Get Mystery Box with random crypto!

ህመማቸውን በዝምታ የሚ ያሳልፉ ልቦች! •••••••●■ ■●•••••• አንድ የቀዶ ጥገና ሀኪም | Ethiomewlid ኢትዮ መውሊድ

ህመማቸውን በዝምታ የሚ ያሳልፉ ልቦች!

•••••••●■ ■●••••••

አንድ የቀዶ ጥገና ሀኪም በአስቾካይ ወደ ሀኪም ቤት ተጠርቶ ወደ ሀኪም ቤቱ ሲሸባ ወደ ኦፕሬሲዮን ክፍል ከመግባቱ በፊት …የታማሚው ልጅ አባት እየጮሀበት..«ምንደነው እስካሁን መዘግየት?!ልጄ እኮ አስጊ ሆኔታ ላይ ነው ያለው..ምንም የማዘን ስሜት የለብህም?! " ይለዋል

ሀኪሙ : ፈገግ ኣለና «እባክህ ረጋ በልና ስራዬን ልስራበት ፤ ይልቅ በአሏህ ተመካና ለልጅህም ዱዓእ አድርግለት» ይለዋል።

የልጁ አባትም: «የልጅህ ህይወት እንዲህ አስጊ ሆኔታ ላይ ቢሆን ትረጋጋ ነበር?!» ኣለው… ሀኪሙ ትቶት ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል ገባ...ከሁለት ሰኣት በጟላ በፍጥነት እየወጣ ለአባትዬው : ቀዶ ጥገናው በተሳካ ሆኔታ እንደተጠናቀቀና ልጁም ደህና እንደሆነከ ነገረው። «አሁን ሌላ ቀጠሮ ስላለብኝ መሄድ ኣለብኝ» ብሎ ከአባትዬው ኣንድም ጥያቄ ሳያስተናግድ ሄደ።

አስታማሚ ነርሷ ስትወጣ አባትዬው እንዲህ ኣላት: «ይህ ትእቢተኛው ሀኪም ችግሩ ምንድነው?!» ብሎ ጠየቃት ።
እሷም እንዲህ ብላ መለሰችለት፡ «ልጁ በመኪና አደጋ ሞቶበታል፤ ቢሆንም ግን ልጅህ ያለብትን አሳሳቢ ሆኔታ ስለተረዳ ስንጠራው ያለበትን ትቶ መጣ። የልጅህን ህይወት ካዳነ በጟላ ግን ልጁን ለመቅበር ፈጥኖ ሄደ።»
-------
የሚታመሙ ልቦች ሆነው የማይናገሩ ኣሉ... ስለዚህ ሳታረጋግጥ ሰዎች ላይ አትፍረድ።

@Ethiomewlid