Get Mystery Box with random crypto!

Freelance Jobs Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofreelance11 — Freelance Jobs Ethiopia F
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofreelance11 — Freelance Jobs Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofreelance11
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 525
የሰርጥ መግለጫ

⭕️ Companies can post open job advertisements through our channel free of charge!
⭕️ Keep up to date for more than 20⁺ open job announcements per day.

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-12-01 17:37:26
#Qatar

ዛሬ ጥዋት የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በዶሃ ከኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒን በዶሃ ተገናኝተው በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ጋሬዎ ዘግቧል።

ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ በኳታር 2021 የፊፋ የአረብ ዋንጫ መክፈቻ ላይ የተሳተፉ ሲሆን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ቆያታቸውን በማጠናቀቅ ከዶሃ መውጣታቸውን ከኳታር ዜና አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@freeActNews
112 views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 16:36:04
#ቪድዮ

የኡጋንዳ ጦር ከጎረቤቱ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) ሃይሎች ጋር በመሆን በ Allied Democratic Force (ADF) ታጣቂ ቡድን ላይ በጋራ የአየር ድብደባ እና የመድፍ ጥቃት መፈፀሙን ትላንት አሳውቋል።

ዛሬ ደግሞ ኡጋንዳ ይህን የታጠቀ ቡድን ለማደን እና ለመቅጣት ጦሯን ድንበር አሻግራ ወደ ኮንጎ መላኳ ተሰምቷል።

የኡጋንዳ ባለስልጣናት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በካምፓላ ለደረሰው የአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ጥቃት ADFን ተጠያቂ አድርገዋል።

ይሄ የታጠቀ ቡድን በምስራቃዊ ኮንጎ ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ጥቃቶችን ፈጽሟል በሚል ይከሰሳል።

ሁለቱም ሀገራት ADF የተባለው የታጠቀ ቡድን በርካታ ሲቪል ሰዎችን መጨፍጨፉን ይገልፃሉ።

@freeActNews
110 views13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 16:31:04
ቪድዮ : የኡጋንዳ ጦር ከጎረቤት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) ሃይሎች ጋር በመሆን በ Allied Democratic Force (ADF) ታጣቂ ቡድን ላይ በጋራ የአየር ድብደባና የመድፍ ጥቃት መፈፀሙን ትላትን አሳውቋል።

በዛሬው ዕለት ደግሞ ኡጋንዳ ይህን የታጠቀ ቡድን ለማደንና ለመቅጥት ጦሯን ድንበር አሻግራ ወደ ኮንጎ መላኳ ተሰምቷል።

የኡጋንዳ ባለስልጣናት በዚህ ወር መጀመሪያ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ካምፓላ ለደረሰው የአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ጥቃት ADFን ተጠያቂ አድርገዋል።

ይሄ የታጠቀ ቡድን በምስራቃዊ ኮንጎ ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ጥቃቶችን ፈጽሟል በሚልም ይከሰሳል።

ሁለቱም ሀገራት ADF የተባለው የታጠቀ ቡድን በርካታ ሲቪል ሰዎችን መጨፍጨፉን ይገልፃሉ።

@freeActNews
95 views13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 16:09:04
የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር ኩዌት ናቸው።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከኩዌት ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሳባህ ካሊድ አልሃምድ አልሳባህ ጋር በሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ ተወያይተዋል።

አቶ አህመድ ዛሬ ህዳር 22 በኩዌት በሚገኘው ባያን ቤተመንግስት ተገናኝተው ነው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በኢትዮጵያና በኩዌት የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ ውይይት ያካሄዱት።

ውይይቱ ፍሪያማ እንደነበር የገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ በኩል ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን በኩዌት በኩል ፦
• የነዳጅና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ሞሀመድ አልፋሬስ፣
• የገንዘብ ሚኒስትር እና የኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ካሊፋ ሃማዳ
• የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና አማካሪ አብዱል አዚዝ አልዳኬል በውይይቱ ላይ ተገኝተው እንደነበር ከኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@freeActNews
80 views13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 16:08:07 #ተጨማሪ

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ገዳይ ሚኒስትር ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

አቶ ደመቀ በህወሓት የጦርነት አስተሳሰብ ምክንያት ስለጠፋው የሰው ህይወትና ስለወደመው ንብረት በዝርዝር አስረድተዋል።

አቶ ደመቀ ፥ " የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው ሰኔ ወር ባወጀው የአንድ ወገን ሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ውሳኔ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ህወሓት ለሰላም ጥረት ደንታ ቢስ መሆኑን አሳይቷል " ብለዋል።

" ምንም እንኳን የፀረ-መንግስት እንቅስቃሴዎች ቢደረጉም ፤ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ላደረጉ ወዳጆች ምስጋና ይግባቸውና ዛሬ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለው ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ነው " ብለዋል። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ጦር ግንባር ለመቀላቀል መወሰናቸውን ተከትሎ ጠላት ወደኃላ ሽሽት ላይ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።

አቶ ደመቀ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር እየተካሄደ ያለውን የኦሊሴጎን ኦባሳንጆን የሰላም ጥረት መደገፍ ቀጥለናል ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ችግሩ በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።

ዋንግ ዪ በበኩላቸው ቻይና እንደ ወዳጅ ሀገር የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለች መሆኗን ገልፀዋል። የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን ለመጫን የሚያደርጉትን ሙከራ እንደምትቃወም ተናግረዋል።

" ለማጨብጨብ ሁለት እጅ ያስፈልጋል " ያሉት ዋንግ ዪ ህወሓት የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበለትን የሰላም ሃሳብ መቀበል ነበረበት ብለዋል።

አገራቸው የኮቪድ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ከማጠናከር ባለፈ ከኢትዮጵያ ጋር በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በአቅም ግንባታና በልማት ትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

ቻይና የኢትዮጵያ መንግስት ሁኔታዎችን በቁጥጥር ስር እንደሚያውል እና መላው ኢትዮጵያውያንንና በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑ ቻይናውያንን ለመጠበቅ አቅም እንዳለው ታምናለች ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ፥ የዛሬው ጉብኝታቸው ቻይና የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ያለውን ሁኔታ እንደሚያረጋጋ እምነት እንዳላት የሚያሳይ እና ዜጎቿን ከአዲስ አበባ ከተማ የማስወጣት ጥሪዎችን በጭፍን አለመቀበሏን የሚያሳይ እንደሆነ ገልፀዋል።

በመጨረሻም በቻይናና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራና የማይበጠስ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል።

@freeActNews
70 views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ