Get Mystery Box with random crypto!

የጠቢቡ ሰለሞን ቀለበት ምንድን ነው? - የሀይል ምንጩስ ከወዴት ነው? - ዛሬ ላይ የት ሀገሬ የ | የኢትዮጵያ ታሪክና ጥበቦች

የጠቢቡ ሰለሞን ቀለበት ምንድን ነው?

- የሀይል ምንጩስ ከወዴት ነው?
- ዛሬ ላይ የት ሀገሬ የት ቦታ በምን ሁኔታ ላይ  ይገኛል? 
- ሚስጥሩን ለመፍታት ታምሩንም ለማየት ምን አይነት ጸሎት ይጸለያል ?

የጠቢቡ ሰለሞን የሃይሉ ምንጭ የነበረው እና ታላላቆቹ የቀደሙት የኢትዮጵያ ነገስታት እንዲሁም አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳት ይጠቀሙበት የነበረው ቀለበት ምስጢር ምን እንደሆነ ለመረዳት አለም ላይ ያሉ ብዙ የጥንት መዛግብቶች እየታሰሱ ይገኛሉ ፡፡

በዚሁ ሃያል ቀለበት ከሰው ተፈጥሮ በላይ የሆኑ የጥበብ እና የንቃተ ህሊና ስፋትን ያላብሳል ይህ መለኮታዊ ሃይል የተጎናጸፈ ቀለበት ለሰሎሞን የማስተዋል ፣በጥበብ የመምራት፤ ነገሮችን ከሰው በተለየ መልኩ የመመርመር ፣ ከእንስሳ ጋር ሳይቀር የመግባባት የመነጋገር ጥበብን አጎናጸፈው።

ከመካከለኛ ዘመን ወዲህ ስለዚህ ቀለበት በስፋት ይነገራል በተለይ በመካከለኛ ምስራቅ ባሉ አረብ ሃገራት እጅግ ትኩረትን የሳበ ቀለበት ነው። ከዚህም የተነሳ በክታብ በአሸን ክታብ እንዲሁም በመልክት የቀለበቱ ቅርጽና ይዘት ይሰፍር ነበር።

ይህ ቀለበት የተሰራው በአንድ ገጹ ከንሃስ በሌላ ገጹ ደግሞ ከብረት ሲሆን በሁለቱም የቀለበት ገጾች ላይ ህቡዕ ስሞች ወይም በአንደኛው ስመ አምላክን (አስማትን) ይዞል። ይህ ሃይል ያለው ቀለበት ለሰሎሞን ከእግዚአብሔር እንደተሰጠው ይታመናል። በዚህም ድንቅ ቀለበት የተፈጥሮ ነፋሳትን እና ውሃዎችን እንዲሁም እንስሳትንም ያዝ ነበር።

በተለያየ ዘመንም ስለዚህ እንቁ ሃይል ስላለው የሰሎሞን ቀለበት ሃሳባዊ መላምት ተሰጥቶበታል። ይህ የሰሎሞን ቀለበት ከ አባቱ ከዳዊት ኮከብ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ባለ ስድስት ከዋክበት ቅርጽ ይዞል። ታድያ ይህ የዳዊት ኮከብ በመባል የሚታወቀው የዛሬዋ እስራኤል ብሔራዊ አርማ ከ ሰሎሞን ቀለበት ጋር ለምን ተመሳሰለ የሚለውን እንመልከት።

ባለስድስት ቀንድ ኮከብ የሰለሞን ማኅተም፥ የዳዊት ኮከብ [የዳዊት ጋሻ]፥ የቴዎድሮስ ኒሻን፥ የላሊበላ ጌጥ፥ የአክሱም ጌጥ፥ የፋሲል ጌጥ፥ የይምርኀነ ክርስቶስ ጌጥ (ማኅተም) በመባል ሲጠራ አብዛኛውን ጊዜ ግን የሰለሞን ማኅተም አለያም የዳዊት ኮከብ በመባል ይታወቃል።

የዚህ ኮከብ አመጣጥ እንዲህ ነው፦ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚደጋገሙት ክስተቶች ውስጥ የኮከብ መታየት አንዱ ነው። ለምሳሌ ሙሴ ሲወለድ ፥ ሰለሞን ቤተመቅደስ ሲሰራና ክርስቶስ  ሲወለድ የታየው ኮከብ ለአብነት ተጠቃሽ ነው። ይህ ሰለሞን አርማው አድርጎ በምኩራባት እንዲሰቀል ያዘዘው የኮከብ ቅርፅና በአገራችን ለብዙ ዘመናት የቆየው የሰሎሞናው ሥርወ-መንግስት እንደአርማ ይጠቀምት የነበረው ኮከብ ንጉሥ ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን መስሪያ ቦታ በፈለገ ጊዜ ከላይ በሠማይ እያበራ የቤተመቅደሱን መሥሪያ ሥፍራ የጠቆመው ኮከብ ነው።
ነብየ እግዚአብሔር ንጉሥ ዳዊት የቤተ መቅደሱን መስሪያ ቦታ የሚጠቁመውን በራዕይ ያየውን የኮከብ ቅርፅ ስሎ ቤተ መቅደሱን እንደሚሰራ አስቀድሞ ለተነገረለት ልጁ አስቀምጦለታል። ልጁም ስዕሉን ተጠቅሞ ኮከቡን ከከዋክብት ለይቶ ባየው ጊዜ ኮከቡ ባበራለት ሥፍራ ላይ ቤተመቅደሱን ሰርቷል።

ወደአገራችን ስንመጣ ደግሞ የካም ዘሮች የደሸት ልጆች በታላቁ ወንዝ በግዮን (አባይ)ዳርቻ በሚዋኙበት ጊዜ ምስለ ፍቁር ወልዳንና ይሄንን ባለስድስት ጫፍ ኮከብ በግዮን ውኃ ላይ ተስሎ እንዳዩትና ከዛን ጊዜ ጀምረው የኮከቡን መውጣት በልጅ ልጆቻቸው እየተቀባበሉ በተስፋ ይጠብቁት እንደነበር የታሪክ መዛግብት ላይ እናገኘዋለን። የካም ልጆች (ኢትዮጵያዊያን) የዚህን ኮከብ በሰማይ መገለጥ ሲጠባበቁ ከኖሩ በኋላ መድኀኔዓለም  ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ኮከቡ በሰማይ ላይ ሲያበራ በመመልከታቸው ከአባቶቻቸው ጀምረው ይጠብቁት የነበረው ትንቢት እንደደረሰ በማወቅ ኮከቡን ተከትለው ቤተልሔም ድረስ በመሄድ በከብቶች በረት ለተወለደው ለጌታችን ለእየሱስ ክርስቶስ እጅ መንሻ እንደሰጡ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ላይ ተጽፎልናል። ይህ ባለ ስድስት ጫፍ ያለው  ቅርጽ ከጥንት ኢትዮጵያውያን ጋር በቀጥጣ ይቆራኛል ።

የዚህ ኮከብና የሰሎሞን ቀለበት የኢትዮጵያዊያን ግንኙነት የሚጀምረው ከ ሰሎሞናዊው ስርወ መንግስት አስቀድሞ የኖኅ ልጅ ካም ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበትና ኮከቡን በግዮን ውኃ ላይ ከተመለከቱበት ጊዜ ጀምሮ ነው።

እንግዲህ ከላይ ለመዳሰስ እንደሞከርነው የእሴይ ልጅ ዳዊት የቤተመቅደሱን መሥሪያ ሥፍራ የሚያመለክተውን ኮከብ በትንቢት ካየ በኋላ በዙፋኑ፣ በጋሻውና በምኩራቦቹ ሁሉ እያስቀረፀ አስቀምጦታል። የእርሱ ልጅ ሰሎሞንም በተመሳሳይ ኮከቡን በንግስና ዙፋኑና በቀለበቱ ላይም  በሌሎች ቦታወች ሁሉ ላይ ማስቀረጽ ጀመረ። ኢትዮጵያዊቷ ንግስት ማክዳ (ንግስተ ሳባ ወይም ንግስተ አዜብ) የሰሎሞንን ጥበብ በሰማች ጊዜ በእንቆቅልሽ ልትፈትነው ከብዙ እጅ መንሻ ጋር ወደ ሀገረ ኢየሩሳሌም ተጓዘች። በእንግድነቷም ጊዜም ከንጉስ ሰለሞን ጸነሰች። የእስራኤል ቆይታዋን አጠናቅቃ ስትመለስም ንጉስ እብነመለክ/አቤሜሌክ ወይም ቀዳማዊ ምንሊክን ወለደች። ንጉሥ ምኒልክ እድሜው በሃያዎቹ መጀመሪያ በሆነ ጊዜ አባቱን የእስራኤልን ንጉሥ ሰለሞንን ጎብኝቶ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ ብዙ ሌዋውያን ካህናትንና ታቦተ ጽዮንን ከብዙ አጃቢ አይሁዶች ጋር ይዞ መጣ። ከዚህም በኋላ ምንሊክ በኢትዮጵያ በነገሰ ጊዜ ቀድሞ በእናቱ ዙፋን ላይ ተቀርጾ የነበረውን የዘንዶ ምስል በማጥፋት ከአባቱ ያገኘውን ባለ ስድስት ጫፍ የኮከብ  ምስል በዙፋኑና በእቃዎቹ እንዲሁም በጋሻውና በቤተመቅደሶች ሁሉ ላይ ቀረጸ።

ከዚህም በኋላ ዘራቸው ከሰለሞን የሚመዘዝ የሰሎሞናዊ ሥርወ ንግስት ነገስታት ሁሉ ይህን ኮከብ  እና የሰሎሞን የጣት ቀለበትን እንደአርማ ይጠቀሙበት ነበር።

የኮከቡ ትርጉም የሰፋ ቢሆንም Element encyclopedia of secret signs and symbols ከተሰኘው የAlede Nozedar መጽሐፍ በሰፊው ይገልጻል። እያንዳንዳቸው የኮከቡ ጉጦች (ጫፎች) የተወከሉበት ቁጥር አላቸው። ቁጥሮቹም በሁለንታ ውስጥ የሚገኙትን ፈለኮችን ይወክላሉ። ይኸውም፦
1=ጨረቃ
2=ቤነስ
3=ሜርኩሪ
4=ሳተርን
5=ማርስ
6=ጁፒተር
7=ፀሐይ ተብለው ይሰየማሉ። ይህም የሚያሳየው ምልክቱ ስለጠፈር የያዘው
ሚስጢር እንዳለ ነው። ከዚህም በተጨማሪ መሀል ላይ መስቀሉ ሲጨመር የመስቀሉን ብርሃናማነት [ፀሐይነት] ያሳያል።

ከዚህ በተጨማሪ ምልክቱ ለኢትዮጵያ የትንሳኤዋ አርማ ነው። በትንቢት እንደሚነገረው ይህ ኮከብ በመጨረሻው ዘመን ይመጣል ተብሎ ስለ ሚታመነው የንጉሥ ቴውድሮስ ቀና ዘመን በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ እያበራ በመታየት የትንሳኤዋን ብስራት ያውጃል ተብሎም ይነገራል። ይሄን የሰማው ካሣ ኃይሉ የንግስና ስሙን ዳግማዊ ቴዎድሮስ በማለት ኮከቡን የአንገቱ ማዕተብ ላይ አድርጎት እንደነበረ ታሪክ ያወሳል ። የጀግኖቹ የሽልማት ኒሻን ሁኖም ነበር።

ታድያ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በዳዊት ኮከብ አምሳል የተቀረጸው እጅግ መግነጢሳዊ ሐይል ያለውን የጣት ቀለበት አርባ አመት እስራኤልን በጥበብ እንዲመራ አድርጓል የእሱ የዘር ሀረጎቹም  በሚገባ ተጠቅመውበታል።  የሰሎሞን የጣት ቀለበት ብዙ ሚስጥሮችን የሚፈታ ታምራትን እንዲያደረጉ ሀይልን የሚሰጥ ጥበብን የሚለግስ ስመ አምላክ የታተመበት የእግዚአብሔር ስጦታ ነበር።

#ፈለገ_ጥበባት