አለ እንዴ?" ሲላት የረድኤት አባት
ለረዢም ሰዓት በር ላይ እንደቆመች ስላዬ
"ማን ነዉ?" እያሉ ወደ በሩ ተጠጉ፡፡ ወጣቱንም ባዩ ጊዜ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ
ወጣቱ ልጅ ለረድኤት የጠየቃትን ጥያቄ ለአባቷ ለጋሽ ሀብታሙ ደገመላቸዉ፡፡ ጋሽ ሀብታሙም አለ ወደውስጥ ግባ ልጄ፡፡ አሉት  እሺ ብሎ ገባ የሚከራየውን ቤት ገብቶ አየ ስንት እንደሚከራይ ጠየቃቸውና ተስማምተው ቢኒያም ወደ ቤት ተመለሰ ፡፡ ... ከዚህ ጊዜ በኃላ ነበር ረድኤት ቢንያምን ያወቀችዉ፡፡ ቢንያም እጅግ በጣም ዉብና
ማራኪ ልጅ ነዉ፡፡ ሚስቱ ደግሞ ኤደን ትባላለች፡፡ እጅግ ሲበዛ ዝምተኛና ቆንጂዬ ናት፡፡ ቤት
ስለምትዉልና ረድኤትም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ብትሆንም ሰመርን ከቤተሰቦቿ ጋር ስለምታሳልፍ ሁሌም አብረዉ ይዉሉ ነበር፡፡
ኤዲ ምንም ያክል ዝምተኛ ብትሆንም ለባሏ ግን ፍቅርን መስጠት የምትችል፤ በተለይ
ሲጫወቱና ሰዉነቱ ላይ እየተንከባለለች ቅብጥብጥ ቅብጥ፤ ሽፍድ ስትልበት... ረድኤት "እኔ በሆንኩ" ብላ ትቀናባታለች፡፡ .
.
..... ቢኒያም ከስራ ሊመጣ አከባቢ ኤዲ እጅግ በጣም ተዉባ ከወትሮዉ በተለዬ ይበልጥ
አምራ የግቢዉን በር ለመክፈት ከቤቷ ወጥታ በሯ አጠገብ ትቀመጣለች፡፡ ልክ በሩ
እንደተንኳኳ ሩጣ ትሄድና ቶሎ ትከፍታለች፡፡ ቢኒያምም እቅፉ ዉስጥ አስገብቶ ሲስማት
ለተወሰነ ሰዓታት የተለያዩ ሳይሆን ለአመታት ተራርቀዉ ተነፋፍቀዉ የተገናኙ ይመስላሉ፡፡
ቢኒያም ፍቅር መስጠት ተክኖበታል፡፡
ሲያፈቅራትና ሲወዳት ምድር ላይ ሌላ ሴቶች እስከመፈጠራቸዉም ረስቶ ነዉ፡፡ ለሱ ሴት
ማለት እሷ ብቻ ናት፡፡ እንደ እናት ያከብራታል፤ ያፈቅራታል በጣም ይሳሳላታል፡፡ ፍቅራቸዉ
እንኳን አብሯቸዉ ለሚኖር ሰዉ ለአንድ ቀን በመንገድ ላይ ያያቸዉ ራሱ ይቀናባቸዋል፡፡
.
....ከግቢዉ ነዋሪም ጋር በጣም ተግባብቷል፡፡ ጋሽ ሀብታሙ ለብቻቸዉ ባገኛቸዉ ሰዓት "አባባ
ገና ወጣት ነህ አረጁ የሚል ሰዉ ተሳስቷል፡፡ አሁን እኔ እና አንቱ ሩጫ ብንሽቀዳደም
አዝነውልኝ ካልተዉልኝ በስተቀር ትበልጡኝ የለ እንዴ! አንቱኮ ሀይሌ ገ/ስላሴን ያስንቃሉ፡፡" እያለ
ይቀልዳቸዋል፡፡ እሳቸዉም የወጣትነት ጊዜያቸዉ ታዉሷቸዉ በጨዋታዉ ከሳቁ በኃላ "አይ
ልጄ..." ብለዉ ትረካቸዉን ይጀምራሉ፡፡ ለወሬያቸዉ አክብሮ ጆሮ ስለሰጣቸዉ ከስራ
የሚመለስበትን ሰዓት እንደ ኤዲ እርሳቸዉም ይጠባበቃሉ፡፡ በተለይ ደሞ ረድኤት...!

           አስተማሪ የፍቅር ታሪክ
   ......ክፍል 2 ይቀጥላል....

ክፍል 2 እንዲለቀቅ ሸር በማረግ ተባበሩን....

የፍቅር መንገድ
https://t.me/fkr2727

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share የፍቅር መንገድ
https://t.me/fkr2727
የፍቅር መንገድ
https://t.me/fkr2727
┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄
112 views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 20:42:04 እስቲ ይሄን የታፈነ ቤት መስኮቶቹን ከፋፍተን ውጭ ላይ የበቀሉ አበቦችን እንመልከት
(አሌክስ አብርሃም )

1ኛ . እስካሁን ፌስ ቡክ ላይ ፖለቲካን እንደስነፅሁፍ የሚያሽሞነሙኗት ብዙ ፀሃፍት አይቻለሁ ! ለእያንዳንዷ ለሚናገራት ነገር መረጃ እያቀረበ በሰለጠነና ፍፁም ጨዋነት በተሞላበት መንገድ ሃሳቡን የሚገልፅ ሰው ግን እንደዚህ ልጅ አላየሁም ! ሳውቀው ጀምሮ አቋሙ አይወላውልም ! በአማርኛም በእንግሊዝኛም ሲፅፍ ቋንቋው የተመረጠና በሳል ነው ! የሚመርጣቸው ቃላት ሁሉ ይገርሙኛል ! የፖለቲካ አቋሙ ምንም ይሁን ምን የሚያስቀምጥበት መንገድ ግን ግልፅ እና እምቅ ሃሳብ ያዘለ ነው ! ማንንም ያከብራል ! አሁን ካሉት የፖለቲካ ፀሃፍት ውስጥ ነብሴ የምታከብረው ምርጥ ሰው ነው ! Abenezer B. Yisihak


2ኛ . አጠር ያሉ ጉዳዮችን ቅልብጭ ባለ አገላለፅ ያስቀምጥና ሌላውን እንድታስቡበት ሃሳብ ጭሮባችሁ ያልፋል ! ምን ይሄ ብቻ ምርጥ ፅሁፍ ካየ ወደግድግዳው ሸር አድርጎ ያላየ እንዲያየው ይጋብዛል ! ደግሞ ስጠረጥር ስእልም ሳይሞክር አይቀርም ….ምርጥ ሃሳብ ማየት የሚችል ሰው ነው ! እውነቱን ለመናገር ፌስቡክ ላይ ፈልጌ አፈላልጌ ‹‹የት አባታቸው ሄዱ አሁን እዚህ አልነበሩ ፡) እያልኩ ከማነባቸው ሰወች አንዱ ነው ….. እንደውም የሆነ በቅርብ በአካል የማውቀው ልጅ ሁሉ ይመስለኛል ……አድናቆት ያበዛሁበት ከመሰላችሁ አሁኑኑ በዚህ አድራሻው ሂዱና አይታችሁት ውሸት በሉኝ ! ግርማሥላሴ ሰይፉ ጂብራን

3ኛ. በምትፅፋቸው ነገሮች ጥራትና ብቃት ጥርጥር የለኝም ! ጎበዝ ናት እንደውም ስነፅሁፍና የፖለቲካው አንጃ ግራንጃ ፌስ ቡክ ላይ የተሳሰሩባት ቀጭን ክር ትመስለኛለች ! የፖለቲካ አቋሟ ምንም ይሁን ምን አፃፃፏ ግን ደስ ይለኛል ጓደኛዋ ካልሆናችሁ ይቻት Elsa Legesse

4ኛ . በስራው አዲስና የቆዮ መፅሃፍትን ሰብሳቢ …ሻጭ ነው ! ግርም የሚለኝ በጎነት የሞላው ልጅ …. መፅሃፍ ልትገዙ ሂዳችሁ ስለመፅሃፍ እያወራችሁ ቁጭ ያደርጋችኋል አንዳንዴ ነጋዴ ሁሉ አይመስለኝም ! ከምር መፅሃፍቶች እንዲነበቡ የሚመኝ ወጣት ነው …የጠፉ መፅሃፍቶችን ሰብስቦ የመፅሃፍት አውደ ርእይ ያዘጋጃል ፡፡ ገበያ ላይ የማይገኙ መፅሃፍት ካገኘ (ደግሞ ያገኛል ) ልክ እንደህፃን ልጅ በስርአት መርጦ በእንክብካቤ ያስቀምጧቸዋል ብሎ ለሚያስባቸው ደንበኞቹ ይሰጣል ! በአካል አውቀዋለሁ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አለፍ እንዳላችሁ ታገኙታላችሁ ፌስቡክም ላይ ይሄው Mexico Book Corner

5ኛ . ትዝብቶች አጫጭር ታሪኮች አልፎ አልፎም ግጥሞች ይፅፋል በጎ አሳቢ እናም ያመነበትን በራሱ መንገድ ሳያቋርጥ የሚፅፍ ልጅ ነው ጓደኞቹ ብትሆኑ ባሏችሁ ላይ አንድ ጎበዝ ልጅ ጨመራችሁ ማለት ነው! ሶፎንያስ ሆሳዕና

6ኛ . እንደኳስ በህይወቴ የምጠላው ነገር የለም ! የኳስ ወሬ የኳስ ዜና … ገና በሩቁ ያንገሸግሸኛል ! ግን አሁን የማስተዋውቃችሁ ልጅ ብዙ ጊዜ ሴት ጋዜጠኞች የማይዳፈሩትን የስፖርት ዜና ያውም በራሷ ተነሳሽነት ከሽና የምታቀርብ ጠንካራ ልጅ ናት ! ወቅታዊ የአገር ውስጥ የስፖርት ጉዳዮችንም እዚሁ ፌስቡክ ላይ ትፅፋለች በሬዲዮ ስለስፖርት ጠንካራ ትችት ስትሰጥም ሰምቻት አውቃለሁ Nura Ye Juhara Lej ብርታቷ ይገርመኛል !

7ኛ . ፖለቲካ ላይ እንደዚህ ልጅ ያላገጠባት ሰው የለም ! ዘና ብሎ ማለት የሚፈልገውን ይላል ….አንዳንዴ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሃሳቡን ሰርቀው ሳያስፈቅዱ አለም አቀፍ መድረክ ላይ በማቅረባቸው መበሳጨቱን ሁሉ በመግለፅ በዚህ ሃዘን ምክንያት ፕሮፋይል ፒክቸሩን ሊያጠቁር ይችላል ! እንዲህ በዋዘኛ ታዲያ የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮችን ያነሳል ይጥላል ‹‹የዚህ ትውልድ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ›› በዚህ ልጅ የአቀራረብ ፎርማት ቢቀርብ ‹‹የኤድናሞል ትውልድ ሳይቀር ፖለቲከኛ ይሆን ነበር ›› ...... ፍሰሃ ደስታ

8ኛ . ማንም ሰው የሚናገረውን ነገር መልሶ ሲናገረው አዲስ ያስመስለዋል ! ይሄ ልጅ ፖለቲካ ሲፅፍ በጎ በጎውን እያየ ነው …. ሲቃወምም ሲደግፍም ምክንያታዊ በዛ ላይ ለሚናገረው ነገር ከምር ይጨነቃል ! መንግስትን ደግፎ በርካታ ጉዳዮችን በግልፅ ያስቀምጣል ያልጣመውንም ነገር ሲፅፍ አለመጣሙ እንዲጥመን አድርጎ ነው ... በሳል ትንታኔውን እወድለታለሁ …ወዳጆቹ ሲያቆላምጡት ‹‹ሙክታሮቪች ›› ይሉታል Muktar Ousman Adem ሙክታር ‹‹ኢትዮጲያ 22.5 በመቶ እድገት አስመዘገበች ቢለኝ አምነዋለሁ ! ምክንያቱም ኡስማን ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት በላይ ኢትዮጲያን የመውደድ መንፈስ የተጠናወተው ልጅ ስለሚመስለኝ ነው !!

9ኛ .መጀመሪያ አካባቢ ‹‹ጠጅ ጠላ እብድ ወፈፌምናምን ›› ስለምትል አየጭጭ የምን መቀዣበር ነው ብየ አይንሽን ላፈር ብያት ነበር …(ለምን ይዋሻል) በኋላ የምትፅፈቸውን ፅሁፎች ሳይ የመጨረሻ ነቋሪ…. እይታዋ የሚገርም ልጅ ሁና አገኘኋትና የምትለጥፋቸውን ማንበብ ጀመርኩ እላችኋለሁ ! አሪፍ ነቋሪ ነች … ያውም ዘና ያለች እንደው ስጠረጥር እግረ መንገዷን ምናምን ወርወር አድርጋ ስለምትጠፋ እንጅ መረር አደርጋ ብትፅፍ ፌስ ቡክ ላይ ካሉን ሴት ፃህፍት የመጀመሪያውን ቦታ እንደምትይዝ አልጠራጠርም Lemlem Megerssa ነገሮችን እንግዳ በሆነ መነገድ ነው የምትመለከተው !

10ኛ . ያቆየሁት ስለሱ ምን እንደሚባል ግራ ገብቶኝ ነው …አረብ አገር ያለውን ሰቆቃ ልሳን ሁኖ የሚናገር በፅሁፍም በተግባርም ስራው ከሚነገርለት በላይ የሆነ ምርጥ ሰው ! ይሄ ልጅ ‹‹ የሴቶች መብት እኩልነት ›› እያለ የፈለገውን ቢነግረኝ በደንብ ነው የምሰማው ….የተግባር ሰው ነው ! አይሰለችም ወደአገራቸው በተለያየ ምክንያት መመለስ ያቃታቸው ሚስኪን እህቶችን ሰዎችን በማስተባበር የአገራቸውን አፈር እንዲረግጡ በማድረግ እየከፈለ ያለው መስዋእትነት ያስደምመኛል … ስለሱ ምንም ማለት አልችልም ! ከምር በትክክል ስለሴቶች የሚገደው አካል ቢኖር ለዚህ ልጅ ያለምንም ግነት ሃውልት ባቆመለት ነበር እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን ከልቤ አከብርሃለሁ !! Nubiya Kush Kedamawi

═══════❁✿❁ ═══════
ለምርጥ ጽሑፎች በማንኛውም ሶሻል ሚዲያ ጭምር ቻናላችንን ግቡና #Join #Shere አድርጉ ።

http://facebook.com/abrsh2727
http://twitter.com/abrsh2727
http://tiktok.com/@abrsh2727
http://instagram.com/@abrsh2727
https://t.me/abrsh272
እንደምወዳችሁ ታውቃላችሁ አ
═══════❁✿❁ ═══════
144 views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 20:14:28
ይህን በፎቶ ላይ የምታዩት ወጣት ሳምሶን ንጉሴ ይባላል ሁለቱም ኩላሊቶቹ መስራት አቁመዋል ይህን ታዳጊ ወጣት ለመርዳት የ100 ብር challenge ታስቦአል ! ስለዚህ ከታች ባለው በራሱ አካውንት 100 ብር በማሥገባት ያስገባችሁበትን ደረሠኝ ኮመንት ላይ አስቀምጡልኝ
1000097322396(ንግድ ባንክ)
በሞባይል ባንኪንግ መጠቀም ትችላላችሁ
ለመርዳት የምትፈልጉ ወገኖች
0964471413
#የፍቅርመንገድ #የፍቅርመንገድ
165 views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 20:14:07
132 views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 19:53:14
❖ ሲዖል ባዶ ነው ፤ ምክንያቱም ሁሉም ዲያብሎሶች ያሉት
እዚህ ምድር ላይ ነው።
✎ ከክፋት ስትርቅ ሰላምህን ታበዛለህ ፤ ቅንና መልካም ስትሆን
ደግሞ ከጭንቀትና ከጸጸት ትድናለህ።
✎ ለማንኛውም ሰው ጆሮህን ስጥ ፤ ድምፅህን ግን ቀንስ ፤
ሁሉንም ውደድ ፤ ጥቂቶቹን እመን ፤ ማንንም ግን አትበድል።
✎ የውሸት ጓደኛና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸው ፤ ሁለቱም
የሚቆዩት ፀሐይ እስካለች ድረስ ነው።
✎ ጨውን ሺ ጊዜ ስኳር ብትለው ስሙን እንጂ ጣዕሙን
መቀየር አይችልም።
✎ የቀንን ውበት አይቶ ለማድነቅ የግድ ጨለማን መጠበቅ
ያስፈልጋል።
✎ መልካም ስም ለሰው ልጅ የመንፈስ ቀንዲል ናት።
✎ ማንም ሰው ህይወት ስህተት ወይም ትክክል መሆኑን
የሚያውቀው ሲፈተን ነው።
#William_Shakespeare


የፍቅር መንገድ !!
140 viewsedited  16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ