Get Mystery Box with random crypto!

ማደግህን አታቁም! (የፍቅር መንገድ) አጋጣሚዎችን መፍጠር ፣ የተለያዩ አማራጮችን መሞከር ፣ እራ | የፍቅር መንገድ

ማደግህን አታቁም!
(የፍቅር መንገድ)

አጋጣሚዎችን መፍጠር ፣ የተለያዩ አማራጮችን መሞከር ፣ እራስን ማብቃት ፣ እራስን ማሳደግ ፣ ከፍ ማለት የየለት ተግባሩ የሆነ ሰው ሁሌም እድገቱ ይቀጥላል ፤ ነገዎቹ በሙሉ ከዛሬ የተሻሉ ናቸው ። ነገር ግን ማሰብና መመኘት ብቻውን ምንም ላያመጣለት ይችላል ።

አዎ! የአንድ ሰው ትልቁ እስር ቤት አዕምሮው እንደሆነ ይታወቃል ። ከለመደው ሰራ ሊወጣ ቢፈልግ ፣ ከለመዳቸው ሰዎች መለየት ቢያስብ ፣ አዲስ ነገር መሞከር ቢፈልግ ፣ የመጀመራው እንቅፋቱ የገዛ እሳቤው ነው ። ዛሬ ከሚኖረው ህይወት የተሻለ ሌላ ህይወት መኖሩን አንዲያስብ አይፈቅድለትም ፤ ቢያስብም እንቅስቃሴ እንዲጀምር አያደርገውም ። የስራው በሃሪ ከእራሱ አስተሳሰብ ጋር ተደምሮ ከሳጥን /box/ ውጪ እንዳይመለከት ያደርገዋል ።

አዎ! አብዛኛው ሰው የሚሰራውን ስራ ፣ የሚኖረውን ኑሮና እለት እለት የሚያሳልፈውን ድግግሞሽ አይወደውም ። ከዛ የመላቀቅ ድፍረቱና ቆራጥነቱ ስለጎደለው ብቻ ያልተመቸውን እንደተመቸው ፣ ያልተስማማውን እንደተስማማው ፣ ያላስደሰተውን እንዳስደሰተው በማሰብ ይኖረዋል ።

አዎ! ጀግናዬ..! ማደግህን አታቁም!ከአዕምሮህ አጥር ውጪ መመልከት ጀምር ፤ የዛሬውን ያለመመቸት ከመመቻቸትና ከመላመድ ይልቅ የተሻለውን ምቾት ወደመፈለግ ግባ ፤ የትም ብትሆን ፣ ምንም ብትሰራ ያንተ ህይወት ሃላፊነት የእራስህ ብቻ ነው ። ላለማደግህ ፣ ላለመቀየርህ ፣ ላለማወቅህ ፣ ላለመደሰትህ ፣ ላለመርካትህ ካንተ ውጪ ሌላ ተጠያቂ አካል የለም ። ተደላድሎ የተቀመጠን ማንም አይረዳውም ፤ ተመቻችቶ የተኛውን ማንም አይቀሰቅሰውም ፤ እንዳልደላህ በመልፋት አሳይ ፤ እንዳልተመቸህም በመንቃት አሳይ የሚያግዝህ የሚረዳህም የእራሱን ድርሻ እንዲወጣ አድርግ