Get Mystery Box with random crypto!

Ethiomewlid ኢትዮ መውሊድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomewlid — Ethiomewlid ኢትዮ መውሊድ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiomewlid — Ethiomewlid ኢትዮ መውሊድ
የሰርጥ አድራሻ: @ethiomewlid
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.18K
የሰርጥ መግለጫ

ሙሐመድ ﷺ ዉዴታዎ ያሰባስበናል፤ በሙሐመድ ፍቅር አንድ ነን! አንድነታችን በሙሐመድ ፍቅር ነው።
የፌሰቡክ ፔጃችንን ላይክ በማድረግ ይቀላቀሉ፦
Fb.com/Ethiomewlid
የዩትዩብ ቻናላችን Subscribe አድርጉ!
https://goo.gl/ohhc8z
በ ኢኒስታግራም በዚህ ሊንክ Follow ያድርጉ
Instagram.com/ethiomewlid

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2020-06-06 19:27:30 ዱዓእ ይበልጥ ተቀባይነት የሚያገኝበት ግዜዎች

1ኛ፦ በሱጁድ ግዜ፦
...
ኢማም ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ “አንድ ባሪያ ለጌታው ቅርብ የሚሆነው በሱጁድ ላይ ሲሆን ነው” በሐዲሱ ላይ የተጠቀሰው “ቅርብ” ትርጉሙ የቦታና የአቅጣጫ ቅርበት ሳይሆ ን የእዝነቱና የረህመቱ ነው።
:
2ተኛ፦ ጁምዓ ቀን የሆነ ሰአት ላይ፦
...
ሙስሊም በሷሒሓቸው እንዳስቀመጡት የአሏህ መልእክተኛ ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
«ጁምዓ በውስጧ የሆነ ሰአትን ይዛለች ባሪያው በዛች ሰአትቆሞ እየሰገደ አሏህን የጠየቀ እንደሆነ የጠየቀው ይሰጠዋል»
☞ ሰአቷ በርግጠኝነት ባትታወቅም በብዛት ከዐስር ሷላት ግዜ በኋላ ፀሃይ ወደ መጥለቋ አከባቢ እንደሆነች ዑለማኦች ይናገራሉ።
:
3ተኛ፦ ከለሊት የመጨረሻው 1/3ኛው ግዜ፦
...
ኢማም አንነሳኢይ እንደዘገቡት “ከለሊት ግማሹ ካለፈ በኋላ አሏህ ተጣሪን(መላኢካን) እንዲህ ብሎ እንዲጣራ ያዛል:ጌታችሁ እንዲህ ይላል፦ ማነው ዱዓ አድርጉ የምቀበለው፤ ጠይቆስ የምሰጠው፤ ምህረትን ፈልጎ የምምረው? ይላል።” ይህ ሐዲስ የኢማም አን–ነሳኢይ ዘገባ ሲሆን በቡኻሪይ ላይ ያለውን “የንዚሉ ረቡና” የሚለውን ይፈስራል። ምክንያቱም ፈጣራሪያችን በመውጣት እና በመውረድ አይገለፅምና።
:

4ተኛ ፦ በአዛን እና ኢቃማ መካከል
...
አነስ ኢብን ማሊክ ከነቢዩ ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዳስተላለፉት “በአዛንና በኢቃማ መሀል የሚደረግ ዱዓእ አይመለስም” ብለዋል። [ቲርሚዚይ እና አቡዳዉድ]
:
5ተኛ፦ አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት ነቢዩ ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ 3 ዱዓኦች ያለምንም ጥርጥር ተቀባይነት አላቸው፤ የተበደለ ሰው ዱዓእ፡ የተጓዥ ዱዓእ እና ወላጅ በልጁ ላይ የሚያደርገው ዱዓእ” [አቡ ዳዉድ እና ነሳኢይ]

አንብበው ከጨረሱ በኋላ SHARE ማድረግ አይርሱ። በዚህ የፌስቡክ ገፃችንም ላይክ በማድረግ ይከታተሉ @ethiomewlid
3.7K views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-03-28 02:36:15 Watch "فيلم قصير لمناسبة ذكرى المولد النبوي " on YouTube


4.4K views23:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-03-25 19:21:16
ኢላሂ ረመዳንን በሰላም አድርሰን!

@Ethiomewlid
4.2K viewsedited  16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-03-21 17:01:02
ረጀብ 27 | ነቢያችን በቁድስ ነቢያትን ኢማም ሆነው ያሰገዱበት፤ የኢስላም መሰረት የሆነው 5 አውቃት ሶላት የወጀበበት ለሊት። ለዝህች ቀን ትውስታ እንኳን አደረሳችሁ! ለሊቷን በዒባዳ በዱዓእ ማሳለፍ አትርሱ!
@ኢትዮ መውሊድ @ethiomewlid
16.0K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-01-23 17:44:34 ህመማቸውን በዝምታ የሚ ያሳልፉ ልቦች!

•••••••●■ ■●••••••

አንድ የቀዶ ጥገና ሀኪም በአስቾካይ ወደ ሀኪም ቤት ተጠርቶ ወደ ሀኪም ቤቱ ሲሸባ ወደ ኦፕሬሲዮን ክፍል ከመግባቱ በፊት …የታማሚው ልጅ አባት እየጮሀበት..«ምንደነው እስካሁን መዘግየት?!ልጄ እኮ አስጊ ሆኔታ ላይ ነው ያለው..ምንም የማዘን ስሜት የለብህም?! " ይለዋል

ሀኪሙ : ፈገግ ኣለና «እባክህ ረጋ በልና ስራዬን ልስራበት ፤ ይልቅ በአሏህ ተመካና ለልጅህም ዱዓእ አድርግለት» ይለዋል።

የልጁ አባትም: «የልጅህ ህይወት እንዲህ አስጊ ሆኔታ ላይ ቢሆን ትረጋጋ ነበር?!» ኣለው… ሀኪሙ ትቶት ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል ገባ...ከሁለት ሰኣት በጟላ በፍጥነት እየወጣ ለአባትዬው : ቀዶ ጥገናው በተሳካ ሆኔታ እንደተጠናቀቀና ልጁም ደህና እንደሆነከ ነገረው። «አሁን ሌላ ቀጠሮ ስላለብኝ መሄድ ኣለብኝ» ብሎ ከአባትዬው ኣንድም ጥያቄ ሳያስተናግድ ሄደ።

አስታማሚ ነርሷ ስትወጣ አባትዬው እንዲህ ኣላት: «ይህ ትእቢተኛው ሀኪም ችግሩ ምንድነው?!» ብሎ ጠየቃት ።
እሷም እንዲህ ብላ መለሰችለት፡ «ልጁ በመኪና አደጋ ሞቶበታል፤ ቢሆንም ግን ልጅህ ያለብትን አሳሳቢ ሆኔታ ስለተረዳ ስንጠራው ያለበትን ትቶ መጣ። የልጅህን ህይወት ካዳነ በጟላ ግን ልጁን ለመቅበር ፈጥኖ ሄደ።»
-------
የሚታመሙ ልቦች ሆነው የማይናገሩ ኣሉ... ስለዚህ ሳታረጋግጥ ሰዎች ላይ አትፍረድ።

@Ethiomewlid
4.5K viewsedited  14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-01-23 17:44:23
3.7K views14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-01-18 15:21:43
3.5K views12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-01-12 12:59:53 ✧ ለሞተ ሙስሊም ቁርኣንን ማንበብ ይወደዳል
………

እቂል ኢብኒ የሳር ከተላለፈው ሀዲስ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
عن ﻣﻌﻘِﻞ ﺑﻦ ﻳَﺴﺎﺭ ﺃﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻗﺎﻝ : " ﺍﻗﺮﺀﻭﺍ ﻳـﺲ ﻋﻠﻰ ﻣﻮﺗﺎﻛﻢ " ﺭﻭﺍﻩ ﺃﺑﻮ ﺩﺍﻭﺩ ﻭﺍﻟﻨﺴﺎﺋﻲ ﻭﺍﺑﻦ ﻣﺎﺟﻪ ﻭﺃﺣﻤﺪ ﻭﺍﻟﺤﺎﻛﻢ ﻭﺻﺤﺤﻪ ﺍﺑﻦ ﺣﺒﺎﻥ .
....
ለሙስሊም ሙታኖቸ ቁርኣን ፣ ዱዓ እና የሰደቃ ምንደ እንደሚደርሳቸው የተረጋገጠ ነው። ለሞተ ሙስሊም ቁርኣንን ማንበብ ከሰለፎች ግዜ ጀምሮ የተለመደ ሆኗል። የተወደደና ምስጉን ተግባር እንደሆነ ታላለቅ ኡለማኦች ተናግረዋል።

ኢማም አል-ነወዊይ እንዳሰተላለፉት ኢማሙ ሻፊዒይ እንዲህ ብለዋል፦
« የሞተ ሰው ዘንድ ከቁርኣን የተወሰነው ቢነበብ የተወደደ ነው፤ ቁርኣንን ሙሉውን የኸተሙ እንደሆነ ደግሞ ተመራጭ ነው።»
ﺭﻭﻯ ﺍﻟﺤﺎﻓﻆ ﺍﻟﻨﻮﻭﻱ ﻋﻦ ﺍﻹﻣﺎﻡ ﺍﻟﺸﺎﻓﻌﻲّ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﺃﻧﻪ ﻗﺎﻝ :
ﻭﻳﺴﺘﺤﺐ ﺃﻥ ﻳُﻘﺮﺃ ﻋﻨﺪ ﺍﻟﻤﻴّﺖ ﺷﻰﺀ ﻣﻦ ﺍﻟﻘﺮﺀﺍﻥ ﻭﺇﻥ
ﺧﺘﻤﻮﺍ ﺍﻟﻘﺮﺀﺍﻥ ﻋﻨﺪﻩ ﻛﺎﻥ ﺣﺴﻨًﺎ

እንዲሁም በ "ሱነኑል በይሀቂይ" እንደተዘገበው: አብዱላህ ኢብኑ ዑመር ቀብር ለይ ሆነው የ"ሱረቱል በቀራ" የመጀመሪያውና የመጨረሻ አንቀፁን ማንበባቸው ተዘግቧል።
@ethiomewlid
4.4K viewsedited  09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-01-12 12:59:42
3.4K views09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-12-24 02:03:08

3.5K views23:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ