Get Mystery Box with random crypto!

የአምባሳደር ስዩም መስፍን ባለቤትና ወንድ ልጁ ፍርድ ቤት ቀረቡ በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር | FastMereja.com

የአምባሳደር ስዩም መስፍን ባለቤትና ወንድ ልጁ ፍርድ ቤት ቀረቡ

በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር የዋሉት የአምባሳደር ስዩም መስፍን የትዳር አጋር ወ/ሮ ፈለገህይወት በርሔና ልጃቸው አጋዚ ስዩም ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ከመስከረም 30 በኋላ መንግስት የለም በማለት ከህወሓት ፀረ ሰላም ቡድኖችና ከኦነግ ሸኔ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበል በአዲስ አበባ ሁከትና አመፅ ለመቀስቀስ ገንዘብ በማሰራጨትና ወጣቶችን በመመልመል ተጠርጥረው መያዛቸውን መርማሪ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በስዩም መስፍን ስም በተመዘገበ የመንግስት ቤቶች እና በፀሀይ ሪል እስቴት ውስጥ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ላይ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ምርመራ ተደርጓል ሲል መርማሪ ፖሊስ አስረድቷል፡፡

በተለይም በመንግስት ቤቶች በተደረገው ፍተሻ ሁለት ሽጉጦች ተገኝተዋል፡፡ እንዲሁም በፀሀይ ሪል እስቴት በሚገኝ መኖሪያ በተደረገ ብርበራ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ማግኘቱን መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡

ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል ሲልም አስረድቷል፡፡

የአቶ ስዩም መስፍን ባለቤት ወ/ሮ ፈለገህይወት አንደኛው ሽጉጥ ባላቤቴ ራሱን የሚጠብቅበት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከውጭ ሀገር በስጦታ የተሰጠው ነው ስትል አብራርታለች፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ዋስትና እንዲሰጣቸው የጠየቁም ሲሆን፤ ወይዘሮዋ ልጄ አጋዚ የአዕምሮ ህመምተኛ ስለሆነ መድሀት እንዲገባልን ስትል ጠይቃለች፡፡

ጉዳዩን የተከታተለው ችሎት ለተጨማሪ ምርመራ 8 ተጨማሪ ቀናት በመፍቀድ፣ ለፖሊስ በታሰሩበት ቦታ አስፈላጊው መድሀኒት እንዲገባላቸው አዟል፡፡
Via: ፋና

@fastmereja