Get Mystery Box with random crypto!

Ethio techs Link

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_techs — Ethio techs Link E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_techs — Ethio techs Link
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_techs
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 39
የሰርጥ መግለጫ

✅ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @ethio_techs_group
✅Apps💽 👉 @ethioapps1
✅Games🎮 👉 @ethiogamestore
✅ለቻናሉ መስራች አስተያየትዎን ለመስጠት👇 @ethiotechsbot
✅YouTube 👇
https://www.youtube.com/channel/UCE1Op1fM_boEqB8xXqpjYxQ
✅Facebok Page 👇
http://Facebook.com/ethiotechs1

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-03-26 19:36:27 ጥያቄ ያላችሁ እንደተለመደው @ethio_techs_group ላይ ጠይቁን።

ማንኛውም አፕ ከፈለጉ @ethioapps1 ላይ ያገኛሉ።

ማንኛውም ጌም ከፈለጉ @ethiogamestore ላይ ያገኛሉ።
1.7K views⩙꠹ꪊᦔꪖꪀꪀꪖꫝ⩙, 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 20:07:48 እድሜ ለቴሌ ብር ስንመሰገን ውለናል

ቢያንስ ከ1 ሚሊየን #Spin (Transactions) መሀል 1 ሽልማት ይኖራል ብዬ እገምታለሁ #እንበርታ

በነገራችን ላይ በርካታ ፊውቸሮችን አካቷል እመለስበታለሁ...

                   #Share
@ethio_techs @ethio_techs
2.5K viewsPOLY, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 19:10:15
#JFF

                   #Share
@ethio_techs @ethio_techs
2.7K viewsPOLY, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 22:16:41 አዲሱ የንግድ ባንክ ኤቲ-ኤም ካርድ ላይ የሚፈረምበት ምክንያት የገባው አለ?

                   #Share
@ethio_techs @ethio_techs
1.4K viewsPOLY, 19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 19:40:35
#Waptrick ደጉ ጊዜ

                   #Share
@ethio_techs @ethio_techs
2.2K viewsPOLY, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 21:47:39 ሰው ሰራሽ አይን
ሰው ሰራሽ አይን (Bionic Eye)


በልዩልዩ ቀለሞችና በሚታዩ ነገሮች የተሞላች ሕይወት ውስጥ የእይታ ችሎታን እንደማጣት ከባድ ነገር የለም፡፡ በአሁኑ ሰዓት በአለማችን ላይ 40 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በአይነስውርነት ምክንያት ፍዳቸውን እያዩ ሲሆን 140 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ከዝቅተኛ የእይታ አቅም ጋር እየታገሉ ይገኛሉ፡፡ ይህን ጉዳይ እንደአገር ብንመለከተው ደግሞ፣ ለምሳሌ ህንድ በአለም ላይ ከሚገኙ አገራት በበለጠ በርካታ አይነስውሮች ያሉባት አገር ሆና እናገኛታለን፡፡ እንደሚታወቀው አይደለም ለረዥም ዘመን ለአንዲት ቀን እንኳን ያለ አይን ብርሃን የዕለት ተግባርን መከወን እጅግ አዳጋች ነው፡፡

ታዲያ ምን ተሻለ?

ምስጋና ለህክምና ሳይንሱ ጠበብቶችና ለቴክኖሎጂ ይሁንና የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የይለፍ ፍቃድ የሰጠውን ሰው ሰራሽ ዓይን በመፈብረክ ሰከንድ ሳይት የተባለ መቀመጫውን ካሊፎርኒያ ያደረገ አንድ ኩባንያ እይታን ዳግም መመለስ ችሏል፡፡

#ባዮኒክ_አይን

የባዮኒክ አይን አልያም ሰው ሰራሽ አይን ዓላማ እንደ ሬቲናቲስ ፒግሜንቶሳ ባሉ የዓይን ሕመም የሚሠቃዩ ሰዎችን እይታ ወደነበረበት መመለስ ነው። የምስል ሴንሰር፣ ማይክሮፐሮሰሰር፣ ተቀባይ፣ አስተላላፊ እና ሬቲናል ቺፖችን የያዘ ኤሌክትሮኒካል ስርዓት የሆነው ይህ አይን አይነስውሮችን ዳግም ማየት እንዲችሉ የማድረግ ብቃት አለው፡፡
የዚህ አይን ተከላ የሚካሄደው በሬቲና ውስጥ በሚገኙ ያልታመሙ ሴሎች ላይ ሲሆን የኮምፒዩተር ቺፑ በአይን ጀርባ ላይም ይቀመጣል፡፡ ይህ ቺፕ ደግሞ ሰውየው በሚለብሰው መነፀር ላይ ከተገጠመ አነስተኛ ካሜራ ጋር የሚገናኝበት ዘዴ አለው፡፡ በመቀጠል ካሜራው ላይ የተገኘውን ምስል ቺፑ አእምሮ ሊረዳው ወደሚችለው ኤሌክትሪካል ምልክት ይለውጠዋል፡፡ በዚህ አንድ አይነስውር የፈለገውን ነገር ልክ ተፈጥሮአዊ አይን እንዳለው ሰው ሁሉ መመልከት ይችላል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በባዮኒክ አይን አማካኝነት የሚታዩ ምስሎች ነገርየውን ለመለየት ግን በቂ ይሁኑ እንጂ ያን ያክል ግልጽ አለመሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡

በነገራችን ላይ ይህም ባዮንክ አይን ለበርካቶች ተስፋ ሰጪ ቢሆን ዳሩ የተወሰኑ ተግዳሮቶች አሉበት፡፡

- የመጀመሪያው ዋጋው በሁሉም ሰው ዘንድ የሚቀመስ አይደለም፡፡ለምሳሌ ለሁለት ጥንድ አይኖች እስከ 30ሺ ዶላር መክፈል ግድ ይላል፡፡

- በሁሉም አይነት የአይን በሽታዎች ለተጠቁ ሰዎች ይህ ሰው ሰራሽ አይን መፍትሄ ሆኖ መቅረብ አይችልም፡፡ ለምሳሌ በግላኮማ የተጠቃ ሰው ባዮኒክ አይኑ ብዙም የሚፈይድለት ነገር የለም፡፡

- ሰው ሰራሽ ነገሮችን በሰው ልጅ ሰውነት ውስጥ በንቅለተከላና መሰል መንገዶች ማስገባት በጣም አደገኛ ስለሆነ ህክምናው ምናልባትም ከከፍተኛ ጉዳት እስከ ሞት ድረስ ሊያደርስም ይችላል የሚል ስጋት አዝሏል፡፡

- ይህ ሰው ሰራሹ አይን ልክ እንደሰው ተፈጥሮአዊ አይን ስላልሆነ 100% ጥርት ያለ እይታ ላያስገኝ ይችላል፡፡

                   #Share
@ethio_techs @ethio_techs
1.2K viewsPOLY, 18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 21:45:04
ሰው ሰራሽ አይን
ሰው ሰራሽ አይን (Bionic Eye)


                   #Share
@ethio_techs @ethio_techs
1.2K viewsPOLY, 18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 14:55:34
ቴሌቪዥን ላይ #ጥቁር_ጥላ ለምን ይፈጠራል?

LCD ቴሌቪዥኖች በተለያየ ምክንያት ጥቁር ጥላ/dark shadow ሊፈጥሩ ይችላሉ። ከነዚህም ምክንያቶች መካከል ስክሪን ውስጥ የሚገቡ ቆሻሻዎች፣ ከላይ ስክሪኑ ሲቆሽሽ፣ የሞቱ ፒክስሎች (dead pixels) አሊያም የማይንቀሳቀሱ ፒክስሎች (stuck pixels) የተወሰኑት ናቸው። ከነዚህ መካከል የቀደሙት ሁለቱን በቀላሉ መፍታት ሲቻል በሞቱ እና በማይንቀሳቀሱ ፒክስሎች አማካኝነት የሚፈጠሩ ጥቁር ጥላዎችን ማጥፋት ግን ቀላል የሚባል አይደለም።

ምክንያቶቹ ምንድናቸው?

የማይንቀሳቀሱ እና የሞቱ ፒክስሎች በተለያዩ ምክንያቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ከነዚህም መካከል “burn in” አንዱ ነው። ይህም ቴሌቪዥኖች ላይ የማይንቀሳቀሱ ምስሎች ለረዥም ሰዓት ሲቆዩ የሚፈጠር ነው። የማይንቀሳቀሱ ምስሎች (still image) ቴሌቪዥን ስክሪን ላይ ለረዥም ጊዜ በሚቆዩ ጊዜ የቴሌቪዥኑ ስክሪን የምስሎቹን ቀለም የመያዝ እና የማስቀረት እድል ይኖረዋል። ይህም በረዥም ጊዜ የቴሌቪዥናችን ስክሪን ጥቁር ጥላ(black shadow) እና ጥቁር ነጥብ(black spot) እንዲያመጣ ምክንያት ይሆናል። ስለዚህ ቴሌቪዥናችንን ማንም በማይጠቀምበት ጊዜ መዝጋት ይመከራል።

በተጨማሪም የማይንቀሳቀሱ ምስሎች (ለምሳሌ ያቆመነው ቪዲዮ) ከግማሽ ሰዓት በላይ ቴሌቪዥኖች ስክሪን ላይ መቆየት የለበትም።

                   #Share
@ethio_techs @ethio_techs
2.3K viewsPOLY, 11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 12:08:12 ኖኪያ ከ60 አመት በላይ የተጠቀመበትን አርማ ሊቀይር ነው

ሰማያዊ ቀለም የነበረው የቀድሞው አርማ አምስት የተለያየ ቅርፅ ባላቸውና ሲገጣጠሙ ኖኪያን በሚፈጥሩ ቃላት ተተክቷል። ታሪካዊው የሞባይል ስልክ አምራች አሁን ላይ የቴሌኮም መሳሪያዎችን ለሌሎች ተቋማት ማቅረብ ላይ አተኩሯል።

ታሪካዊው የሞባይል ስልክ አምራች አሁን ላይ የቴሌኮም መሳሪያዎችን ለሌሎች ተቋማት ማቅረብ ላይ አተኩሯል

ታዋቂው የሞባይል ስልክ አምራች ኖኪያ ከ60 አመት በላይ የተገለገለበትን አርማ ሊቀይር መሆኑን አስታወቀ።

በሰማያዊ መደብ ላይ በነጭ ባሰፈረው ሰሙ አለምን ያዳረሰው ኖኪያ፥ አሁን ላይ ዘመኑን የዋጀ አርማ አዘጋጅቻለሁ ብሏል።

አዲሱ አርማ ኖኪያ የሚለውን ቃል የሚፈጥሩ አምስት የተለያየ ቅርፅ ያላቸው ፊደላት የያዘ ነው ብለዋል የኖኪያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፔካ ሉንድማርክ።

የአርማ ለውጡ ያስፈለገውም ኖኪያን አሁንም ድረስ ሞባይል አምራች አድርጎ የመቁጠር ዝንባሌ ስለሚታይ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ኖኪያ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ምርቶችን ለስማርት ስልክ አምራቾችና ለቴሌኮሙዩኒኬሽን ተቋማት በማቅረብ ላይ የሚገኝ የቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው።

ኩባንያው በተለይ በ5ጂ ኔትወርክ እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች በስፋት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስፈፃሚው ለሬውተርስ ተናግረዋል።
ኖኪያ እንደ ፈር ቀዳጅነቱ ባይሆንም ከስማርት ስልክ ገበያውም አልወጣም።

ለሌሎች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሚያቀርባቸው ግብአቶች ግን ከአመት አመት እየጨመሩ መሄዳቸው ተነግሯል።

ኖኪያ ባለፈው አመት እንኳን ከ2 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ ግብአቶችን ለመሰል የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አቅርቧል።

በህንድ ከሚገኘው ፋብሪካው ወደ አሜሪካ የሚልከው የስማርት ስልክ ቁጥርም በ2022 በ10 በመቶ ማደጉን ነው ዘገባው የሚያሳየው።

በፈረንጆቹ 1865 በፊንላንድ የተመሰረተው ኖኪያ በቴሌኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ትልቅ አበርክቶ ያለው ተቋም ነው።

                   #Share
@ethio_techs @ethio_techs
2.6K viewsPOLY, 09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 12:06:14
#EthioTechs_News

#ኖኪያ ከ60 አመት በላይ የተጠቀመበትን አርማ ሊቀይር ነው....

                   #Share
@ethio_techs @ethio_techs
2.5K viewsPOLY, 09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ