Get Mystery Box with random crypto!

FACT NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_factnews — FACT NEWS F
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_factnews — FACT NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_factnews
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 289
የሰርጥ መግለጫ

መረጃ ይከበር !!!

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 18:15:22 #ዜና ማሳሰቢያ

የዋግህምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ለባንኮች ማስጠንቀቅያ ሰጠ።

በሰቆጣ እና በሌሎች የዞኑ ከተሞች የሚሰሩ ባንኮች ባልተጨበጠ ሰበብ ባንኮቻቸውን መዝጋታቻው እንዳበሳጨው የዞኑ ምክር ቤት ባዛሬው ዕለት አስታውቋል።

በሰቆጣ ከተማ አና በዞኑ ከ70,000 በላይ ስደተኞች እንዳሉና ህዝቡም ቢሆን ባንኮችን እየተጠቀመ እና አግልግሎት እያገኘባቸው ሳለ ባልተረጋገጠ የሰላም እጦት መረጃ ባንኮቹን መዝጋታቸው ለታሪክ ውርደት መሆኑን እና ህዝብን እንደመካድ ሚወሰድ እንደሆነ ነው ያስታወቀው።

ባንኮቹም በፍጥነት ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ምክር ቤቱ አሳስቧል።
ሚመለከታችው  ባንኮች ---የኢትዮጵያ ንግድ ፣ አባይ፣ ዳሽን፣ አቢሲንያ፣ አንበሳ፣ አዋሽ፣ ቡና፣ ህብረት፣ አማራ፣ ፀደይ ባንኮች ናቸው።

@ethio_factnews
Share the fact
24 viewsedited  15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:20:19
አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በአዲስ አበባ ያሰራው ባለ 5 ኮከብ ሆቴል በቅርቡ ሊመረቅ መሆኑ ተነግሯል።

በይቻላል መንፈስ በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ጥራታቸውን የጠበቁ ሆቴሎችን እየገነባ የቆየው አትሌቱ አሁን ላይ ደግሞ በሸገር ላም በረት አካባቢ የተገነባው እና ሀይሌ ግራንድ የተሰኘውን ውብ ሆቴል በቅርቡ እንደሚመረቅ ነው የተነገረው። ሆቴሉ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እና ፕሬዘደንሺያል የሆኑ ክፍሎችን እንደያዘ ታውቋል ለምሽትም ክለብ በግሩም ሁኔታ ተዘጋጅቷል ነው የተባለው።

ለሆቴሉም የቅጥር እን የሠራተኞች ስልጠና መጀመሩ ስለታወቀ የሚመለከታችሁ እድሉን ተጠቀሙ!!

@ethio_factnews
እውነታን ያጋሩ
28 views10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:18:33 የውሸት ሰበር

የተለያዩ ሚድያዎች ቆቦ ተመልሳ በመከላከያ ቁጥጥር ስር ውላለች እያሉ በሰበር መልኩ እየተናገሩ ነው እውነታው ግን መከላከያ ቆቦን አልተቆጣጠራትም ግን በቅርብ ርቀት ውጊያ እያረገ መሀኑ ነው ታማኝ መረጃ ምንጮች የሚናገሩት።

በቆቦ ከተማ አሁን ላይ ስልክ እየሰራ አይደለም በወሬ ተለቃለች ቢባልም ምድር ላይ ያለው ግን ቆቦ አሁንም በህውሃት ስር መሆኗ ነው።

ሰላም ለሀገራችን
@ethio_factnews
Share the fact
166 views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:18:18 የተለያዩ የሰሜን ወሎ ከተሞች የሰዓት እላፊ እያወጁ ነው።

ካለው የፀጥታ ሁኔታ አንፃር ወልዲያ፣ደሴ፣ደባርቅ እንዲሁም ሌሎች ከምሽቱ 1:00 በኋላ እንቅስቃሴን አግደዋል እንዲሁም ከየትኛውም የፀጥታ ሀይል በስተቀረ የጦር መሳሪያ መያዝ በከተሞቹ ተከልክሏል።

@ethio_factnews
share the fact
55 views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:15:34 የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሼንን ለቀጣይ 4 አመት አቶ ኢሳያስ ጅራ እንዲመሩ ተመርጠዋል።

አቶ ኢሳያስ ጅራ--94
አቶ መላኩ ፈንታ--27
አቶ ቶኪቻ አለማየሁ---17
ድምፆችን ነበር ያገኙት

@ethio_factnews
እውነታን ያጋሩ!
52 viewsedited  17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 12:01:34 ህውሃት መግለጫ አወጣ


በሰላማዊ ወገኖች ላይ የሚፈፀም የአየር ድብደባ፥ የጠላቶቻችን ውድቀት የሚያፋጥን ነው!

ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ ሚካኤል

ፋሽስታወያኑ እያካሄዱት ያለው የቀቢፀ ተስፋ ግፎች ትግላችን የበለጠ እንድጠናክር እና ውድቀታቸውን እንዲያፋጠን ከማድረግ ውጭ መሬት ላይ የተከናነቡትን ሽንፈት ሊለውጠው እንደማይችል የትግራይ መንግስት ፕሬዝደንት ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ ሚካኤል አስታወቁ።

ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ ሚካኤል ዛሬ በ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ፋሽስቶች የጀኖሳይድ እቅዳቸው ለማሳካት ነሓሰ 20 2014ዓ/ም በመቐለ ከተማ እና ነሓሰ 19 2014ዓ/ም በመኾኒ አከባቢ በፈፀሙት የአየር ድብደባ በሰላማዊ ወገኖች ላይ እልቂት አስከትለዋል።

ህዝባችን የጠላቶቻችን ባህሪ እና ተግባር ግምት ውስጥ በማስገባት ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስታውሰዋል።

ደ/ፅዮን ገ/ሚካኤል የተናገሩት VIA DW
59 views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:50:56 ሰበር

ህውሃት ቆቦ ከተማን መቆጣጠሩን መንግስት አረጋገጠ።

በመከላከያ ሃይለኛ ክንድ ህውሃት እያከተመ ነው ሲል የነበረው መንግስት በ1 ቀን ውስጥ በስልታዊ ማፈግፈግ ቆቦን ለቆ ወቷል።

ከትግራይ እንደተሰደዱ በማስመሰል ቆቦ ውስጥ የነበሩ ሰርጎ ገቦች ሁኔታውን ከባድ እንዳረጉትን የከተማ ውጊያ በማድረግ የሚያልቀውን ህዝብ ለመታደግ ወደ ሌላ ይዞታ መመለሱን ነው መንግስት የገለፀው።

@ethio_factnews
እውነትን ያጋሩ
61 views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:33:53 #ዜና

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዘደንት መንበሩን ምርጫ ለማድረጎ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ በሸገር ጀምሯል።

ከዚህ ቀደም ጉባኤው በጎንደር ከተማ ይካሄዳል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ያለ አጥጋቢ ምክንያት በ አዲስ አበባ እንዲካሄድ ተወስኗል። ውሳኔውንም ተመልክቶ የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሸን ቅሬታ ማቅረቡ የሚታወስ ነው።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው ጉባኤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ለጎንድር ከተማ እና ህዝብ ክብር እንዳላቸውና በጦርነት የተጎዳውን የጎንደር ኢኮኖሚ ለማገዝ በማሰብ ለ2 ወር ያህል ውድድር እንዲካሄድ መደረጉን አስታውሰው። የትኛውም የመንግስት አካል ቦታ እንዲቀየር ትዕዛዝ መስጠት አይችልም ወሳኔውም የተለያዩ ጣልቃ ገብነቶች በመታየታቸው የተወሰደ አስተዳደራዊ እርምጃ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ለፕሬዘደንት ምርጫውም የወቅቱ
1 የወቅቱ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ
2.የአልማ እና የአማራ ባንክ ፕሬዘደንት የሆኑት መላኩ ፈንታ
3.አቶ ቶኪቻ አለማየሁ

እንዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች ለፕሬዘደንትነት ይወዳደራሉ።

ጥሩ አመራር የሚሰጠውን እና እግር ኳሱን የሚለውጥ ሰው እንዲያሸንፍ ምኞታችን ነው።

@ethio_factnews
Share the fact
57 viewsedited  17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:27:01 #ዜና ---የሰሜኑ ጦርነት አሁናዊ ሁኔታ

ህውሃት ግምባር ፈጥሮ ወደ አማራ ክልል ጥቃት ጀምሯል የሚል መረጃ መንግስት ከሶስት ቀናት በፊት አውጥቷል በዚህም ህውሃት ጦርነት እስትናፋሱ እንደሆነና የሰላም ስምምነቱን ጥሶ ኢትዮጵያን የማፈረስ እንቅስቃሴውን አስጀምሯል።--ዘፌደራል መንግስት

ብልፅግና የትግራይን ህዝብ ዳግም ችግር ውስጥ ለመክተት የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ ጦርነቱን በይፋ ከፍቷል በዚህም አብይ የሚመራው መንግስት በይፋ ወደ ትግራይ ጦርነት አውጇል። ዘ TPLF via DW

ታድያ ማነው ጦርነት ያስጀመረው ???

ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት የህውሃት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የሰላም ስምምነቱ ታክቲካሊ ፈረሷል ሲል ተናግሯል ይህም ህውሃት ወደ ጦረነት ለመግባት የበሩን ቁልፍ ፍለጋ መጀመሩን ያሳያል።
በተጨማሪም የመከላከያ አየር ሀይል ለህውሃት መሳሪያ ሊያቀብል የነበረ የጦር ድንበር ላይ ተመቶ ወድቋል ሲል ተናግሯል።
መመታቱ እውነት ከሆነ ጦርነቱ በህውሃት መጀመሩን ልናረጋግጥ እንገደዳለን! ምክንያቱም የጦር አውሮፕላኑ መሳሪያ ሊያቀብል ሲል የተመታው ከጥዋቱ 3:30 ላይ ነው ጦርነቱ ዳግም የተጀመረወ ደግሞ ከሌሊቱ 11:00 ላይ ነው ታድያ በዚች የሰዓታት ክፍተት ውስጥ ህውሃት የሚረከበው መሳሪያ በመቼው ሰለ ጦርነቱ መጀመር ምን አውቆ ነው ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው? ስለዚህ ህውሃት ጦርነቱን ለመጀመር ቀደሞዎኑ ስላሰበ ነው መሳሪያ ድጋፍ ከወዳጆቹ የጠየቀው ብለን ልነወስን ይቻለናል ማለት ነው።

በተጨማሪም የመከላከያ አየር ሀይል ሀይል ትናንት በመቀሌ የትግራይ ቴሌቪዥን ማሰራጫ ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተናግሯል።

ህውሃት ደግሞ በህፃናት መጫወቻ እና ትምህርት ቤት ላይ የአየር ድበደባ ተከናወኖ በዞዎች መጎዳታቸውንና መሞታቸውን በቪድዮ ማሰረጃ ተደግፎ ለዓለም ህዝብ አሳውቋል።

ከታማኝ መረጃ ምንጮች እንደተመለከትነው 4 ሰዎች (ህፃን መሆናቸው ያልተረጋገጠ) በአየር ድብደባው መሞታቸው እና ህፃናት መጎዳታቸው ተነግሯል ከቃል መረጃ ይልቅ የቪድዮ መረጃ ተገቢ ስለሆነ መቀሌ ላይ የደረሰው የአየር ድበደባ ምናልባትም ህፃናት የሚገኙበት ስፍራ ሊሆን ይችላል የሚሉ የተለያዩ ፍንጮች ይሳዩናል።

የአየር ድበደባው የደረሰበት ቦታ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ቪድዮ እጃችችን ላይ ቢገኝም ለተመልካች የሚቀርቡ ስላልሆኑ ላለመልቀቅ እንገደዳለን

@ethio_factnews
FACTን ያጋሩ
134 viewsedited  11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 13:55:50 ለተመልካች ማይቀረቡ መረጃዎች እዚህ ቦታ የላቸውም ከ ምንም ከማንም ለማንም አይደለንም ግን ከኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ ነን።

ጦርነቱን ተመልክቶ ለTPLF ሆነ ለፌደራል መንግስት የወገኑ ፕሮፖጋንዳዎች እዚህ አይገኙም ማንም ኢትዮጵያዊ የሚገባው መረጃ በFACT NEWS !

በቅርቡ
Coming soon

@ethio_factnews
55 viewsedited  10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ