Get Mystery Box with random crypto!

#ተጨማሪ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በኢትዮጵያ ም | Freelance Jobs Ethiopia

#ተጨማሪ

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ገዳይ ሚኒስትር ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

አቶ ደመቀ በህወሓት የጦርነት አስተሳሰብ ምክንያት ስለጠፋው የሰው ህይወትና ስለወደመው ንብረት በዝርዝር አስረድተዋል።

አቶ ደመቀ ፥ " የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው ሰኔ ወር ባወጀው የአንድ ወገን ሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ውሳኔ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ህወሓት ለሰላም ጥረት ደንታ ቢስ መሆኑን አሳይቷል " ብለዋል።

" ምንም እንኳን የፀረ-መንግስት እንቅስቃሴዎች ቢደረጉም ፤ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ላደረጉ ወዳጆች ምስጋና ይግባቸውና ዛሬ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለው ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ነው " ብለዋል። ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ጦር ግንባር ለመቀላቀል መወሰናቸውን ተከትሎ ጠላት ወደኃላ ሽሽት ላይ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።

አቶ ደመቀ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር እየተካሄደ ያለውን የኦሊሴጎን ኦባሳንጆን የሰላም ጥረት መደገፍ ቀጥለናል ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ችግሩ በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል።

ዋንግ ዪ በበኩላቸው ቻይና እንደ ወዳጅ ሀገር የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለች መሆኗን ገልፀዋል። የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን ለመጫን የሚያደርጉትን ሙከራ እንደምትቃወም ተናግረዋል።

" ለማጨብጨብ ሁለት እጅ ያስፈልጋል " ያሉት ዋንግ ዪ ህወሓት የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበለትን የሰላም ሃሳብ መቀበል ነበረበት ብለዋል።

አገራቸው የኮቪድ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ከማጠናከር ባለፈ ከኢትዮጵያ ጋር በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በአቅም ግንባታና በልማት ትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

ቻይና የኢትዮጵያ መንግስት ሁኔታዎችን በቁጥጥር ስር እንደሚያውል እና መላው ኢትዮጵያውያንንና በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑ ቻይናውያንን ለመጠበቅ አቅም እንዳለው ታምናለች ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ፥ የዛሬው ጉብኝታቸው ቻይና የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ያለውን ሁኔታ እንደሚያረጋጋ እምነት እንዳላት የሚያሳይ እና ዜጎቿን ከአዲስ አበባ ከተማ የማስወጣት ጥሪዎችን በጭፍን አለመቀበሏን የሚያሳይ እንደሆነ ገልፀዋል።

በመጨረሻም በቻይናና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራና የማይበጠስ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል።

@freeActNews