Get Mystery Box with random crypto!

እስቲ ይሄን የታፈነ ቤት መስኮቶቹን ከፋፍተን ውጭ ላይ የበቀሉ አበቦችን እንመልከት (አሌክስ አብ | የፍቅር መንገድ

እስቲ ይሄን የታፈነ ቤት መስኮቶቹን ከፋፍተን ውጭ ላይ የበቀሉ አበቦችን እንመልከት
(አሌክስ አብርሃም )

1ኛ . እስካሁን ፌስ ቡክ ላይ ፖለቲካን እንደስነፅሁፍ የሚያሽሞነሙኗት ብዙ ፀሃፍት አይቻለሁ ! ለእያንዳንዷ ለሚናገራት ነገር መረጃ እያቀረበ በሰለጠነና ፍፁም ጨዋነት በተሞላበት መንገድ ሃሳቡን የሚገልፅ ሰው ግን እንደዚህ ልጅ አላየሁም ! ሳውቀው ጀምሮ አቋሙ አይወላውልም ! በአማርኛም በእንግሊዝኛም ሲፅፍ ቋንቋው የተመረጠና በሳል ነው ! የሚመርጣቸው ቃላት ሁሉ ይገርሙኛል ! የፖለቲካ አቋሙ ምንም ይሁን ምን የሚያስቀምጥበት መንገድ ግን ግልፅ እና እምቅ ሃሳብ ያዘለ ነው ! ማንንም ያከብራል ! አሁን ካሉት የፖለቲካ ፀሃፍት ውስጥ ነብሴ የምታከብረው ምርጥ ሰው ነው ! Abenezer B. Yisihak


2ኛ . አጠር ያሉ ጉዳዮችን ቅልብጭ ባለ አገላለፅ ያስቀምጥና ሌላውን እንድታስቡበት ሃሳብ ጭሮባችሁ ያልፋል ! ምን ይሄ ብቻ ምርጥ ፅሁፍ ካየ ወደግድግዳው ሸር አድርጎ ያላየ እንዲያየው ይጋብዛል ! ደግሞ ስጠረጥር ስእልም ሳይሞክር አይቀርም ….ምርጥ ሃሳብ ማየት የሚችል ሰው ነው ! እውነቱን ለመናገር ፌስቡክ ላይ ፈልጌ አፈላልጌ ‹‹የት አባታቸው ሄዱ አሁን እዚህ አልነበሩ ፡) እያልኩ ከማነባቸው ሰወች አንዱ ነው ….. እንደውም የሆነ በቅርብ በአካል የማውቀው ልጅ ሁሉ ይመስለኛል ……አድናቆት ያበዛሁበት ከመሰላችሁ አሁኑኑ በዚህ አድራሻው ሂዱና አይታችሁት ውሸት በሉኝ ! ግርማሥላሴ ሰይፉ ጂብራን

3ኛ. በምትፅፋቸው ነገሮች ጥራትና ብቃት ጥርጥር የለኝም ! ጎበዝ ናት እንደውም ስነፅሁፍና የፖለቲካው አንጃ ግራንጃ ፌስ ቡክ ላይ የተሳሰሩባት ቀጭን ክር ትመስለኛለች ! የፖለቲካ አቋሟ ምንም ይሁን ምን አፃፃፏ ግን ደስ ይለኛል ጓደኛዋ ካልሆናችሁ ይቻት Elsa Legesse

4ኛ . በስራው አዲስና የቆዮ መፅሃፍትን ሰብሳቢ …ሻጭ ነው ! ግርም የሚለኝ በጎነት የሞላው ልጅ …. መፅሃፍ ልትገዙ ሂዳችሁ ስለመፅሃፍ እያወራችሁ ቁጭ ያደርጋችኋል አንዳንዴ ነጋዴ ሁሉ አይመስለኝም ! ከምር መፅሃፍቶች እንዲነበቡ የሚመኝ ወጣት ነው …የጠፉ መፅሃፍቶችን ሰብስቦ የመፅሃፍት አውደ ርእይ ያዘጋጃል ፡፡ ገበያ ላይ የማይገኙ መፅሃፍት ካገኘ (ደግሞ ያገኛል ) ልክ እንደህፃን ልጅ በስርአት መርጦ በእንክብካቤ ያስቀምጧቸዋል ብሎ ለሚያስባቸው ደንበኞቹ ይሰጣል ! በአካል አውቀዋለሁ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አለፍ እንዳላችሁ ታገኙታላችሁ ፌስቡክም ላይ ይሄው Mexico Book Corner

5ኛ . ትዝብቶች አጫጭር ታሪኮች አልፎ አልፎም ግጥሞች ይፅፋል በጎ አሳቢ እናም ያመነበትን በራሱ መንገድ ሳያቋርጥ የሚፅፍ ልጅ ነው ጓደኞቹ ብትሆኑ ባሏችሁ ላይ አንድ ጎበዝ ልጅ ጨመራችሁ ማለት ነው! ሶፎንያስ ሆሳዕና

6ኛ . እንደኳስ በህይወቴ የምጠላው ነገር የለም ! የኳስ ወሬ የኳስ ዜና … ገና በሩቁ ያንገሸግሸኛል ! ግን አሁን የማስተዋውቃችሁ ልጅ ብዙ ጊዜ ሴት ጋዜጠኞች የማይዳፈሩትን የስፖርት ዜና ያውም በራሷ ተነሳሽነት ከሽና የምታቀርብ ጠንካራ ልጅ ናት ! ወቅታዊ የአገር ውስጥ የስፖርት ጉዳዮችንም እዚሁ ፌስቡክ ላይ ትፅፋለች በሬዲዮ ስለስፖርት ጠንካራ ትችት ስትሰጥም ሰምቻት አውቃለሁ Nura Ye Juhara Lej ብርታቷ ይገርመኛል !

7ኛ . ፖለቲካ ላይ እንደዚህ ልጅ ያላገጠባት ሰው የለም ! ዘና ብሎ ማለት የሚፈልገውን ይላል ….አንዳንዴ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሃሳቡን ሰርቀው ሳያስፈቅዱ አለም አቀፍ መድረክ ላይ በማቅረባቸው መበሳጨቱን ሁሉ በመግለፅ በዚህ ሃዘን ምክንያት ፕሮፋይል ፒክቸሩን ሊያጠቁር ይችላል ! እንዲህ በዋዘኛ ታዲያ የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮችን ያነሳል ይጥላል ‹‹የዚህ ትውልድ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ›› በዚህ ልጅ የአቀራረብ ፎርማት ቢቀርብ ‹‹የኤድናሞል ትውልድ ሳይቀር ፖለቲከኛ ይሆን ነበር ›› ...... ፍሰሃ ደስታ

8ኛ . ማንም ሰው የሚናገረውን ነገር መልሶ ሲናገረው አዲስ ያስመስለዋል ! ይሄ ልጅ ፖለቲካ ሲፅፍ በጎ በጎውን እያየ ነው …. ሲቃወምም ሲደግፍም ምክንያታዊ በዛ ላይ ለሚናገረው ነገር ከምር ይጨነቃል ! መንግስትን ደግፎ በርካታ ጉዳዮችን በግልፅ ያስቀምጣል ያልጣመውንም ነገር ሲፅፍ አለመጣሙ እንዲጥመን አድርጎ ነው ... በሳል ትንታኔውን እወድለታለሁ …ወዳጆቹ ሲያቆላምጡት ‹‹ሙክታሮቪች ›› ይሉታል Muktar Ousman Adem ሙክታር ‹‹ኢትዮጲያ 22.5 በመቶ እድገት አስመዘገበች ቢለኝ አምነዋለሁ ! ምክንያቱም ኡስማን ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት በላይ ኢትዮጲያን የመውደድ መንፈስ የተጠናወተው ልጅ ስለሚመስለኝ ነው !!

9ኛ .መጀመሪያ አካባቢ ‹‹ጠጅ ጠላ እብድ ወፈፌምናምን ›› ስለምትል አየጭጭ የምን መቀዣበር ነው ብየ አይንሽን ላፈር ብያት ነበር …(ለምን ይዋሻል) በኋላ የምትፅፈቸውን ፅሁፎች ሳይ የመጨረሻ ነቋሪ…. እይታዋ የሚገርም ልጅ ሁና አገኘኋትና የምትለጥፋቸውን ማንበብ ጀመርኩ እላችኋለሁ ! አሪፍ ነቋሪ ነች … ያውም ዘና ያለች እንደው ስጠረጥር እግረ መንገዷን ምናምን ወርወር አድርጋ ስለምትጠፋ እንጅ መረር አደርጋ ብትፅፍ ፌስ ቡክ ላይ ካሉን ሴት ፃህፍት የመጀመሪያውን ቦታ እንደምትይዝ አልጠራጠርም Lemlem Megerssa ነገሮችን እንግዳ በሆነ መነገድ ነው የምትመለከተው !

10ኛ . ያቆየሁት ስለሱ ምን እንደሚባል ግራ ገብቶኝ ነው …አረብ አገር ያለውን ሰቆቃ ልሳን ሁኖ የሚናገር በፅሁፍም በተግባርም ስራው ከሚነገርለት በላይ የሆነ ምርጥ ሰው ! ይሄ ልጅ ‹‹ የሴቶች መብት እኩልነት ›› እያለ የፈለገውን ቢነግረኝ በደንብ ነው የምሰማው ….የተግባር ሰው ነው ! አይሰለችም ወደአገራቸው በተለያየ ምክንያት መመለስ ያቃታቸው ሚስኪን እህቶችን ሰዎችን በማስተባበር የአገራቸውን አፈር እንዲረግጡ በማድረግ እየከፈለ ያለው መስዋእትነት ያስደምመኛል … ስለሱ ምንም ማለት አልችልም ! ከምር በትክክል ስለሴቶች የሚገደው አካል ቢኖር ለዚህ ልጅ ያለምንም ግነት ሃውልት ባቆመለት ነበር እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን ከልቤ አከብርሃለሁ !! Nubiya Kush Kedamawi

═══════❁✿❁ ═══════
ለምርጥ ጽሑፎች በማንኛውም ሶሻል ሚዲያ ጭምር ቻናላችንን ግቡና #Join #Shere አድርጉ ።

http://facebook.com/abrsh2727
http://twitter.com/abrsh2727
http://tiktok.com/@abrsh2727
http://instagram.com/@abrsh2727
https://t.me/abrsh272
እንደምወዳችሁ ታውቃላችሁ አ
═══════❁✿❁ ═══════