Get Mystery Box with random crypto!

የተሳሳተ መረጃ ማስተካከያ ============== ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ የኢ | FastMereja.com

የተሳሳተ መረጃ ማስተካከያ
==============
ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢፌዲሪ ፈዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሀገር ክህደት ወንጀል የፈፀሙ በርካታ የከሀዲው ጁንታ ህዋሀት ቡድን አባላት የሆኑ ጀኔራል መኮንኖች ፣ ከፍተኛና የመስመር መኮንኖች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ ማውጣቱንና እነዚህን ህገወጦች በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል መጀመሩን ለህዝብ ይፋ ማደረጉ ይታወቃል።
ኮሚሽኑ የክትትል ስራውን አጠናክሮ የቀጠለ ቢሆንም በኢትዮ FM የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ገልፀዋል በሚል 38 የህዋሀት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል ስል ያስተላለፈው መረጃ ሐሰትና በም/ኮሚሽነር ጀነራሉ ያልተላለፈ መሆኑን እየጠቆምን ተያዙ በሚል ሃላፊው የገለፁት መከላከያ ውስጥ የግንኙነት መስመር ያቋረጡና ከዚህ ድርጊት ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፍቃዱን (ወዲ ነጮን) ጨምሮ 38 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ስለመቅረባቸው መሆኑን እየጠቆምን ከጁንታው ቡድን አባላት ከአሁን በፊት ከተገለጹት በስተቀር እስከአሁን ተጨማሪ አዲስ የተያዙ አለመኖራቸው ታውቆ ሌሎች ሚዲያዎች ይህንን የተዛባ መረጃ ለህብረተሰቡ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን ።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን

@fastmereja