Get Mystery Box with random crypto!

ዱዓእ ይበልጥ ተቀባይነት የሚያገኝበት ግዜዎች 1ኛ፦ በሱጁድ ግዜ፦ ... ኢማም ሙስሊም በዘገ | Ethiomewlid ኢትዮ መውሊድ

ዱዓእ ይበልጥ ተቀባይነት የሚያገኝበት ግዜዎች

1ኛ፦ በሱጁድ ግዜ፦
...
ኢማም ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ “አንድ ባሪያ ለጌታው ቅርብ የሚሆነው በሱጁድ ላይ ሲሆን ነው” በሐዲሱ ላይ የተጠቀሰው “ቅርብ” ትርጉሙ የቦታና የአቅጣጫ ቅርበት ሳይሆ ን የእዝነቱና የረህመቱ ነው።
:
2ተኛ፦ ጁምዓ ቀን የሆነ ሰአት ላይ፦
...
ሙስሊም በሷሒሓቸው እንዳስቀመጡት የአሏህ መልእክተኛ ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
«ጁምዓ በውስጧ የሆነ ሰአትን ይዛለች ባሪያው በዛች ሰአትቆሞ እየሰገደ አሏህን የጠየቀ እንደሆነ የጠየቀው ይሰጠዋል»
☞ ሰአቷ በርግጠኝነት ባትታወቅም በብዛት ከዐስር ሷላት ግዜ በኋላ ፀሃይ ወደ መጥለቋ አከባቢ እንደሆነች ዑለማኦች ይናገራሉ።
:
3ተኛ፦ ከለሊት የመጨረሻው 1/3ኛው ግዜ፦
...
ኢማም አንነሳኢይ እንደዘገቡት “ከለሊት ግማሹ ካለፈ በኋላ አሏህ ተጣሪን(መላኢካን) እንዲህ ብሎ እንዲጣራ ያዛል:ጌታችሁ እንዲህ ይላል፦ ማነው ዱዓ አድርጉ የምቀበለው፤ ጠይቆስ የምሰጠው፤ ምህረትን ፈልጎ የምምረው? ይላል።” ይህ ሐዲስ የኢማም አን–ነሳኢይ ዘገባ ሲሆን በቡኻሪይ ላይ ያለውን “የንዚሉ ረቡና” የሚለውን ይፈስራል። ምክንያቱም ፈጣራሪያችን በመውጣት እና በመውረድ አይገለፅምና።
:

4ተኛ ፦ በአዛን እና ኢቃማ መካከል
...
አነስ ኢብን ማሊክ ከነቢዩ ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዳስተላለፉት “በአዛንና በኢቃማ መሀል የሚደረግ ዱዓእ አይመለስም” ብለዋል። [ቲርሚዚይ እና አቡዳዉድ]
:
5ተኛ፦ አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት ነቢዩ ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ 3 ዱዓኦች ያለምንም ጥርጥር ተቀባይነት አላቸው፤ የተበደለ ሰው ዱዓእ፡ የተጓዥ ዱዓእ እና ወላጅ በልጁ ላይ የሚያደርገው ዱዓእ” [አቡ ዳዉድ እና ነሳኢይ]

አንብበው ከጨረሱ በኋላ SHARE ማድረግ አይርሱ። በዚህ የፌስቡክ ገፃችንም ላይክ በማድረግ ይከታተሉ @ethiomewlid