✧ ለሞተ ሙስሊም ቁርኣንን ማንበብ ይወደዳል ……… እቂል ኢብኒ የሳር ከተላለፈው ሀዲስ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ عن ﻣﻌﻘِﻞ ﺑﻦ ﻳَﺴﺎﺭ ﺃﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻗﺎﻝ : " ﺍﻗﺮﺀﻭﺍ ﻳـﺲ ﻋﻠﻰ ﻣﻮﺗﺎﻛﻢ " ﺭﻭﺍﻩ ﺃﺑﻮ ﺩﺍﻭﺩ ﻭﺍﻟﻨﺴﺎﺋﻲ ﻭﺍﺑﻦ ﻣﺎﺟﻪ ﻭﺃﺣﻤﺪ ﻭﺍﻟﺤﺎﻛﻢ ﻭﺻﺤﺤﻪ ﺍﺑﻦ ﺣﺒﺎﻥ . .... ለሙስሊም ሙታኖቸ ቁርኣን ፣ ዱዓ እና የሰደቃ ምንደ እንደሚደርሳቸው የተረጋገጠ ነው። ለሞተ ሙስሊም ቁርኣንን ማንበብ ከሰለፎች ግዜ ጀምሮ የተለመደ ሆኗል። የተወደደና ምስጉን ተግባር እንደሆነ ታላለቅ ኡለማኦች ተናግረዋል። ኢማም አል-ነወዊይ እንዳሰተላለፉት ኢማሙ ሻፊዒይ እንዲህ ብለዋል፦ « የሞተ ሰው ዘንድ ከቁርኣን የተወሰነው ቢነበብ የተወደደ ነው፤ ቁርኣንን ሙሉውን የኸተሙ እንደሆነ ደግሞ ተመራጭ ነው።» ﺭﻭﻯ ﺍﻟﺤﺎﻓﻆ ﺍﻟﻨﻮﻭﻱ ﻋﻦ ﺍﻹﻣﺎﻡ ﺍﻟﺸﺎﻓﻌﻲّ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﺃﻧﻪ ﻗﺎﻝ : ﻭﻳﺴﺘﺤﺐ ﺃﻥ ﻳُﻘﺮﺃ ﻋﻨﺪ ﺍﻟﻤﻴّﺖ ﺷﻰﺀ ﻣﻦ ﺍﻟﻘﺮﺀﺍﻥ ﻭﺇﻥ ﺧﺘﻤﻮﺍ ﺍﻟﻘﺮﺀﺍﻥ ﻋﻨﺪﻩ ﻛﺎﻥ ﺣﺴﻨًﺎ እንዲሁም በ "ሱነኑል በይሀቂይ" እንደተዘገበው: አብዱላህ ኢብኑ ዑመር ቀብር ለይ ሆነው የ"ሱረቱል በቀራ" የመጀመሪያውና የመጨረሻ አንቀፁን ማንበባቸው ተዘግቧል። @ethiomewlid 4.4K viewsedited 09:59