Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር ኩዌት ናቸው። የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከኩዌት ጠቅላይ | Freelance Jobs Ethiopia

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር ኩዌት ናቸው።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከኩዌት ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሳባህ ካሊድ አልሃምድ አልሳባህ ጋር በሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ ተወያይተዋል።

አቶ አህመድ ዛሬ ህዳር 22 በኩዌት በሚገኘው ባያን ቤተመንግስት ተገናኝተው ነው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በኢትዮጵያና በኩዌት የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ትብብር ላይ ውይይት ያካሄዱት።

ውይይቱ ፍሪያማ እንደነበር የገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ በኩል ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን በኩዌት በኩል ፦
• የነዳጅና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ሞሀመድ አልፋሬስ፣
• የገንዘብ ሚኒስትር እና የኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ካሊፋ ሃማዳ
• የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና አማካሪ አብዱል አዚዝ አልዳኬል በውይይቱ ላይ ተገኝተው እንደነበር ከኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@freeActNews