Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​┄┉✽‌ ✿ምኞቴ ‌✽‌┉┄             ▬▬▬❁ ክፍል ሁለት ❁▬▬▬ | የፍቅር መንገድ

​​​​​​┄┉✽‌ ✿ምኞቴ ‌✽‌┉┄
    
       ▬▬▬❁ ክፍል ሁለት ❁▬▬▬

....የፍቅርን ሸማ ለብሶ ለኤዲ መዉደድን አጉርሶ በመኖር የተካነዉ ቢኒያም ይሄ ፍቅር
አሰጣጡ ረድኤት እንድትወደዉ አድርጓታል፡፡
ሁሌም ስለሱ ታስባለች ከቤት የሚወጣበትን ሰዓት እየጠበቀች ታየዋለች... ወደ ስራ ሲሄድ
እሷም እንደ ኤዲ ከአይኗ እስኪጠፋ ድረስ በአይኗ ትሸኘዋለች!፡፡
... ቀኑ እሁድ ቀን ነበር ረፋድ አከባቢ የረድኤት እናትና አባት ከቤታቸዉ በረንዳ ላይ በልጃቸዉ
ፍላጎት ቡና እየጠጡ ነዉ፡፡ ጨዋታዉ ደምቋል፡፡ የረድኤት እናት (እማማ በለጡ) የልጅነት
ቁንጅናቸዉ ዛሬም አለ፡፡ ፊታቸዉ ላይ ፈገግታቸዉ ያሳብቅባቸዋል፡፡ እሳቸዉን አይቶ ረድኤትን
"ልጃችሁ ናት?" ማለት አስፈላጊ አይደለም፡፡ ረድኤትን በካርቦን አስደግፈዉ የሳሏት እንጂ
አምጠዉ የወለዷት ብቻ አትመስልም፡፡
... ኤዲ አስከዛሬ ብቻዋን የምሰራዉን ስራ ዛሬ በቢኒ አጋዥነት ቤታቸዉ በረንዳ ላይ እቃ
ያጥባሉ፡፡ የነ ረድኤት ቤትና የነ ቢኒ ቤት ፊት ለፊት ስለሆነ ከቤት ዉጭ የሚደረጉ ነገሮች
እያንዳንዳቸዉ ይተያያሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ረድኤት ቡና ማፍላቷን ረስታ በነሱ ፍቅር ተስባ
በመተዛዘናቸዉ ተደምማ ዛሬም 'ኧረ የኔ በሆነ" አይነት ስሜት ታያቸዋለች፡፡
... ቢኒ በስራቸዉ መካከል ሚስቱን ዉሃ ረጨት እያረገ ይቀልዳታል፤ በመሃል ደሞ
ስራቸዉን ረስተዉ ይተያያሉ፡፡ በስስት ያያታል ሳያወሩ በአይን ይግባባሉ፡፡ እሷን ሲመለከት
ልቡ ቦታዉን ለቆ አይኑ ላይ የመጣ ይመስላል፤ የአይኖቹ ብሌን ልብ ቅርፅ ይሰራሉ ምንም
አይነጋገሩም ግን በአይኖቻቸዉ ፍቅርን ያዜማሉ፡፡
... የሚገርመዉ ግን ሶስተኛ አይንም ነበረ፡፡ ረድኤት! ... ረድኤትም በኤዲ ቦታ ራሷን ተክታ
ቢኒን ታየዋለች የራሷ ባል አስኪመስላት በስስት ታየዋለች፡፡ በሃሳብ ተጉዛ ራሷን ከቢኒ
ጋር አርጋ ነዉ የምታስበዉ፡፡ እናቷ ሲጠሯት እንኳ አሰማም፡፡ እማማ በለጡ ተጣሩ "ረድኤት"
ዝም መልስ የለም እሷ ክንፍ አዉጥታ በራለች ዘመናትን ተሻግራ ከቢኒ ጋር ተጋብታ፤
ቆንጅዬ ልጆችን ወልዳ........... በሀሳብ ጭ.... ልጥ ብላች፡፡
እናቷ እየተጣሩ ነዉ፡፡ "ረድኤት" "ኧረ ረድኤት" ብለዉ ሲጮሁ ደንግጣ ከሃሳቧ ብትት
ከእንቅልፏ ንቅት አለች፡፡ ነገሩ የእማማ በለጡ አጠራር የልጃቸዉን ብቻ ሳይሆን
ጥንዶቹንም አስደንግጧቸዋል፡፡
ቢኒ በስስት ኤዲን እየተመለከታት "አንቺ ባትኖሪኮ ምን እንደምሆን ሳስበዉ..." ብሎ
ሳይጨርሰዉ ኤዲም "ከእኔ የተሻለች ፈጣሪ ይሰጥህ ነበር" አለችዉ፡፡
ቢኒ ሁሌም ቢሆን "ከኔ የተሻለች..." ስትል አይወድም፡፡ ምክንያቱ ደሞ ከእሷ የተሻለች
ሴት አለ ብሎ ማሰብ ስለማይፈልግ፡፡

..."ፈቲዬ አንቺ ደሞ በዚች ቃል ሁሌ ታናጅኛለሻ?" እሷም ወሬ ለማስቀየር... "የኔ ማር..."
ስትለዉ "እንደዉም ካንቺ የተሻለች አገባለሁ" ሲላት ንዴቱ ወደራሷ ዞረና "ሂድ" ብላ ዉሃ
ረጨችበትና አኮረፈች፡፡
ኤዲ ስትስቅም ስታኮርፍም በጣም ዉብ ናት፡፡ ካኮረፈች ደግሞ እንደ ህፃን ልጅ ያረጋታል ፡፡
ቢኒም ማባበል ጀመረ ቶሎ እንደማትስቅ ስለገባዉ ልመናዉን ተወና ለቅጣቱ ተዘጋጀ፡፡....
እሷ አታወራም አኩርፋለች "ዛሬ ራሴን ራሴ ነኝና የምቀጣዉ፡፡ ተመልከቺኝ ..." ብሎ እንደ
ህፃን ልጅ ተንበረከከ እጁንም ወደላይ አርገበገበ፡፡ አሁንም እንዳኮረፈች ናት ከዚያ
አጎበደደና ጆሮዉን ሲይዝ ኤዲ በሳቅ ፍርስ አለች፡፡
... ረድኤትና ቤተሰቦቿም "ምንድነዉ ያሳቃት?" ብለዉ ሲመለከቱ... 


          አስተማሪ የፍቅር ታሪክ
             
ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል ካነበባቹ በኋላ #SHARE ሳታደርጉ አትለፉ::
  
ክፍል 3..... ይቀጥላል

ክፍል 2 እንዲለቀቅ ሸር በማረግ ተባበሩን....
#የፍቅርመንገድ @የፍቅር_መንገድ @Fkr2727