2023-02-01 23:33:18
እንደዛሬ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ውስጤ እረክቶ አያውቅም፡፡
፡፡፡ ፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ዋናው መልእክት
የ EOTC ሲኖዶስ በሰጠው መግለጫ ጥጠሚ አብይ አህመድ ትላንት ለካቢኔው የተናገራቸውን ስህተቶች አንድ በአንድ ነቅሶ አውጥቷል::
ዋና ዋናዎቹ ነጥቦች:-
1- ህገወጡን ሲኖዶስ ከህጋዊው ሲኖዶስ ጋር አቻ አድርጎ ማቅረብ
- ስህተት
2- ጉዳዩ ቀላል በድርድር የሚፈታ ነው ያለው
(ከባድ ቀኖናዊ ጥሰት በመኾነኑ)
- ስህተት
3- ሁለት ፓትርያርክ ሃገር ላይ ነበር ያለው
- ውሸት
4- ትግራይ ጳጳስ ተሹሞ ፣ ሲኖዶስ ተቋቁሞ ነበር ያለው
- ውሸት
5 - ባለፈው 4ዓመት ለ EOTC ተሰጠ ያለው መሬት - (ቤ/ክ already በስሯ ላሉ ለይዞታዋ ህጋዊ ካርታ ነው የወሰደችው)
- ውሸት
6- ጠ/ሚው በግልፅ ለህገወጡ ስብስብ ድጋፍ ማሳየቱ ፣ መንግስት ህጋዊ እውቅና ላለው የቤ/ክ ሲኖዶስ ህግ በማስከበር መተባበር ሲገባው .. በተቃራኒ ቆሞ ህገወጦችን ማገዙ ፣ አባቶችን ማዋከብ ና ማሰሩ
- ህገወጥ
7- በቋንቋ መጠቀምን በተመለከተ ቤ/ክ ላይ ያቀረበው ክስ .. በኦሮምኛ ቋንቋ መገልገል ብቻ ሳይኾን መፅሃፍትም እንደታተሙ ፣ መንፈሳዊ ኮሌጆችም እደተከፈቱ ፣ ህገወጥ ተግባር ላይ ያሉትም ሰዎች በዚችው ቤ/ክ የተሾሙ እንደነበሩ በመጥቀስ
- ውሸት እንደኾነ አሳይቷል::
1.2K viewsየኤፍሬም እይታዎች, 20:33