2023-07-22 16:41:11
ፔስጅ ለኪልያን ምባፔ የላከው ደብዳቤ:-
በመጀመሪያ በ2022 የፀደይ ወቅት የነበረው ውይይታችን ሁል ጊዜ ከፓሪስ ሴንት ጀርሜን ጋር እንድትቀጥል መሆኑን ማስታወስ አስፈላጊ ነው ፤ ለብዙ ዓመታት ለሙያህ የማይቻለውን እያደረግክ ስለዝውውር ጥያቄ ሲነሳምጥሩ ምላሽ እንድንሰጥ ከሚፈቅድ ቤተሰብህ ጋር በመሆን ተስማምተን ቆይተናል::
ይህ ስሜት በሁሉም ውይይታችን ውስጥ ነበር ፤ይህም ያለማቋረጥ በክለባችን ውስጥ የምንፈልገው በጎነት ነው። በተጨማሪም በዚህ መንፈስ በግንቦት 21 ቀን 2022 በፓርክ ዴስ ፕሪንስ ከ"2025" ማሊያ ጋር ፎቶ በመነሳት ትብብርህን አሳውቀሀል ይህም ለመላው ደጋፊዎቻችን እና ለአለም እግር ኳስ ማህበረሰብ ግልፅ ነበር።
ፒኤስጂ ያስታውሳል በእግር ኳስ ዓለም ውስጥ ኢንቨስትመንቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት የአንተ የወደፊት እጣ ፋንታ በዚህ ክረምት ብቻ ይወሰናል ወይም ከጁን 30, 2024 በኋላ የውል ማራዘሚያ ሊሆን ይችላል ይህም በእኛ መካከል በግልጽ የተመሰረተ እና የታወቀ ነው::
ሁሉም ታላላቅ ተጫዋቾች ክለባቸውን ትተው ፤ዘለቄታዊ ትሩፋትን ትተው ፤በተራው ደግሞ የረዳቸውን ክለብ በመርዳት ይደጋገፋሉ::
ክለቡ ባለፈው የበጋ የዝውውር መስኮት እራሱን ፈትሿል፣ ወደ ፈረንሣይ እና ሌሎች አውሮፓ ክለቦች መልማዮችን በመጠቆም ሌሎች ተጫዋቾችን በመተካት በከፊል ሊሳካ እንደሚችል ተገንዝቧል፤ ከአንተ ጋር ግን ከአቅማችን በላይ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነንም ፍላጎቶህን ለማሟላት ሞክረን ነበር (ሌላ ተጫዋች ከሚፈልገው በተለየ አድርገንልሀል) አሁን ይህ የክለባችን እቅድ አይደለም::
የዝውውር መስኮቱ ከተጀመረ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ የማራዘሚያ ውል እንደማትፈርም ደብዳቤህ ላይ የፈረምክ ይመስላል።
ስለዚህ ለእኛ ለተዋዋይ ወገኖች የተሻለውን አማራጭ አንድ ላይ ለመወሰን መገናኘቱ አጣዳፊ ነበር ይህም ለ 24/25 የውድድር ዘመን እድሳት ወይም በዚህ የዝውውር መስኮት መሸጥ የሚለውን በቅርብ ጊዜ በማወቅ የክለቡን ዘላቂ ችግር ማስወገድ የሚሉት ብቸኛ አማራጮቻችን ናቸው ለዚህ ውሳኔም ቀጠሮ ሰጥተንሀል::
በዚህ ቀጠሮ ላይ ደግሞ አንተ በፍጥነት መወሰን ስላልቻልክ ለመስማማት ስንል የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ምክትል ዳይሬክተር በመላክ ከአማካሪዎችህ ጋር ተገናኝተው ውሳኔህን እንዲነግሩን እናደርጋለን።
ይሄን ውሳኔ ስትወስን ግን ባለፉት ዓመታት ያለህን ቁርጠኝነት፣ በጎ ፈቃድ ፤ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ኢንቨስትመንት ስለወደፊቱ እንድታስብ እና ባለፈው ጊዜ ሁሉ ድጋፍ ያደረጉልህን የታላቁ ክለብ ደጋፊዎችን እንድታስቡ እንመኛለን።
[RMCsport]
@ETHIO_REAL_MADRID14
@ETHIO_REAL_MADRID14
3.3K views𝐁𝐥𝐚𝐧𝐜𝐨𝐬, 13:41