2024-07-01 18:23:08
ቀለብ ላለመቁረጥ የ4 አመት ልጁ ላይ የግድያ ሙከራ የፈጸመ አባት በእስራት ተቀጣ።
#FastMereja
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በደኖ ወረዳ ኮዬ ቀበሌ ነዋሪ የሆነዉ ከድር አህመድ የተሰኘዉ ግለሰብ ለልጁ ወርሃዊ ተቆራጭ ላለማድረግ ሲል የአራት አመት ህጻን ልጁ ላይ የግድያ ሙከራ መፈጸሙ ተሰምቷል።
ግለሰቡ በፍቺ ካጠናቀቀዉ የትዳር ህይወቱ ላገኘዉ አንድ የአራት አመት ህጻን ልጅ ላይ ነዉ መርዝ በመስጠት የግድያ ሙከራዉን ያደረገዉ።
ግለሰቡ ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት አክረም ከድር የተሰኘዉ የአራት አመት ህጻን ልጅ ላይ አደገኛ ነዉ ፥ የሰዉልጅንም በፍጥነት ይገድላል የተባለዉን ለጫት ተክል ተባይ ማጥፊያነት የሚገለግል መርዝን በምግብ አድርጎ የሰጠዉ።
ተከሳሽ ህጻን አክረም የሚማርበት ብሪቱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመሄድ ከጓደኞቹ ጋር ሲጫወት የነበረዉን ጨቅላ በመጥራት እና ከትምህርት ቤቱ በማስወጣት በሚወደዉ ምግብ ዉስጥ መርዙን እንደሰጠዉ ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል ተብሏል።
የአረም ማጥፊያ የተቀላቀለበትን ምግብ የተመገበዉ ህጻን ወደ ትምህርት ቤቱ ቢመለስም በግማሽ ሰዓት ዉስጥ ማስመለስ እና መሬት ላይ ወድቆ መንፈራፈር ይጀምራል።ህጻናት ጓደኞቹ የአክረምን ህመም ተመልክተዉ ለመምህራን በሰጡት ጥቆማ ህጻኖ ወደ በደኖ ጤና ጣቢያ ተልኮ የህክምና እርዳታ አግኝቶ ህይወቱ ሊተርፍ ችሏል።
ከፖሊስ በምርመራዉ ወላጅ አባቱ ባደረገዉ ድርጊት በቁጥጥር ስር አዉሎ ህጻኑ የግድያ ሙከራ እንደተፈጸመበት በሰዉና በህክምና ማስረጃ በማረጋገጥ ያቀረበውን መዝገብ አቃቤ ህግ ክስ የመሰረተ ሲሆን ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተከሳሽ ከድር አህመድ በገዛ ልጁ ላይ የግድያ ሙከራ በመፈጸሙ በ 7 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታውቋል።
***
ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja
6.3K views15:23