Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ታሪክና ጥበቦች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopiahistorywisdom — የኢትዮጵያ ታሪክና ጥበቦች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopiahistorywisdom — የኢትዮጵያ ታሪክና ጥበቦች
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopiahistorywisdom
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.65K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያ ባለብዙ ጥበቦች፣ ባህሎችና ቋንቋዎች ባለቤት ህዝብ መገኛ ስትሆን ፤ ታሪኳ በሳይንሱ ከሚሊዮን ዓመታት በፊት ከሉሲ ሲጀምር በሀይማኖቱ ደሞ ከ7ሺ ዓመታት በፊት ከአዳም ከዛም ከጥፋት ውሃ በኋላ ደሞ ከ5ሺ ዓመታት በፊት ከኖህ እንደምትጀምር ተጨባጭ ማስረጃዎች ያትታሉ። ይህ የቴሌግራም ቻናል የሀገራችንን ታሪክ፣ ባህልና ጥንታዊ ጥበቦች ለናንተ ያካፍላል። አብረውን ይጓዙ።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-15 16:33:48 #ፈጠራና_ለዉጥ_በኢትዮጵያ_ከጥንት_ጀምሮ_እስከ_1930ዎቹ

#ክፍል 2

በመካከለኛው ዘመን በንጽጽር ኢትዮጵያ ለሌሎች ዓለማት ሥልጣኔ እና እውቀት በሯን መዝጋቷ የአገሪቱን የፈጠራና የለውጥ ጉዞ ተንፏቃቂ አድርጎት ነበር። በዘመኑ ምቹ የነበረው የዓየር ጠባይ የሚሰጠው ምርት ከበቂ በላይ በመሆኑ ጊዜው የደስታና የፈንጠዚያ ነበር ማለት ይቻላል። አንዳንዴ የዓየር ሁኔታው ሲዛባና ህዝቡ ለድርቅ ብሎም ለረሃብ ሲጋለጥ ሁኔታው ከፈጣሪ እንደተላከ ቁጣ ነበር የሚታየው። ይህም ችግሩ የፈጠራና የለውጥ አስተሳሰብ አብዮት እንዳይነሳ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል።

በዘመኑ ከውጭ ዓለማት ጋር ግንኙነት ለማድረግ ከሞከሩት ነገሥታት መካከል #አጼ_ይስሐቅ ተጠቃሽ ነው። የአጼ ይስሐቅ የውጭ ግንኙነትም ቢሆን በዋነኝነት ትኩረቱን ያደረገው በጦር መሳሪያና በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ ነበር። ይህ ንጉሥ የቱርኪሽ ማምሉኮችን በመቅጠር ለወታደሮቹ ሥልጠና እንዲሰጡለት ፣ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እንዲሰሩለትና የግብር ስርዓቱን እንዲያደራጁለት አድርጎ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በ1428 ዓ.ም. በዛሬዋ ስፔን አከባቢ ለምትገኘው የአራጎን ንጉሥ አፎንሶ የእጅ ሥራ ጥበበኞችን(artisan) እንዲልክለት የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፎ ነበር።

#አጼ_ልብነ_ድንግል ለፖርቱጋሉ ንጉሥ ማኑኤል ቀዳማዊ በጻፈው ደብዳቤ የወርቅና የብር እንዲሁም የነሃስ ማንጠር ችሎታ ያላቸውን እና በነዚህ ማዕድናት ቤተክርስቲያንን ማስዋብ የሚችሉ ባለሞያዎችን እንዲልክለት ጠይቋል። አክሎም እኝህን ባለሞያዎች ቢልክለት ተንከባክቦ እንደሚይዛቸው እና ወደ አገራቸው መመለስ በፈቀዱ ጊዜም ያለምንም ችግር መመለስ እንደሚችሉ በእግዜብሔር ስም ቃል ገብቶለታል።
-Send masters who can make figures of gold and silver, copper, iron, tin, and lead, and send me lead for the churches; and masters of gilding with gold leaf, and of making gold leaf; and this soon, and let them come to remain with me here and in my favor. And when they may wish to return at their desire, I will not detain them and this I swear by Jesus Christ, Son of the Living God.”
ከዚህም በተጨማሪ አጼ ልብነ ድንግል ለንጉሥ ማኑኤል ቀዳማዊ ልጅ Joao III ተመሳሳይ ደብዳቤ ጽፎ ነበር።
የኋላ ኋላ በአህመድ ግራኝ ወረራ ጊዜ በ1541 ዓ.ም Christovao da Gama የተመራ 400 ወታደሮችንና 130 ባሮችን ያቀፈ ቡድን ከፖርቱጋል መጥቶ በጦርነቱ ላይ ድጋፉን ሰጥቷል። ከጦርነቱም በኋላ አጼ ገላውዲዎስ እነኝህን የውጭ ዜጎች አገር ውስጥ ለማስቀረት ትልቅ ጥረት ማድረጉን ታሪክ ይነግረናል። በዚሁ ጊዜ አጼ ገላውዲዎስ የቀጠራቸው የአርመን፣የግብጽ እና የሶሪያ ዜጎች በቤተመንግሥት ግንባታ ሥራ ላይ ተሳትፈው ነበር።

#ዘመነ_ሰርጸ_ድንግል
ሌላው በመካከለኛው ዘመን ከነበሩ የኢትዮጵያ ነገሥታት መካከል የተለያዩ ባለሞያዎችን ከውጭ አገር ለማስመጣት ሙከራ ያደረገው አጼ ሰርጸ-ድንግል ነው። አጼ ሰርጸ-ድንግል በ1589 ዓ.ም. ለፖርቱጋሉ ንጉሥ ፍሊፔ ዳግማዊ በጻፈው ደብዳቤ ፣ የተለያዩ የጦር መሳሪያ ሥራ እውቀት ያላቸውን ባለሞያዎች እንዲልክለት ጠይቆ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ሰርጸ-ድንግል በጉዛራ ቤተመንግሥት እንዲገነቡለት Garneau እና Arnaud የተባሉ ፈረንሳዊያን ባለሞያዎችን ቀጥሮ እንደነበር ይነገራል። የሰርጸ-ድንግል ወንድም ዘ-ድንግልም እንዲሁ ለንጉሥ ፍሊፔ ሶስተኛ የብረት ሥራ ባለሞያዎችን እንዲልክለት በደብዳቤ መጠየቁን ታሪክ ያወሳል።

#ምጽአተ_ኢየሱሳዊያን (jesuits)
የ16ኛው እና የ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያና የአውሮፓዊያን ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ የተሸጋገረው የኢየሱሳዊያንን በ1557ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ተከትሎ ነው። የኢየሱሳዊያንን መምጣት ተከትሎ የአውሮፓን ድጋፍ እጅጉን ይሹ የነበሩት #ዘ_ድንግል እና #ሱስኒዮስ የሮማን ካቶሊክ እምነት ተቀበሉ። ነገር ግን ኢየሱሳዊያኑ ተስፋ እንዳደረጉት ሰፊው ህዝብ የሮም ካቶሊክ እምነትን ለመቀበል ፍቃደኛ አልነበረም። በዚህም የተነሳ ብዙ ደም አፋሳሽ አመጾች ተከስተው ነበር።

ከ1541-1633 ዓ.ም. በነበረው ዘመን ከፖርቱጋሎች ጥቂት እንቅስቃሴዎች በተቀር ኢትዮጵያ ከውጭ አገራት ጋር የነበራት ግንኙነት በአገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲሁም በፈጠራና ለውጥ ላይ ያስከተለው ለውጥ እምብዛም ነው። በዘመኑ የነበሩ የአገሪቱ ነገሥታትም ከጦር መሳሪያ በቀር በሌሎች ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት ሲያደርጉ አይታይም። በሌላም በኩል ከውጪ የመጡትን ባለሞያዎች እውቀት ወደ አገር ልጅ የሚያሸጋግር ተቋም አልነበረም። የሰውም ሞያውን የመልመድ ፍላጎት ነበር ለማለት የሚያስደፍር አልነበረም።
1.2K viewsedited  13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 14:46:13 #ፈጠራና_ለዉጥ_በኢትዮጵያ_ከጥንት_ጀምሮ_እስከ_1930ዎቹ

በኢትዮጵያ ከጥንት እስከዛሬ የተለያዩ የፈጠራ ሥራ ሙከራዎችና የሥልጣኔ አሻራዎች ታይተዋል። የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት እኝህን የለውጥና የሥልጣኔ ጮራዎች፣ በተለይም ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ እስከ 1930ዎቹ የታዩትን በታሪክ መዝገብ ሰንደው አኑረውልናል። እኛም ለናንተ ለተወደዳችሁ አንባቢዎቻችን በሚመች መልኩ እንዲህ ወደ አማርኛ ቋንቋ መልሰን አሰናድተናል። መልካም ንባብ!
የኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ መልክዓ-ምድር እና በተራሮች የተከበበች አገር መሆኗ አውሮፓዊያን አፍሪካን በተቀራመቱበት ዘመን (scramble for Africa) ነጻነቷን ጠብቃ ለረዥም ዘመናት እንድትኖር ረድቷታል። የዚህች አገር በቅኝ ያለመገዛት ታሪክ እንቆቅልሽ የሆነበት Daniel Thwaite የተባለ ጸሀፊ The Seething African Pot: A Study of Black Nationalism, 1882-1935 በተሰኘ መጽሀፉ ስለኢትዮጵያ ክብር እንዲህ ይላል፤
ይች የአፍሪካ ትንሳኤ ተምሳሌት ፣ የጥቁር ትግል አይበገሬነት ህያው ማሳያ ሲል ይህ ደራሲ የገለጻት አገራችን ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ የሄደችበት የታሪክ መንገድ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት የተለየ ነው። ይህም መሆኑ አገሪቱ በታሪኳ ያለፈችበት የፈጠራና ለውጥ (innovation and change) ሂደት የራሱ የሆነ አሉታዊም አውንታዊም ገጽታ እንዲኖረው አድርጎታል።

#ጥንታዊ_አክሱም

ይህ ዘመን በኢትዮጵያ የፈጠራና ለውጥ ታሪክ ውስጥ ወርቃማው ዘመን ነበር ሊባል ይችላል። በስነ-ህንጻው ዘርፍ የአክሱም ሀውልት በዘመኑ ኢትዮጵያዊያን የነበሩበትን የስነ-ህንጻ ደረጃ ሲያመላክት፣ በዘመኑ የነበረው የጽሁፍና የቋንቋ እድገት፣ በገንዘብ የመገበያየት ሥልጣኔ፣ ወዘተ የዘመኑን የእድገት ደረጃ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።

የአክሱም ዘመን ኢትዮጵያ ለውጭው ዓለም እውቀትና ጥበብ በሯን የዘጋች አልነበረችም። ለዚህ እንደማሳያ በክብረ ነገሥት ላይ የሰፈረውን የንግሥት ሳባንና የንጉሥ ሰለሞንን ታሪክ ማንሳት ይቻላል። በዚህ ታሪክ ውስጥ ንግሥተ ሳባ ስለ ሰለሞን ጥበብ ሰምታ ለጥበብ ካላት ታላቅ ፍላጎት የተነሳ እየሩሳሌም ድረስ ተጉዛ ከንጉሥ ሰለሞን መገናኘቷን እናያለን። ከዚህም በተጨማሪ እንደ ዞስካለስ ዓይነቱ የአክሱም ነገሥታት የግሪክን ስነ-ጽሁፍ ጠንቅቀው ያውቁ እንደነበር በታሪክ ድርሳናት ተጽፎ እናገኛለን። ከዚህም በተጨማሪ የግሪክ ፊደላት በአክሱማዊያን ሳንቲሞች ላይ ታትመው ይታዩ ነበር። በአክሱማዊያን ኪነ-ህንጻ ላይም የግሪክ አማልክት የሆኑት ዜዉስ፣አሬስ እና ፖሴይዶን ተቀርጸው ይታያሉ።

በሀይማኖቱ ረገድ በአክሱም ዘመነ መንግሥት የታዩትን ለውጦች ስንመለከት፣ የአክሱም ዘመን ኢትዮጵያዊያን በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በንጉሥ ኢዛና ዘመነ መንግሥት ክርስትናን መቀበላቸውን በኋላም ከአረቡ አለም ለተሰደዱ መስሊሞች አምባ መጠጊያ መሆናቸውን ታሪክ ይነግረናል። በዚህ ጊዜ የአክሱም ንጉሥ የነበረው ንጉሥ አርማህ፣ እሱን ተማምነው የመጡትን የነብዪ መሐመድ ተከታዮች ከሳሾቻቸው አሳልፎ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁት…..” የወርቅ ተራራ ብትሰጡኝ እንኳን እንኚህን ሰዎች አሳልፌ አልሰጣችሁም”። ነበር ያላቸው።
ንጉሥ አርማህ …..”የወርቅ ተራራ ብትሰጡኝ እንኳን እንኚህን ሰዎች አሳልፌ አልሰጣችሁም”።

#የአክሱማዊያን_የንግድ_ግንኙነት

የአክሱም ዘመን ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምስራቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከነበሩ አገራት መካከል ግንባር ቀደም ነበረች። ለጊዜውም ቢሆን ደቡብ አረቢያን ተቆጣጥረው የነበሩት አክሱማዊያን በታላላቆቹ ኢምፓየሮች ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትን እና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ጥያቄዎችን ያስተናግዱ ነበር። በዚህም ምክንያት በንግዱ ዘርፍ ከግብጽ፣ኑቢያ፣አረቢያ፣ ፐርሺያና ህንድ ግንኙነት የነበራቸው አክሱማዊያን መርከቦቻቸው ቀይ ባህርን እና የህንድ ውቂያኖስን አቋርጠው ሩቅ ተጓዦች ነበሩ።

በቀጣይ ክፍል የመካከለኛውን ዘመን ኢትዮጵያ የፈጠራና የለውጥ ታሪክ እንቃኛለን።
1.4K viewsedited  11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 08:35:02 ኦርቶዶክስን በኦርቶዶክሳውያን የማዳከም አዲስ ስልት!

....የቀጠለ

(5) ከዚኽን በፊትም በተለመደው የፖለቲካ ሴራ አካሔድ መሠረት ቅዱስ ፓትርያርኩን ከመንበር አውርደው በሌላ ተረኛ ለመተካት ባለሥልጣናቱ ፊት ለፊት መምጣቱን አልፈለጉትም፡፡ እናም፥ መጀመሪያ ቅዱስነታቸውን እነርሱ ‹‹ጁንታ›› ከሚሉት አካል ጋር ፈርጀው ለማሸማቀቅ፣ በምእመኑ ዘንድ ለማስጠላትና ‹‹በፈቃዳቸው ለቀቁ›› ለማስባል ሞከሩ፡፡ ‹‹እኔም ኦርቶዶክሳዊ
ነኝ›› የሚሉ፣ በተግባር ግን ያልኾኑ ‹‹መምህራን›› እና አክቲቪስቶችን ከጀርባ ‹‹አይዟችሁ!›› እያሉ በጸያፍ አገላለጾች አስሰደቧቸው፤ ከልክ በላይም አፍ አስከፈቱባቸው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን
ዋና ጸሐፊ ‹‹አይወክሉንም!›› የሚል መግለጫ አስሰጡ፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ኹሉ ግን በሚገርም ኹኔታ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ፣ እንደ አንድ ልብ መካሪ ኾኖ ‹‹ከአባታችን ጎን ነን!›› ብሎ አሳፈራቸው፡፡ ይኽንን የሕዝቡን ሥነ ልቡና ያስተዋሉት ፖለቲከኞቹ ከቅዱስነታቸው ጋር የ ግል ቅራኔ ያላቸውንና የሥልጣን ጥም ያሰከራቸውን ‹‹ጳጳሳት›› በኅቡዕ አደራጅተው መንቀሳቀስ ይዘዋል፡፡ ‹‹ደኅንነቶች ነን›› በሚሉ ሰዎችና ለተረኛው መንግሥት እንቀርባለን በሚሉ ‹‹አባቶች›› አማካይነት ‹‹መንግሥት የሚፈልገው ይኽንን ነው›› ብለው እያስወሩ በአባቶችን ውሳኔ ላይ ከወዲሁ ጫና ለማሳደር እየተሞከረ፣ ቤት ለቤትም ቅስቀሳዎች እየተደረጉ መኾኑ እየተሰማ
ነው፡፡ ገና ቅዱስ ሲኖዶሱ ሳይሰበሰብም፡- ‹‹ቅዱስ ፓትርያርኩ በሌሉበት ምልዓተ ጉባኤ እንደሚካሔድ፣ እንደራሴ እንደሚሾም›› ማስወራት ይዘዋል፡፡ የእኛን አባቶች እየተዋጓቸው ያሉት በእኛው አባቶች ነው የሚያስብለውም ይኸው ነው!

(6) ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በማርቀቅና በማጽደቅ ሒደት ውስጥም የግለሰቦች ፍላጎትና የውጭ አካላት እጅ እየገባ እንደኾነ ተሰምቷል፡፡ ገና ሕጉ በቅዱስ ሲኖዶስ ታይቶ ሳይጸድቅ ‹‹የማስፈጸሚያ ሰነድ›› የሚል ረቂቅ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ባሉት የወቅቱ ፈላጭ
ቆራጮች አማካይነት ሌላ አጀንዳ ማስቀየርያ መዘጋጀቱም ታውቋል፡፡ ስሙን ‹‹ሕገ ቤተ ክርስቲያን›› እያሰኙት የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም ለግለሰቦች ፍላጎት አሳልፎ የሚሰጠውን አካሔድ ግን ‹‹ሕጋዊ›› ለማስመሰል የሚሔዱበት ርቀት ያስተዛዝባል! ሌላው ቀርቶ ‹‹እኛ
መነኮሳት ነን፤ ንብረታችን ኹሉ የቤተ ክርስቲያን እንጂ የእኛ መኾን የለበትም›› የሚል ሐሳብ የሰጡ ሊቃነ ጳጳሳትን እንኳን ምን ያኽል ሲያገልሏቸው እንደነበር የምናስታውሰው ነው!

(7) የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ አንድነትና መዋቅራዊ ጥንካሬ ለጎሣ ፖለቲካቸው የመከፋፈል ሴራ አልመች ሲል የ16ኛውን መቶ ክፍለ ዘመን እሾኽ (‹‹ቅብዓት›› የሚባል ኑፋቄ)
በ21ኛው ክፍለ ዘመን መልሰው ለመትከል ምሥራቅ ጎጃምን የሚያስጨንቋትም አሉ፡፡
በየትኛውም የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሥርዓት ‹‹ጳጳሳት›› እንደተሾሙ ተነገረ፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን ምልዓተ ጉባኤ ትኩረት ለመሳብና አጀንዳውንም ለማስቀየርም ሲሉ ‹‹የጳጳሳቱ በዓለ ሢመት ተዘጋጅቷል›› ብለው የጥሪ ካርድ በተኑ፡፡ ይኽ ኹሉ ሲኾንና ከመደበኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ተደጋጋሚ አቤቱታ ለመንግሥት መዋቅሮች ሲቀርብ ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለዋል፤ በአጥፊው ፋንታም ሰላማውያኑ ታስረዋል፡፡ ‹‹ተለያይቶ
የነበረውን ሲኖዶስ አንድ አደረግሁ›› ብለው የሚመጻደቁት አካላት ‹‹ሌላ ሲኖዶስ›› ለመፍጠር ለምን እንደሚሯሯጡ ግን ግልጽ አይደለም!
ኦርቶዶክስን በራሳቸው በኦርቶዶክሳውያን አማካይነት የማዳከም ስልት፤ አዲሱ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ሴራ!

ከ ‹‹ግንጊልቻ›› መጽሐፍ፣ ምዕ.4፥ ገጽ.89-92 ላይ ባለው ሐሳብ መነሻነት የተጠናቀረ
1.8K views05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 08:35:02 ኦርቶዶክስን በኦርቶዶክሳውያን የማዳከም አዲስ ስልት!

ባለፉት የታሪክ ገጽታዎቻችን ውስጥ በጉልበትና በይፋዊ ተቃርኖ ኦርቶዶክስን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ሲደረጉ የነበሩ እንቅስቃሴዎች ኹሉ አልተሳኩም፤ እንዲያውም የበለጠ ሲያጠናክሯትና ሲያስፋፏት ተስተዋሉ እንጂ፡፡ ለምሳሌ፡- በግራኝ አህመድ ወረራ ዘመን
ኦርቶዶክሳውያኑን በግዳጅ የማስለም ድርጊቶች ተፈጽመው ነበር፤ ሕዝቡም ወደ እስልምና ሲገባ አምኖበት ሳይኾን ተገዶ ስለነበር ጊዜ እስኪያልፍ በትዕግሥት ሲጠባበቅ ቆይቶ ነበር፡፡ እናም፥ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እነዚያ የመከራ ዘመናት ሲያልፉ ሃይማኖታቸውን እንዲክዱ
ተገደው የነበሩ ምእመኖቿን መልሳ ወደ ጉያዋ ለመሰብሰብ እንዲያስችላት ‹‹አንቀጸ አሚን›› የተባለ የማስተማሪያ መጽሐፍ አዘጋጅታ፣ ‹‹መጽሐፈ ቄዴር›› የተባለ የማጥመቅያ ሥርዓትም
ሠርታ ተልእኮዋን መልሳ ለማጠናከር ችላለች። ኦርቶዶክሳዊነትን ለማክሰም የተሠራ ሴራ ጭራሹን እንዲጠናከር ዕድል መፍጠሩን ይኽ አንዱ የታሪክ ምስክርነት ነው፡፡
በኋላ በጣልያን ወረራ ጊዜም ካቶሊኮች የእስልምናውን ክንፍ በመደገፍ ሁለቱ ‹‹የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው›› በሚመስል መርሕ ተባብረው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ሲሠሩ ነበር፡፡ ለምሳሌ፡- በካቶሊኮቹ ሴራ ‹‹ሁለቱ እሾሆች›› የተባሉ ቅባትና ጸጋ በኢትዮጵያ ምድር በተተከሉ ጊዜ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እነርሱን ለመንቀል ትግል ላይ ስትጠመድ እስልምናው ደግሞ ድምጹን አጥፍቶ ውስጥ ውስጡን ሲስፋፋ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ በዚኽ ታሪካዊ ተሞክሮ መሠረት ደግሞ የጋራ ጠላትን እንዴት በትብብር መዋጋት እንደሚቻል ልምድ ተቀስሞበታል፤ ይበልጥ አዘምኖና አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግም የታመነበት ይመስላል፡፡
አሁንም በግላጭ ኦርቶዶክሳውያንን አስገድዶ ለመጠምዘዝ መሞከር የማይታሰብ ነውና ሌላ ስልት አስፈለጋቸው! ይልቁንም፥ ተፈጥሯዊ በኾነ መንገድ (biological strategy) ቤተ ክርስቲያኒቱ ራሷን በራሷ እንድታጠፋ ኹኔታዎችን ማመቻቸት አዲሱ ስልት ተደርጎ የተያዘ ይመስላል፡፡ ይኽ ስልት አንድ እንዲጠቃ የተፈለገው ተቋም ራሱን በራሱ እንዲያጠፋ መርዳት (helping the institution to self-suicide) የማድረጊያ ዘዴ ነው፡፡ ይኽ ተፈጥሯዊ
የመባሉም ምስጢር ችግሩን በሚመስል መፍትሔ የመከላከል ስልትን ስለሚከተል ነው፡፡
ለምሳሌ፡- በሥነ-ሕይወታዊ የጥናት ዘርፍ ትላትሎችን ከግብርና ሰብል ጥቃት ለመከላከል ሲፈለግ ለሰብሉ ጎጂ ያልኾኑ፣ ነገር ግን ትላትሎቹን የሚበሉ ሌሎች እንስሳት የማርባት ዘዴ
ማለት ነው፤ በዚኽ የተፈጥሮ ሚዛን (ecological balance) ይጠበቃል፡፡ ከሌሎች ስልቶች የበለጠም ውጤታማ ነው (ኬሚካልን የመሰሉ መፍትሔዎች ለጎጂ ተባዮች ተረጭተው
ጠቃሚዎቹንና ሰብሎችን ጭምር የሚያደርቁ ‹‹ጅምላ ጨራሽ›› ከመኾናቸውም በላይ ለአየር
ብክለት ስለሚያጋልጡ አይመከሩም)፡፡ ተባዮቹን የሚመስሉ ሌሎች ተጻራሪ ተባዮች ሲኾኑ ግን ተመሳሳይ የአኗኗር ዘይቤ ስላላቸው በቀጥታ ከመገናኘታቸውም በላይ ጎጂዎቹ ተባዮችን አዘናግተው (ዘመድ መስለው) እንዲያጠቁአቸው ዕድል ይሰጣቸዋል፡፡
ይኽንኑ ኹኔታ ወደ ተቋም ስናመጣው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ፊት ለፊት በመንግሥታዊ ሥልጣን ተጠቅመው፣ በሰይፍ አስፈራርተውና በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ተከራክረው ማሸነፍ
እንደማይቻል ከታሪክ የተረዱት አካላት አንድነቷን ለመክፈል መጠቀም የጀመሩት አዲሱ ስልት መኾኑ ነው፡፡ ይኽ ስልት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ በቀጥታና በይፋ የሚሰነዝረውን ጥቃት በይፋ ሳያሳውቅ (ለትችት በማያጋልጠው፣ ነገር ግን የተሻለ ውጤታማ በሚያደርገው መልኩ) እንዲያዳክማት የሚያስችላቸው ነው፡፡
ይኽ ተፈጥሯዊ ስትራቴጂ ‹‹ራስን በራስ እንዲያጠፋ የመርዳት›› መርሕን ስለሚከተል ቤተ ክህነቱ እንደተጻራሪ ክንፍ በፈረጃቸው የእስልምናና ሌሎች የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች ከመገዳደር ይልቅ በውስጡ ባሉት ሰዎቹ ተጠቅሞ፣ ስያሜውን በሚመስል ዘዴ፣ የራሱን ተልእኮ
የሚያፋጥንለት የሚመስለውን አሠራር መዘርጋት ይበልጥ ውጤታማ ያደርገዋል፡፡ መዋቅርን በመዋቅር፣ ጳጳስን በጳጳስ፣ ቤተ ክህነትን በቤተ ክህነት፣ ሲኖዶስን በሲኖዶስ፣ ማኅበራትን በማኅበራት፣ አሠራርን በአሠራር ተክቶ ከመጀመሪያው አቅጣጫዋ ወደ ሚፈለገው መሥመር ማስቀየስ፤ በሒደትም ግብዓተ መሬቷን ለመፈጸም እንደማለም ያለ ስልት ነው፡፡
ይኽ ከሰሞንኛ ኹኔታዎች አንጻር ምን ምን ነገሮችን እንድናስተውል ያደርገናል?

(1) ትናንት ‹‹የኦሮሚያ ቤተ ክህነት›› እያሉ ሲያጨናንቁን የነበሩ ‹‹ኦርቶዶክሳውያን›› ወንድሞቻችን ዘግይተው ደግሞ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ፥ ‹‹ሙስሊም ወንድሞቻችን
ቢያፈጥሩበት ምን ችግር አለበት?›› እያሉ ሲከራከሩን አስተውለናል፡፡ የገዛ ወገኖቻችን ከተቀናቃኞቻችን ጎን ኾነው ሞገቱን፤ ኦርቶዶክሳውያንን በኦርቶዶክሳውያን መዋጋት ይሏል ይኽ
ነው!

(2) ይኽንኑ ጉዳይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጠቅላይ ቤተ ክህነቷ አማካይነት ተቃውሞ ስታቀርብ መንግሥት ደግሞ የእርሷኑ ሌላ መዋቅር (የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን) ተጠቅሞ
‹‹ይቅርታ›› አስጠየቀ፤ በመዋቅራችን አማካይነት መዋቅራችንን አጠቃው ማለት ነው!

(3) ለኦርቶዶክሳዊ ቀኖናት ደንታ የሌላቸውና ከመሰል እሴቶች ሊያንሸራትቱን የሚሹ ተሓድሶዎች ‹‹ኦርቶዶክሳውያን›› መስለው፣ ለትግራይ ሕዝብም እንደተቆረቆሩ አስመስለው
በበዓለ ሃምሳ ጾም ዐወጁ፡፡ ይኽንን ሲያደርጉ ግን ‹‹የገዳም አባቶችና የትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት አዘዋል›› እያሉ ነው፡፡ ከእኛው ጾምና ትእዛዘ አበው ጋር ታክከው የእኛኑ ቀኖና ለመናድ የሚደረግ ሌላኛው እንቅስቃሴ!

(4) በውስጣችን ኾነው፣ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያንን አሁናዊ ጭንቀት መፍትሔ እንዳገኙ አስመስለው ‹‹ደጉ ንጉሥ ቴዎድሮስ ይገለጣል!›› የሚሉንም በዝተዋል፡፡ ለዚኽ ማሳመኛቸው
ደግሞ ‹‹ፍካረ ኢየሱስ›› እና ‹‹የገዳም አባቶች መልእክት›› የሚሉ የማግባቢያ አካሔዶችን ይጠቀማሉ፡፡ ገዳማውያኑ ግን በአንድነት ኾነው ‹‹መልእክቱ ከእኛ አይደለም!›› ማለታቸውን ልብ ይሏል፡፡

ይቀጥላል...
1.6K views05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 11:37:34 የንስሀ አባቶች Vs Psychotherapy
(Cognitive behavioral therapy)

psychotherapy በ 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተጠንስሶ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ያደገ የሳይንስ ዘርፍ ነው። በጭንቀት፣ በድብርት፣ በፍርሀት እና ተያያዥ የአእምሮ ህመም የተጠቃ ግለሰብን ለማከም የሚረዳ የስነልቦና ህክምና ዘርፍ ነው። ህክምናው የሚካሄደው በስነልቦና ባለሙያው እና በግለሰቡ መካከል በሚደረግ ንግግር ነው። የስነልቦና ባለሙያው የግለሰቡን ህመምና የህመሙን ምንጭ ከተረዳ በኃላ ህክምናውን የሚሰጥበት የተለያየ መንገድ አለ።

ለአብነትም cognitive behavioral therapy የተሰኘው መንገድ ማንሳት ይቻላል። ዋንኛ ታማሚውን ግለሰብ መርጃ መንገድ ስለችግሩ እንዲያወራ በማድረግ ስለራሱ ስለአካባቢው ያለውን ግንዛቤ ማስፋት ነው። አሉታዊ አስተሳሰቦችን በአዎንታዊ አስተሳሰብ እንዲተካ በማድረግ ከጭንቀት፣
ከድብርት መሰል ህመሞች ተላቆ ግለሰቡ ጤናማና ደስተኛ ህይወት እንዲኖረው ማድረግ የዚህ ህክምና አላማ ነው። እንግዲህ የስነልቦና ሳይንስ ከመጠንሰሱ በርካታ ዘመናትን አስቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ለእያንዳንዱ ግለሰብና ቤተሰብ የንስሀ አባት በመመደብ የ " psychotherapy" አገልግሎት ትሰጥ ነበር። ይህ ማለት አገራችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አማካይነት ለስነልቦና ሳይንስ የህክምና ዘርፍ ፍልስፍና ፋና ወጊ መሆኗን የሚያረጋግጥ ነው።

በንስሀ አባት እና የንስሀ ልጅ መካከል ያለው ግንኙነት ከአንድ የስነልቦና ባለሙያ እና ህመምተኛው መካከል ካለው ግኙነት የጠበቀ ነው። ምክንያቱም የንስሀ አባቶች ልጆቻቸው በስጋም በነፍስ ጠንክረው በሁለት ጎኑ የተሳለ ሰይፍ እንዲሆኑላቸው ስለሚያደርጓቸው ነው። ይህን የሚያደርጉት ከልጆቻቸው ጋር በሚፈጥሩት ቀጣይነት ያለው ንግግር ነው። ልክ እንደ ሳይኮሎጂስቶቹ ሁሉ የንስሀ አባቶች የልጆቻቸው የስጋ ፈተናዎች ( ጭንቀት፣ ድብርት ወዘተ) ለመሻር በሳይንሱ cognitive behavioral therapy ይጠቀሙ ነበር። ልጆቻቸው ስለእራሳቸው፣ ስለቤተሰባቸው፣ ስለህይወት፣ ስለስራቸው ወዘተ አዎንታዊ አመለካከትን እንዲያዳብሩ በማድረግ አስተሳሰብ ላይ ለውጥ ይፈጥራሉ። አዎንታዊ አስተሳሰብ ጤናማ የአእምሮ አሰራርን እንደሚፈጥር አበው ተረድተው ነበር። ልክ እንድ ስነልቦና ሳይንሱ ምግባር ( ethics) ሁሉ በንስሀ አባትና በንስሀ ልጅ መካከል ያለው ግንኙነት ምስጢር የተጠበቀ ነው። ልክ እንደ ስነልቦና ሳይንሱ ሁሉ በኛም ዘንድ በንስሀ አባትና ልጆች መካከልም አዎንታዊ ትምህርትና ለውጥ ለማምጣት ቅጣት Reinforcement እና punishment ነበር።

እንግዲህ በዚህ ፅሁፍ ላይ ማንሳት የፈለኩት ነጮች ያላቸው እኛ የሌለን ያልነበረን እንደሌለ እናእንዳልነበረ ማሳየት ነው። ክብር ብንሰጠው እውቅና ብንሰጠው እና ብናጠናው እጅግ ጥልቅ የሆነ አገራዊ የስነልቦና ፍልስፍና አለን። በስተመጨረሻ psychotherapy እና የስነልቦና ባለሙያዎች የስጋ ብቻ መድህን ናቸው። ንስሀ አባቶች ግን የስጋም የነፍስም መድህን ናቸው። ለዚህ ነው የንስሀ አባት ሊኖረን የሚገባው። በስጋዊ ህይወታችንም ስኬታማ፣ ጤነኛ እና ውጤታማ ለመሆን ለነፍሳችን የሚበጅም ስንቅ ለመሰነቅና ከምንቆሽሽበት ሀጥያት ለመንፃት የንስሀ አባት ያስፈልገናል። የንስሀ ህይወት ያስፈልገናል።

#ራፋቶኤል
3.3K views08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-13 09:37:37 የጠቢቡ ሰለሞን ቀለበት ምንድን ነው?

- የሀይል ምንጩስ ከወዴት ነው?
- ዛሬ ላይ የት ሀገሬ የት ቦታ በምን ሁኔታ ላይ  ይገኛል? 
- ሚስጥሩን ለመፍታት ታምሩንም ለማየት ምን አይነት ጸሎት ይጸለያል ?

የጠቢቡ ሰለሞን የሃይሉ ምንጭ የነበረው እና ታላላቆቹ የቀደሙት የኢትዮጵያ ነገስታት እንዲሁም አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳት ይጠቀሙበት የነበረው ቀለበት ምስጢር ምን እንደሆነ ለመረዳት አለም ላይ ያሉ ብዙ የጥንት መዛግብቶች እየታሰሱ ይገኛሉ ፡፡

በዚሁ ሃያል ቀለበት ከሰው ተፈጥሮ በላይ የሆኑ የጥበብ እና የንቃተ ህሊና ስፋትን ያላብሳል ይህ መለኮታዊ ሃይል የተጎናጸፈ ቀለበት ለሰሎሞን የማስተዋል ፣በጥበብ የመምራት፤ ነገሮችን ከሰው በተለየ መልኩ የመመርመር ፣ ከእንስሳ ጋር ሳይቀር የመግባባት የመነጋገር ጥበብን አጎናጸፈው።

ከመካከለኛ ዘመን ወዲህ ስለዚህ ቀለበት በስፋት ይነገራል በተለይ በመካከለኛ ምስራቅ ባሉ አረብ ሃገራት እጅግ ትኩረትን የሳበ ቀለበት ነው። ከዚህም የተነሳ በክታብ በአሸን ክታብ እንዲሁም በመልክት የቀለበቱ ቅርጽና ይዘት ይሰፍር ነበር።

ይህ ቀለበት የተሰራው በአንድ ገጹ ከንሃስ በሌላ ገጹ ደግሞ ከብረት ሲሆን በሁለቱም የቀለበት ገጾች ላይ ህቡዕ ስሞች ወይም በአንደኛው ስመ አምላክን (አስማትን) ይዞል። ይህ ሃይል ያለው ቀለበት ለሰሎሞን ከእግዚአብሔር እንደተሰጠው ይታመናል። በዚህም ድንቅ ቀለበት የተፈጥሮ ነፋሳትን እና ውሃዎችን እንዲሁም እንስሳትንም ያዝ ነበር።

በተለያየ ዘመንም ስለዚህ እንቁ ሃይል ስላለው የሰሎሞን ቀለበት ሃሳባዊ መላምት ተሰጥቶበታል። ይህ የሰሎሞን ቀለበት ከ አባቱ ከዳዊት ኮከብ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ባለ ስድስት ከዋክበት ቅርጽ ይዞል። ታድያ ይህ የዳዊት ኮከብ በመባል የሚታወቀው የዛሬዋ እስራኤል ብሔራዊ አርማ ከ ሰሎሞን ቀለበት ጋር ለምን ተመሳሰለ የሚለውን እንመልከት።

ባለስድስት ቀንድ ኮከብ የሰለሞን ማኅተም፥ የዳዊት ኮከብ [የዳዊት ጋሻ]፥ የቴዎድሮስ ኒሻን፥ የላሊበላ ጌጥ፥ የአክሱም ጌጥ፥ የፋሲል ጌጥ፥ የይምርኀነ ክርስቶስ ጌጥ (ማኅተም) በመባል ሲጠራ አብዛኛውን ጊዜ ግን የሰለሞን ማኅተም አለያም የዳዊት ኮከብ በመባል ይታወቃል።

የዚህ ኮከብ አመጣጥ እንዲህ ነው፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚደጋገሙት ክስተቶች ውስጥ የኮከብ መታየት አንዱ ነው። ለምሳሌ ሙሴ ሲወለድ ፥ ሰለሞን ቤተመቅደስ ሲሰራና ክርስቶስ  ሲወለድ የታየው ኮከብ ለአብነት ተጠቃሽ ነው። ይህ ሰለሞን አርማው አድርጎ በምኩራባት እንዲሰቀል ያዘዘው የኮከብ ቅርፅና በአገራችን ለብዙ ዘመናት የቆየው የሰሎሞናው ሥርወ-መንግስት እንደአርማ ይጠቀምት የነበረው ኮከብ ንጉሥ ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን መስሪያ ቦታ በፈለገ ጊዜ ከላይ በሠማይ እያበራ የቤተመቅደሱን መሥሪያ ሥፍራ የጠቆመው ኮከብ ነው።
ነብየ እግዚአብሔር ንጉሥ ዳዊት የቤተ መቅደሱን መስሪያ ቦታ የሚጠቁመውን በራዕይ ያየውን የኮከብ ቅርፅ ስሎ ቤተ መቅደሱን እንደሚሰራ አስቀድሞ ለተነገረለት ልጁ አስቀምጦለታል። ልጁም ስዕሉን ተጠቅሞ ኮከቡን ከከዋክብት ለይቶ ባየው ጊዜ ኮከቡ ባበራለት ሥፍራ ላይ ቤተመቅደሱን ሰርቷል።

ወደአገራችን ስንመጣ ደግሞ የካም ዘሮች የደሸት ልጆች በታላቁ ወንዝ በግዮን (አባይ)ዳርቻ በሚዋኙበት ጊዜ ምስለ ፍቁር ወልዳንና ይሄንን ባለስድስት ጫፍ ኮከብ በግዮን ውኃ ላይ ተስሎ እንዳዩትና ከዛን ጊዜ ጀምረው የኮከቡን መውጣት በልጅ ልጆቻቸው እየተቀባበሉ በተስፋ ይጠብቁት እንደነበር የታሪክ መዛግብት ላይ እናገኘዋለን። የካም ልጆች (ኢትዮጵያዊያን) የዚህን ኮከብ በሰማይ መገለጥ ሲጠባበቁ ከኖሩ በኋላ መድኀኔዓለም  ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ኮከቡ በሰማይ ላይ ሲያበራ በመመልከታቸው ከአባቶቻቸው ጀምረው ይጠብቁት የነበረው ትንቢት እንደደረሰ በማወቅ ኮከቡን ተከትለው ቤተልሔም ድረስ በመሄድ በከብቶች በረት ለተወለደው ለጌታችን ለእየሱስ ክርስቶስ እጅ መንሻ እንደሰጡ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ ተጽፎልናል። ይህ ባለ ስድስት ጫፍ ያለው  ቅርጽ ከጥንት ኢትዮጵያውያን ጋር በቀጥጣ ይቆራኛል ።

የዚህ ኮከብና የሰሎሞን ቀለበት የኢትዮጵያዊያን ግንኙነት የሚጀምረው ከ ሰሎሞናዊው ስርወ መንግስት አስቀድሞ የኖኅ ልጅ ካም ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበትና ኮከቡን በግዮን ውኃ ላይ ከተመለከቱበት ጊዜ ጀምሮ ነው።

እንግዲህ ከላይ ለመዳሰስ እንደሞከርነው የእሴይ ልጅ ዳዊት የቤተመቅደሱን መሥሪያ ሥፍራ የሚያመለክተውን ኮከብ በትንቢት ካየ በኋላ በዙፋኑ፣ በጋሻውና በምኩራቦቹ ሁሉ እያስቀረፀ አስቀምጦታል። የእርሱ ልጅ ሰሎሞንም በተመሳሳይ ኮከቡን በንግስና ዙፋኑና በቀለበቱ ላይም  በሌሎች ቦታወች ሁሉ ላይ ማስቀረጽ ጀመረ። ኢትዮጵያዊቷ ንግስት ማክዳ (ንግስተ ሳባ ወይም ንግስተ አዜብ) የሰሎሞንን ጥበብ በሰማች ጊዜ በእንቆቅልሽ ልትፈትነው ከብዙ እጅ መንሻ ጋር ወደ ሀገረ ኢየሩሳሌም ተጓዘች። በእንግድነቷም ጊዜም ከንጉስ ሰለሞን ጸነሰች። የእስራኤል ቆይታዋን አጠናቅቃ ስትመለስም ንጉስ እብነመለክ/አቤሜሌክ ወይም ቀዳማዊ ምንሊክን ወለደች። ንጉሥ ምኒልክ እድሜው በሃያዎቹ መጀመሪያ በሆነ ጊዜ አባቱን የእስራኤልን ንጉሥ ሰለሞንን ጎብኝቶ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ ብዙ ሌዋውያን ካህናትንና ታቦተ ጽዮንን ከብዙ አጃቢ አይሁዶች ጋር ይዞ መጣ። ከዚህም በኋላ ምንሊክ በኢትዮጵያ በነገሰ ጊዜ ቀድሞ በእናቱ ዙፋን ላይ ተቀርጾ የነበረውን የዘንዶ ምስል በማጥፋት ከአባቱ ያገኘውን ባለ ስድስት ጫፍ የኮከብ  ምስል በዙፋኑና በእቃዎቹ እንዲሁም በጋሻውና በቤተመቅደሶች ሁሉ ላይ ቀረጸ።

ከዚህም በኋላ ዘራቸው ከሰለሞን የሚመዘዝ የሰሎሞናዊ ሥርወ ንግስት ነገስታት ሁሉ ይህን ኮከብ  እና የሰሎሞን የጣት ቀለበትን እንደአርማ ይጠቀሙበት ነበር።

የኮከቡ ትርጉም የሰፋ ቢሆንም Element encyclopedia of secret signs and symbols ከተሰኘው የAlede Nozedar መጽሐፍ በሰፊው ይገልጻል። እያንዳንዳቸው የኮከቡ ጉጦች (ጫፎች) የተወከሉበት ቁጥር አላቸው። ቁጥሮቹም በሁለንታ ውስጥ የሚገኙትን ፈለኮችን ይወክላሉ። ይኸውም፦
1=ጨረቃ
2=ቤነስ
3=ሜርኩሪ
4=ሳተርን
5=ማርስ
6=ጁፒተር
7=ፀሐይ ተብለው ይሰየማሉ። ይህም የሚያሳየው ምልክቱ ስለጠፈር የያዘው
ሚስጢር እንዳለ ነው። ከዚህም በተጨማሪ መሀል ላይ መስቀሉ ሲጨመር የመስቀሉን ብርሃናማነት [ፀሐይነት] ያሳያል።

ከዚህ በተጨማሪ ምልክቱ ለኢትዮጵያ የትንሳኤዋ አርማ ነው። በትንቢት እንደሚነገረው ይህ ኮከብ በመጨረሻው ዘመን ይመጣል ተብሎ ስለ ሚታመነው የንጉሥ ቴውድሮስ ቀና ዘመን በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እያበራ በመታየት የትንሳኤዋን ብስራት ያውጃል ተብሎም ይነገራል። ይሄን የሰማው ካሣ ኃይሉ የንግስና ስሙን ዳግማዊ ቴዎድሮስ በማለት ኮከቡን የአንገቱ ማዕተብ ላይ አድርጎት እንደነበረ ታሪክ ያወሳል ። የጀግኖቹ የሽልማት ኒሻን ሁኖም ነበር።

ታድያ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በዳዊት ኮከብ አምሳል የተቀረጸው እጅግ መግነጢሳዊ ሐይል ያለውን የጣት ቀለበት አርባ አመት እስራኤልን በጥበብ እንዲመራ አድርጓል የእሱ የዘር ሀረጎቹም  በሚገባ ተጠቅመውበታል።  የሰሎሞን የጣት ቀለበት ብዙ ሚስጥሮችን የሚፈታ ታምራትን እንዲያደረጉ ሀይልን የሚሰጥ ጥበብን የሚለግስ ስመ አምላክ የታተመበት የእግዚአብሔር ስጦታ ነበር።

#ፈለገ_ጥበባት
2.4K views06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 08:31:27 ታላቁ ንጉስ ነገስት ኢትዮጵስ 1ኛ

ኢትዮጵስ 1ኛ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ1856 እስከ 1800 ዓመት ኢትዮጵያን የገዛ ታላቅ ንጉሥ ነበር። የራጉኤል (ዮቶር) ልጅ የሆነው አባብሄር በሲና ምድረ በዳ በነበረ ጊዜ ከአይሁድ ነገድ የሆነችውን ሩት አሚን አግብቶ ታላቁን ኢትዮጵስን የወለዱ ሲሆን በታላቅ ስርዓትም በግዮን ወንዝ ዳርቻ ስመ መንግስቱ ሰንደቅ ዠን ተብሎ የነገሰ ነው።

በሱ የስልጣን ዘመን በመላ ኢትዮጵያ በረከት ሆኖ ነበር። ዛፎች ልምላሜና ፍሬ ይሰጡም ነበር። አህዛብ ሁሉ የጣኦት አማልክትን የሰባበሩበት የፈጣሪም መንፈስ በመላ ሀገሪቱ የነገሰበት የበረከት ዘመን ነበር።

ንጉስ ነገስት ኢትዮጵስ (ሰንደቅ ዠን) በብዙ የሀገሪቱ ቦታዎች ታላላቅ ከተሞችንና መንደሮችን የቆረቆረ ነው። በሰባተኛ ዘመነ መንግስቱም ወደ ተራራማው የቴሌጋቫ ምድር ሄደ። በዚህ ምድር ጉምዞች ፣ በአያ ፣ ሽናሻ ፣ አገዎች ፣ ትግሬዎች ፣ ኦማርና አረማዎች ይኖሩበት ነበር። በዛም ታላቂቱን ከተማ ሱቫን ሰራ። በላያ በመባልም ትታወቅ ነበር። አሁንም ቢሆን በላያ የተባሉ ህዝቦች ይኖሩበታል። በዘልማድ የበላያ አገዎች ይባላሉ።

ንጉሥ ኢትዮጲስ የአንድ ሃይማኖትን ስነ ምግባርና ተግባር የሰበከ ታላክ ንጉሥ ነበር። ህዝባዊነትን፣ ምልክናንና ክህነቱን በኢትዮጵያ ያፀና መንፈሳዊ ንጉሥም ነበር። በአስፈሪነቱ ፣ በመንፈሳዊነቱና ታማኝነቱ ለእግዚአብሔርና ለሰው ሁሉ የተመቸ ሰው ነበር።

ንጉሥ ኢትዮጲስ በሶስት አመት ውስጥ ታላቅ የሆነ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በማሰራት 1200 ንፁሃን ሰወች ያገለግሉ ዘንድ አስገባ። የእግዚአብሔርን ስርዓት የሚጠብቁና የሚአስተምሩ 400 ነብያትንም አስገባ።
ንጉሱ ይህን ሁሉ ያረግ የነበረው እግዚአብሔር በሃገሩ በኢትዮጵያና ህዝቦቿ ላይ ፅንቶ እንዲኖር በማሰብ ነበር። እግዚአብሔርም አላሳፈረውም " ከእንግዲህ ሀገሪቱ ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ተብላ ትጠራለች እስከ ዘመነ ምጽአትም ድረስ ኢትዮጵያ እግዚአብሔር የሚመለክባት ምድር ሆና እንደምቀጥል" ለንጉሱና ለካህናቱ ቃል ኪዳን ገባላቸው። በዚህ ንጉሥ መልካምነትና በአባቶቻችን ትጋት ከዛ ጊዜ ጀምሮ የወረደው ሀይለ መንፈስ ቅዲስ በኢትዮጵያ ላይ ስለማይነሳ የእግዚአብሔር ሀገር ልትባል ችላለች። ገናም ስትባል ትኖራለች።

ንጉሥ ኢትዮጵስ የኢትዮጵያን ስም ያከበረና ከፍ ከፍ ያደረገ ሀገሪቱንም ኢትዮጵያ ተብላ እንድትጠራ ያደረገ ታላቅ የሀገራችን ባለውለታ ንጉሥ ነበረ። በዘመኑም ምድሩ ከማለምለምና ከተማ ከመቆርቆር በስተቀር ምንም አይነት ጦርነት ችግር መከራ አልነበረም ነበር።

ታላላቅ ሰዎች ከራሳቸው በላይ ለቀጣዩ ትውልድ በማሰብ የሚተጉ ናቸው። የእነ ንጉስ ኢትዮጵስ ትጋትና ድካም ለኢትዮጵያ የዘላለም ቃልኪዳንና በረከት ያስገኝ ነው። ዛሬ ዓለም ከሃይማኖት ርቃ በተለያየ ፍልስፍና እና ትርምስ ውስጥ ባለችበት ከባድ ወቅት እንኳ ኢትዮጵያ ሳትፈራርስና ፈጣሪዋን ሳትተው ይሄው ብዙ ሺ ዓመታት ተሻግራ ቆማለች፤ ይህም መሆኑ ከታላቁ ኢትዮጵስ 1ኛ ጀምሮ የወረደው ሀይለ መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያ ላይ ስለማይነሳ ነው። ዛሬ በተለያየ አቋራጭ ከምናካብተው ጊዜአዊ ዝናና ሃብት ይልቅ በሃቅ ቁመን ለትውልድ መትጋትን ከታላቁ ንጉሳችን ኢትዮጵስ 1ኛ እንማር።
2.0K views05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-02 08:48:01 አድዋ ለኛ ባርነት ወይስ ነፃነት?

አባቶቻችን ወራሪውን የጣሊያን ጦር በመመከት ትውልዳቸውን ከባርነት ቀንበር ነፃ አውጥተዋል፤ ታሪካቸውንም አስጠብቀዋል። ከመላ ኢትዮጵያ የተመሙ ጀግኖች ዛሬ ድረስ ዓለምን በሚያስደምም መልኩ በጦርና ጎራዴ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀውን የጣሊያን (የምዕራባውያን) ጦር በመደምሰስ ታላቅ ጀብዱ ሰርተው የሀገራቸውን ነፃነት አስከብረው በነፃነት መኖር ችለዋል።

እኛ የዚህ ዘመን ትውልዶች አድዋን አስበን እንደ አርበኛ አባትና እናቶቻችን ለብሰን በየአደባባዩ ተገኝተን ስናከብረው ወደር የለንም። የኛ ብቻ ሳይሆን የመላ ጥቁር መለያ (brand) ነውና አድምቀን ማክበራችን እሰየው ነው። የኔ ጥያቄ ግን ወዲህ ነው። እውነት ዛሬ ያለነው ትውልድ ከጠላቶቻችን ነፃ የወጣን ነን ወይ? እውነት ትላንት አባቶቻችን ደጋግመው የመለሷቸው ጠላቶቻችን ዛሬ እየገዙን አደለም ወይ? በዘመናዊነት ስም ምዕራባውያኑ በእጅ አዙር ነፃነታችንን ነጥቀው ባሪያቸው እያደረጉን አደለም ወይ?

- ቋንቋችንና ፊደላችንን አስጥለው በነሱ እንግሊዘኛ ከተኩት ቆይተዋል። 60% በላይ የኢትዮጵያ ቋንቋ በላቲኑ ፊደል ነው ዛሬ ላይ የሚፃፈው።

- የትምህርት ስርዓታችንን ሙሉ በሙሉ አክስመው በነሱ ስርዓት ተክተውታል ሌላው ቀርቶ በነጮቹ ቋንቋ ነው አብዛኛው ትምህርት የሚሰጠው።

- ከተፈጥሮ ተቀምመው የሚሰሩት ፍቱን መድሃኒቶቻችንን ተነጥቀው በአሜሪካኑ አርቴፊሻል ህክምና ከተተኩ ሰነባብተዋል። ስኳሩም ካንሰሩም ከዛ በኋላ በዝቶብናል።

- የረቀቀ ጥበብ የተሞላውን ግዕዛችንን አስጥለው በእንግዘኛቸው ተክተውታል።

- የወጣቱን ጊዜና አይምሮ በኢንግሊዝ ፕሪምየር ሊግና ቁማር ወጥረው ስለ ታሪኩ ፣ ሀገሩና ሀይማኖቱ የሚአሰላስል ወጣት አሳጥተውናል።

- ትውልዱ ከራሱ ታሪክና ትውፊት ይልቅ በሆሊውድ ዝነኞች ትውፊት እየተማረከ ማንነቱን እንዲክድና አልባሌ ነገሮች ላይ እንዲወድቅ ብዙ ተግብረውብናል።

- ባዶእግሩን ከሚማቅቀው ወገኑ ይልቅ የአንጄሊና ጁሊና የክርስቲያኖ ሮናልዶ የትዳር ውሎ የሚያሳስበው ወጣት ፈጥረዋል።

- በተፈጥሮ ከበለፀገው የራሳችንን መዋቢያ አርቀው አስጥለው በምዕራባውያኑ ሂውማን ሄርና ሜካፕ መጌጥ ካስጀመሩን ሰነባብተዋል።

- የትም የማይገኙ የተፈጥሮ ምግቦቻችንን ነጥቀው ዘመን አመጣሽ ድቅል ዝርያና የኬሚካል ማዳበሪያ ተመጋቢ ካረጉን ዓመታት እየተቆጠሩ ነው።

- በቋንቋና ነገድ ፣ በሀይማኖትና አስተሳሰብ ከፋፍለው በዚህም በዛም እያስታጠቁ ከባድ ደም እያቃቡን እያወዳደሙን ይገኛሉ።

- መልካም መስለው በገፍ በሚሰጡን ብድርና እርዳታቸው ቋሚ ጥገኛቸው አርገው በባርነት ቀንበር ካሰሩን ይሄው አስርት ዓመታት አልፈውናል።

ታዲያ ጣሊያን ብገዛን ኖሮ ከዚህ የተለየ ምን ታረገን ነበር። ቋንቋችንን ከማስጣል ፣ ትምህርታችንን ከመቀየር ፣ ህክምናችንን ከመንጠቅ ፣ እሴቶቻችንን ከማክሰም ፣ ታሪካችንን ከማውደም ፣ የትውልዱን አስተሳሰብ ከመመረዝ ውጭ ጣሊያን ምን ታረገን ነበር?

ባይገባን ነው እንጂ የዛሬ ትውልዶች ተገዝተናል! የኛ ትውልድ ሳያውቀው ተምበርክኳል። አደዋን አርበኛ መስለን ደምቀን ስላከበርን ብቻ ነፃ ህዝብ እንደሆንን አናስብ ወገን። 'አደዋ ነፃነት' እያልን ስንዘፍን የሚሰሙን ምዕራባውያን ከት ብለው ነው የሚስቁብን! በትላንት በሬ ላይታረስ ዛሬ እያሉ ነው የሚያፌዙብን። በአባቶቻችን የደረሰባቸውን ውርደት ተበቅለውናልና። አድፍጠው በእጅ አዙር በዘመናዊነትና ስልጣኔ ስም ያኔ ያቀዱትን ዛሬ ፈፅመውብናልና። እንንቃ! ወገን እንንቃ! በባርነት ቀንበር ውስጥ እንዳለን ይግባን መጀመሪያ። እሱን ከተረዳን ዳግም ነፃ መውጣት አይከብደንምና! ዳግም የአባቶቻችንን ጥበብና ስርዓት ፣ እሴቶችና ፊደላት አበልፅገን መመለስ አያቅተንምና።

ዳይ እንግዲ ትውልዴ ታሪክህን ገልጠህ ማንበብ ጀምር ፣ ዶክተሩም የአባቶችህን የህክምና ጥበብ መርምረህ አዘምን ፣ መሃንዲሱ የዱባዩን ህንፃ መቅዳት ትተህ ኢትዮጵያዊ ህንፃዎችን አንፅ ፣ መምህሩ ኢንግሊዝኛን ጥለህ ተማሪዎችህን ረቂቁን ግዕዝ አስተምር ፣ ገበሬው ድቃይ ዝርያችሁን ውሰዱልኝ ካንሰራሙን ማደበሪያቹሁን አልፈልግም በል ፣ ኢኮኖሚስቱ የሀገርህን እምቅ ሀብት ተጠቅመህ ሀገርህን ከእዳ አውጣ ፣ ፅሃፊው ትውልዱን በራሱ ማንነት ቅረፅው ፣ የኪነጥበብ ሰዎች ሆሊውድን ሳይሆን እራሳችሁን ሆናቹ ትውልዱን ቅረፁ ወዘተ.....
#ያኔ ነፃ ትውልድ እንባላለን። በደም የተሰጠንን የአደዋ ነፃነትም እናስቀጥላለን።

@ethiopiahistorywisdom
2.2K views05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-27 10:50:44
ሰርቢያኖች ስለ ጦርነት ያላቸው ድንቅ አባባል

ትንሽዬዋ የደቡብ ምስራቅ አውሮፓዊቷ ሀገር
የሆነችው ሰርብይ ስለ ጦርነት አስከፊነት ትልቅ የሆነ መልእክት ያለው አባባል አላቸው። እሱም ፦

ጦርነት ሲጀምር...ፓለቲከኞች ጥይት ያቀብላሉ። ባለጽጎችም ምግብ
ይሰጣሉ። ድሆች ግን ልጆቻችን ይለግሳሉ።

ጦርነቱም ሲያበቃ...ፓለቲከኞች ቀሪ ጥይቱን ይሰበስባሉ። ባለጸጎችም
ከጦርነቱ በተረፈው ሐብታቸው ማደግ ይጀምራሉ፤ ድሆች ግን ልጆቻቸውን
በመቃብር ሥፍራ ይፈልጋሉ።
ይህ ነው የጦርነት ዶሴው!

ሠላም ለምድራችን !
2.7K views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-22 19:09:12 እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ ባሕርን ተናገረው

እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት

ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር

እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር"

ልብ አድርጉ :-

ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል
ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል

ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል:: ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው::

ይህንንም እናስታውስ

ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው::

ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :-

"ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም"

ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
2.0K views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ