Get Mystery Box with random crypto!

#ዜና ---የሰሜኑ ጦርነት አሁናዊ ሁኔታ ህውሃት ግምባር ፈጥሮ ወደ አማራ ክልል ጥቃት ጀምሯል የ | FACT NEWS

#ዜና ---የሰሜኑ ጦርነት አሁናዊ ሁኔታ

ህውሃት ግምባር ፈጥሮ ወደ አማራ ክልል ጥቃት ጀምሯል የሚል መረጃ መንግስት ከሶስት ቀናት በፊት አውጥቷል በዚህም ህውሃት ጦርነት እስትናፋሱ እንደሆነና የሰላም ስምምነቱን ጥሶ ኢትዮጵያን የማፈረስ እንቅስቃሴውን አስጀምሯል።--ዘፌደራል መንግስት

ብልፅግና የትግራይን ህዝብ ዳግም ችግር ውስጥ ለመክተት የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ ጦርነቱን በይፋ ከፍቷል በዚህም አብይ የሚመራው መንግስት በይፋ ወደ ትግራይ ጦርነት አውጇል። ዘ TPLF via DW

ታድያ ማነው ጦርነት ያስጀመረው ???

ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት የህውሃት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የሰላም ስምምነቱ ታክቲካሊ ፈረሷል ሲል ተናግሯል ይህም ህውሃት ወደ ጦረነት ለመግባት የበሩን ቁልፍ ፍለጋ መጀመሩን ያሳያል።
በተጨማሪም የመከላከያ አየር ሀይል ለህውሃት መሳሪያ ሊያቀብል የነበረ የጦር ድንበር ላይ ተመቶ ወድቋል ሲል ተናግሯል።
መመታቱ እውነት ከሆነ ጦርነቱ በህውሃት መጀመሩን ልናረጋግጥ እንገደዳለን! ምክንያቱም የጦር አውሮፕላኑ መሳሪያ ሊያቀብል ሲል የተመታው ከጥዋቱ 3:30 ላይ ነው ጦርነቱ ዳግም የተጀመረወ ደግሞ ከሌሊቱ 11:00 ላይ ነው ታድያ በዚች የሰዓታት ክፍተት ውስጥ ህውሃት የሚረከበው መሳሪያ በመቼው ሰለ ጦርነቱ መጀመር ምን አውቆ ነው ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው? ስለዚህ ህውሃት ጦርነቱን ለመጀመር ቀደሞዎኑ ስላሰበ ነው መሳሪያ ድጋፍ ከወዳጆቹ የጠየቀው ብለን ልነወስን ይቻለናል ማለት ነው።

በተጨማሪም የመከላከያ አየር ሀይል ሀይል ትናንት በመቀሌ የትግራይ ቴሌቪዥን ማሰራጫ ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተናግሯል።

ህውሃት ደግሞ በህፃናት መጫወቻ እና ትምህርት ቤት ላይ የአየር ድበደባ ተከናወኖ በዞዎች መጎዳታቸውንና መሞታቸውን በቪድዮ ማሰረጃ ተደግፎ ለዓለም ህዝብ አሳውቋል።

ከታማኝ መረጃ ምንጮች እንደተመለከትነው 4 ሰዎች (ህፃን መሆናቸው ያልተረጋገጠ) በአየር ድብደባው መሞታቸው እና ህፃናት መጎዳታቸው ተነግሯል ከቃል መረጃ ይልቅ የቪድዮ መረጃ ተገቢ ስለሆነ መቀሌ ላይ የደረሰው የአየር ድበደባ ምናልባትም ህፃናት የሚገኙበት ስፍራ ሊሆን ይችላል የሚሉ የተለያዩ ፍንጮች ይሳዩናል።

የአየር ድበደባው የደረሰበት ቦታ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ቪድዮ እጃችችን ላይ ቢገኝም ለተመልካች የሚቀርቡ ስላልሆኑ ላለመልቀቅ እንገደዳለን

@ethio_factnews
FACTን ያጋሩ