Get Mystery Box with random crypto!

#አዲስአበባ አንድ ግለሰብ ወድቆ ያገኙትን ከ7 ሺ ብር በላይ ለፖሊስ አስረከቡ፣ ገንዘቡ የኔ ነው | FastMereja.com

#አዲስአበባ

አንድ ግለሰብ ወድቆ ያገኙትን ከ7 ሺ ብር በላይ ለፖሊስ አስረከቡ፣ ገንዘቡ የኔ ነው የሚል ሰው መጥቶ ይውሰድ ተብሏል።

ሚያዚያ 2 ቀን 2015 ዓ/ም አቶ በሽር አህመዲን የተባሉ ግለሰብ ወድቆ ያገኙትን 7 ሺህ 700 ብር የራሴ ያልሆነና ያልለፋሁበት ገንዘብ ነው በማለት ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ማስረከባቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ግለሰቡ የፈፀሙትን ተግባር ፖሊስ አድንቆ ገንዘቡ የእኔነው የሚል ግለሰብ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመቅረብ መረከብ እንደሚችል አስታውቋል፡፡ ማህበረሰቡ ወድቆ ያገኘውን እና ባለቤቱ ያልተገኘ ንብረትን በአካባቢው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ የማስረከብ ልምድ ሊያዳብር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

@fastmereja