Get Mystery Box with random crypto!

#ባህርዳር በባሕር ዳር ከተማ በቦምብ ፍንዳታ ሦስት ሰዎች ተገደሉ በባህር ዳር ከተማ፣ በተለምዶ | FastMereja.com

#ባህርዳር

በባሕር ዳር ከተማ በቦምብ ፍንዳታ ሦስት ሰዎች ተገደሉ

በባህር ዳር ከተማ፣ በተለምዶ ዓባይ ማዶ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ትላንት ምሽት፣ በአንድ የምግብ እና መጠጥ መሸጫ የንግድ ተቋም ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና ወደ 10 የሚደርሱ ሰዎች መቁሰላቸውን፣ በአካባቢው የሚገኘው የዐዲስ ዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተወካይ ሜዲካል ዳይሬክተር አስታወቁ፡፡ ስለ ጥቃቱ ተጨማሪ መረጃ ከፖሊስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም ሲል ቪኦኤ ነው የዘገበው።

@fastmereja