Get Mystery Box with random crypto!

አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) ፍርድቤት ቀረቡ የሕወሓት የጥፋ ቡድን ከፍተኛ አመራር የነበሩት አዲስዓ | FastMereja.com

አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) ፍርድቤት ቀረቡ

የሕወሓት የጥፋ ቡድን ከፍተኛ አመራር የነበሩት አዲስዓለም ባሌማ (ዶ/ር) በፀረ-ሰላም ቡድን ተደራጅተው በመስራት ተጠርጥረው ፍርድቤት ቀረቡ።

ተጠርጣሪው አምባሳደር በነበሩበትም ዘመን ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት ለማበላሸት እና ለማስቆም ተፅዕኖ ሲፈጥሩና ሲሰሩ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።

በተጨማሪም የመንግስት መረጃና ምስጥሮችን አሳልፈው ሲሰጡ እንደነበር መርማሪ ፖሊስ ለችሎቱ አብራርቷል።

ከኦነግ ሸኔ ከፍተኛ አመራሮች ጋርም መረጃ ሲለዋወጡ እና የመንግስትን ምስጢር አሳልፈው በመስጠት ለተፈፀሙ ወንጀሎች በጋራ ሲሰሩ እንደነበር አስረድቷል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።

በህግ ሲፈለጉ ከነበሩት የጁንታው ሕወሓት ቡድን አባላት መካከል አንዱ የሆኑት አዲስዓለም ባሌማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከትላንት በስቲያ መግለፃቸው ይታወሳል።
Via:ኢቲቪ

@fastmereja